🔺🕆ያህዌህ-ንሲ🔱🛐


1735 Members

🕆ያህዌህ-ንሲ🕆
(ኦሪት ዘፀአት 17:15)
*እግዝያብሄር አላማችን ነው*
ለጌታ መኖር ህይወትን ትርጉም የሚሰጠው ብቸኛ ነገር ነው
ስሙ በኛ የሚከብርበት እንጂ የሚሰደብበት አንሁን
መንገድ ይቃና አይኖች ይገለጡ የመስቀሉ ስራ አይረሳንም

#አባቢዬእኖርልሃለሁ
{links} {LinksTitle}
{/links}
Today Views : 0
Yesterday Views : 0
One Year Views : 53
📖Word of the day📖 (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕ. 1) ---------- 10-11፤ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል። 12፤ ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፥ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፥ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ። 13፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ፤ 14፤ መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ። @yaweh_nissi
2019/09/21 19:48
📖📖የእለቱ ቃል📖📖 (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ. 2) ---------- 6፤ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ 8፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። 9፤ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ 10፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ 11፤ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። @yaweh_nissi
2019/09/17 08:45
📖የእለቱ ቃል📖 (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 17) ---------- 10፤ ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። 11፤ እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር። 12፤ የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ። 13፤ ኢያሱም አማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ። 14፤ እግዚአብሔርም ሙሴን። የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ ተናገር አለው። 15፤ ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም ይህዌህ ንሲ ብሎ ጠራው፤ 16፤ እርሱም። እጁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለጫነ የእግዚአብሔር ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ለልጅ ልጅ ይሁን አለ። GOD is our Banner!!! እግዝያብሄር አላማችን ነው! እግዝያብሄር አርማችን ነው! @yaweh_nissi
2019/09/16 09:47
edit title
2019/09/15 23:37
📖Word Of the Day📖 (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕ. 6) ---------- 11፤ አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል። 12፤ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/08/26 19:27
📖Motivation of the Day📖 🎙🔊ማስታወቂያ🔊🎙 በየጊዜው አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች ሲወጡ በመጀመሪያ ወደ ገብያ ከመውጣቱ በፊት ማስታወቂያ ተሰርቶለት ይተዋወቃል፤ ማስታወቂያው እውነት ሆነ ውሸት ሰዎች በሚያዩበት ጊዜ በአእምሮአቸው ውስጥ የሚጭረው ሀሳብ መኖሩ አይቀርም፤ ከዚያ ያው ውጤት በሰዎች ሲወራበት ደግሞ እርሱን ነገር ለመያዝ መሮጥ ይጀምራል። ይሄ ሁሉ ነገር የሚደረገው፤ አንድ ድርጅት ለማስታወቂያ በሚልዩናት ገንዘብ የሚያወጣው የፈጠረው ስራ ለሰው ሁሉ ለማስተዋወቅ ካለው ፍላጎት የተነሳ ነው። ደግሞም በእውነትም ካለ ማስታወቂያ የፈጠረው ፈጠራ ባይፈጥረው ይሻለዋል እንጂ መቼም ቢሆን የሚፈልገው ደረጃ አይደርስለትም። እኛ የፈጠራ ውጤታችን ያልሆነ፤ እውነት ማስታወቂያ ተስርቶለት እንደሌላው የተካበደ የማይመስልበት፤ ከሰማይ በታች ወደ አብ ማድረሻ አማራጭ የሆነ፤ በምድር በፊት አሁንም ወደ ፊትም ታእምራቱ የማያልቅ፤ እኛን ከጠፋው ህይወታችን በሞቱ የታደገን፤ አለም አይቶት የማያውቀውን ሰላም በልባችን ያስቀመጠ ከእርሱ ሌላ ማንም በሌለበት ብቸኛ አዳኝና ታደጊ በሆነበት አለም ላይ ያለነው እየሱስ የሚባል ስጦታ ተሰቶናልና ፤ የአባታችንን ማንነት ለማያውቁት ዘወትር እናስተዋውቀው። አንድን ነገር ብቻ ሳይሆን ሁለንተናን የሚቀይር አምላክ ነው! ስሙ ይባረክ! ተናገሩ፤ መስክሩ፤ አስታዋውቁ ህይወታቹ ማስታውቂያ ሆና ለአለም የአዳኛችሁን ስራ ትመስክር!! @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪💪
2019/08/20 18:41
📖📖Word of the day📖📖 1 Timothy Chapter 2 #Read #Understand #Letthewordspeaktoyou #Nofeminism @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/08/18 15:41
📖📖Word of the day📖📖 1 Timothy Chapter 1 #Read #Understand #Letthewordspeaktoyou @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/08/12 20:01
በክርስቶስ አይን ማየት
🎙🎙 🔊🔊 የዛሬው መስማት የሚገባቹ መልዕክት 👓ራስን በክርስቶስ አይን ማየት👓 👂አድምጡት👂 @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/08/08 23:42
ፀሎት ብዙዎቻችን በብዙ ሰዎች ለምን እንደምንፀልይ ይጠይቁናል። ብዙ አይነት ነገሮችን መልስ አርገን ልናስብ እንችላለን፤ እናም ለሁላችን የዚህ ጥያቄ መልስ በጣም የተለያየ ነው። ግን ምንም አይነት ምክንያት ቢሆን አንድ ሰው እውነተኛ ክርስቲያን ከሆነ ለእግዝያብሄር የሚንበረከክበት ጊዜ በናፍቆት ነው የሚጠባበቀው፤ ነገር ግን ስንቶቻችን የፀሎት ጊዜያችንን ብንጠብቅ ምን ያህል መፀለይ እንዳለብን አናውቅም። በመንፈስ እየፀለይን ከሆነ ጊዜው ሳይታወቅ ያልቃል፤ መንበርከካችንን ሳናውቀው ሰአታት አልፈው እንነሳለን፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በአእምሮ ስንፀልይ የፀሎት ርዕሶቻችንን እየመረጥን አንዱን ሳናነሳ መነሳት ስለማንፈልግ ፀሎታችን ሳናውቀው የጥያቄ ጋጋታ ይሆንብንና ደቂቃዎች ሳይቆጠሩ ጨርሰን እንነሳለን። ስለዚህ ፀሎት ምን ሲሆን ነው የሚያጥረው??? ረጅም ፀሎት ምን ያህል ሲሆን ነው??? ፀሎት አጥሮ በሙሉ ልብ ቢሆን ወይስ ቢረዝም የትኛው ይሻላል?? በሚቀጥለው ሳምንት እነዚህ ጥያቄዎችን ልመልስ እሞክራለሁ በድምፅ የሚቀርብ ት/ት ከሰኞ ጀምሮ በJFM ይጠብቁን!! @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/07/28 14:26
📖Today's Message📖 ኧረ ምን አይነት ድፍረት ነው? እየሱስ ክርስቶስ እኔን ምሰሉ ብሎ ሲናገር የእርሱን የፅድቅ መጠን እያየን የእኛን ኑሮ ስናየው ደግሞ መቼም የማይሆን ነገር ይመስለናል፤ ነገር ግን እየሱስ ክርስቶስ የማንችለውን ነገርሰአድርጉ አይለንም፤ በዚያ ላይ ደግሞ የማይቻል የሚመስል ነገርን ሀዋሪያው ፖውሎስ ሲያደርገው አይተናል። " እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1) ፖውሎስ እዚህ ደረጃ የደረሰው ከፃፋቸው መፅሀፍ ላይ እና ከሀዋሪያት ስራ ላይ መመልከት እንደምንችል ከእየሱስ ክርስቶስ ያለውን ህይወትና ቁርኝት እናያለን፤ ለእግዝያብሄር ያለውን አክብሮትን ትህትና ቅንነት ነበረው። ግን ከምንም ነገር በላይ እርሱን ክርስቶስ በደማስቆ መንገድ ላይ ካገኘው በኋላ በኋላ ሰው ልኮ ለፖውሎስ ሲፀለይለት በመጀመሪያ አይኑ ተከፈት፤ እግዝያብሄር የሚሰራውን እና ሊሰራ የወደደውን ነገር አሳየው። ከዚያም ሃይል ተቀበለ ይላል ቃሉ፤ ያየውን ነገር ለማሳካት መለኮታዊ ሃይል እንደሚያስፈልገው ያውቅ ነበርና። ስለዚህ የዛሬ መልዕክቴእግዝያብሄርን ያየላችሁን ነገር ለማሳካት ይህ የስጋ ህይወትና ምርኮ ለማረግ የጌታ ሃይል ያስፈልጋል፤ እየሱስ ክርስቶስን የረዳው ሃይል፤ ፖውሎስ ክርስቶስን እመስላለሁ ለማለት ድፍረት የሰጠውን ኑሮ እንዲኖር ያደረገው ሃይል፤ ስለዚህ ሌላው ነገር ይቅርብንና ለእርሱ ለጌታችን የሚገባውን አይነት ህይወት እንድኖርለት ፤ ሩጫችንን የሚያስጨርሰን፤ እርሱ ያሰበለንን ነገር እንድንሆን የሚያስችለንን ሃይል እንዲሰጠን እንለምነው፤ እርሱ ነው የሚያዋጣን እመኑኝ። @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/07/14 15:48
📖Today's Message📖 እግዝያብሄር በደሙ የዋጀን ልጆቹ ነን፤ በማንኛውም ነገር ሳይሆን አንድያ ልጁን አሳልፎ ለሞት በመስጠቱ ነው ፍቅሩን የገለፀልን። አስገድዶን ወይም አስፈራርቶን ሳይሆን ፍቅሩና ቸርነቱ ፤ ትዕግስቱና መሃሪነቱ ገዝቶን ይኸው እስካሁን በቤቱ አለን። ስለዚህ ለዚህ ጌታችን እኛ ካልኖርልነት ማን ሊኖርለት ነው???? አለማዊውም እንደ አለማዊ ክርስቲያኑም እንደ አለማዊ እየኖረ ካለ፤ ገብቶን እንዳልገባን፤ አይተን እንዳላየን፤ ሲያወሩ እያወራን፤ ሲናገሩ እየተስማማን፤ ሲኖሩ እየተቀላቀልን፤ ሀይል እያለን ልፍስፍስ፤ ተስፋ እያለን የሞተ የምንሆን ከሆነ ታዲያ እኔን ምሰሉ ብሎ የተናገረው ለእኛ ካልሆነ ለማን ነው??? የዛሬው መልዕክቴ ለአምላካችን ለመኖር እንትጋ፤ የፍቅር እና የምህረት አምላክ ስለሆነ ብቻ መሃሪነቱን እያየን አንዝናናበት፤ ልብ በሉ "እግዝያብሄር አይዘበትበትም: ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል" ይላል ቃሉ። ስለዚህ በምድር ሳለን ለጌታ ተለይተንለት እንኑር፤ ሩጫችንን እንሩጥ፤ ለመዳን ጠርቶናል ለአክሊል ሰርተን እናስደስተው ፤ እግዝያብሄር የሚወዱትን የሚሸልም አምላክ ነው፤ ከወደድነው ደሞ መኖር እንደሚነባን በቅድስና እንኑር፤ ታዲያ እርሱ ፍቅሩን በሞት አሳየን፤ ለእኛ ምልክታችን ምን ይሁን??? ፍቅርን በፍቅር፤ ተግባርን በተግባር እንመልስ!! @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/07/11 08:19
📖Word of the Day📖 (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕ. 9) ---------- 23፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ 24፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር። @jesusfreakmotivation 💪💪💪💪💪
2019/06/21 08:38
📖📖Today's Message📖📖 Release Whatever is Holding you back Pastor Micheal Todd Message from Transformation Church በጣም የሚባርክ መልዕክት ነው አድምጡት @jesusfreakmotivation
2019/06/09 11:18
📖Today's Message📖 ❤ፍቅር እንስጥ እንጂ❤ በክርስትና ህይወታችን ውስጥ በብዙ ነገር መማር ይቀረናል፤ ለዛም ይመስለኛል በብዙ የምንፈተነው ከዛሬ ነገ እንድንሻል በማለቱ ነው። ግን አንድ ነገር በምንም የማንከራከረው ነገር ልክ ክርስትያን ስንሆን የገባን ነገር የፍቅር ጉዳይ ነው። ፍቅር እውነተኛ ከሆነ በብዙ ነገር መገለጥ የሚችልና ብዙ እብደት የሚመስሉ ነገሮች የሚያስደርግ ነው እንደ ደም ላብ ማላብ፤ መስቀልን ተሸክሞ መሰቀል፤ ህይወትን አሳልፎ መስጠት ግን ይህ ነገር እብደት የሚመስለው ለጠላውና ለካደው እርሱ ፃድቅ ሆኖ ለሀጥያተኛው ማድረጉ ነው፤ የኔ ጌታ እየሱስ። አሁን ደግሞ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ የተፃፈው ፍቅር በኛ ውስጥ አለ?? ብዬ መጠየቅ ጀምሬ በእርግጥ ደነገጥኩ፤ እንኳን ለሰው ሀጥያት ልንሞት ቀርቶ የበደለንን ሰው ይቅር ማለት እንደጭነት የከበደብን፤ እንደው ፀጋ በዝቶ ይቅር ብንል ቂም ውስጣችን ይዘን የማንረሳ አይነት ሰዎች መሆናችንን ሳውቅ ታዲያ እንዴት አልደንግጥ? " ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።" (የማቴዎስ ወንጌል 24:12) ታዲያ እየሱስ የነገረን የፍቅር አይነት በየት በኩል አመለጠን? በየት በኩል ጠፋ? በምን እናግኘው? ከወዴትስ እንፈልገው? እንደዚህ አይነት ፍቅሩ የት ሄደ?? እርሱን ጥያቄ እስኪ ራሳችሁን ጠይቁ እኔ ምንም አልልም ራሳችሁን እንድትጠይቁ ነው የምፈልገው!! @jesusfreakmotivations
2019/06/05 17:24
📖Today's Motivation📖 🤔 የቱ ጋር ቀረ??🤔 ሉቃስ ምዕራፍ ሁለት ላይ ሙሉውን ስታነቡት ዮሴፍና ማርያም በመንገድ ላይ ሳሉ እየሱስ በ12 አመቱ ከእነርሱ ኋላ መጥፋቱን ያወቁት ካሰቡበት ሲደርሱ ነው። ይህንን ነገር ለምን አነሳቹ ብላቹ ብትጠይቁ መልሱ ይህ ነው። ብዙዎቻችን ክርስቲያን ከሆንን በኋላ ካሰብንበት ስንደርስ እየሱስ ክርስቶስ በመንገድ ላይ በሆነ ሰአት ላይ ጠፍቶብን ማርያምና ዮሴፍ የራሳቸውን ወሬ እያወሩ በእርሱ ተውጠው እየሱስ መጥፋቱን እንዳላወቁ ሁሉ እኛ በስኬት ጎዳና እያለን ከሚመጣው ማንነት ማጣት፤ ብዙ ገንዘብ፣ ተፈላጊነትና ዝና እናም የመሳሰሉት አእምሮአችንን ይዘው ቸርች መሄድ ከፍላጎት ወደ ልማድ፤ ፀሎት ከምስጋና ወደ ጥያቄ፤ ሰአት ከእግዝያብሄር ቤት ይልቅ ወደ ራስ ጉዳይ ሲቀየር ያኔ እየሱስ ክርስቶስ ጠፍቷል ማለት ነው። ስኬት በዚች ምድር ላይ ከኛ ይልቅ ለአህዛብ እንደሚቀለው እናውቃለን፤ ምክንያቱም አለም ናት ስኬትን የምትሸልመው ሴጣን ደግሞ የዚች አለም ገዢ ነው፤ነገር ግን የክርስቲያን በዚች ምድር መሳካት ከአህዛብ መለየት ያለበት የእየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ህልውና በመኖሩ ነው። ስለዚህ የዛሬው መልእክቴ በመንገዳቹ እየተራመዳቹ በት/ት ሆነ በስራ በማንኛውም የህይወት ጎዳና የእግዝያብሄር ህልውና ፤ የለህይወታቹ ትርጉም የሚሰጠው ነገር ከአጠገባቹ አለመጥፋቱን ዞር ብላቹ ማየታችሁን እንዳትረሱ፤ እውነት የመንፈሳዊ ህይወታችሁን ሁሌ መፈተናችሁን እርግጠኛ ሀኑ፤ ከእግዝያብሄር ያላችሁን ግንኙነት ጥብቅ መሆኑን አረጋግጡ፤ ምክንያቱም እነርሱ እየሱስን ሲያጡት ወደኋላ የመጡበትን መንገድ እንደሄዱ ሁሉ ያለ እየሱስ የተገኘ ማንኛውም ክብር አሁንም ሆነ በኋላ ወደ ኋላ ሳይመለሳቹ አይቀርም፤ ደግሞም እየሱስ የሌለበት ስኬት ለእናንተም ውርደት ነው እንጂ በፍፁም ክብር ሊሆን አይችልም። @jesusfreakmotivations
2019/05/30 09:46
📖Today's Message📖 👂ድምፁን ሰምታችሁት ታውቃላቹ?👂 አንድ ህፃን ልጅ በእናቱ ማህፀን ውስጥ ተፀንሶ ባለበት ጊዜ ከምንም በላይ የሚሰማውና የሚለምደው ድምፅ የእናቱን ልብ ምት ነው። ከዚያም ከተወለደም በኋላም የእናቱን ልብ ምት ድምፁን ስለማይረሳው ሌላ ሰው አቅፎት አላቆምም ያለውን ለቅሶ እናቱ ወደ ራሷ አስጠግታ ስትይዘው ለቅሶውን አቁሞ ይረጋጋል፤ ምክንያቱም የእናቱን ልብ ምት ስለሚያረጋጋው ነው። እኛ በብዙ የህይወት ነውጥ ውስጥ የምናልፍ ሰዎች ነን፤ ግን በብዙ ነገር መረጋጋትን አተን ከማያምነው ጋር እኩል ወየው ጉድ ፈላ ብለን እንጮሃለን፤ ምክንያቱም በጭራሽ ያባታችን ድምፅ ሊያረጋጋን ቢመጣም ስላልመድነው ሊያረጋጋን አይችልም። የእግዝያብሄርን ድምፅ እንዴት ነው ልናውቅ የምንችለው ልትሉ ትችላላቹ፤ እርሱም አንድና አንድ መልሱ ከእግዝያብሄር ጋር ጊዜ ማሳለፍ ስንጀምር ነው። መፀለይ ባበዛን ቁጥር እኛ ለእየሱስ ክርስቶስ ነገሮቻችንን በነገርነው ቁጥር እርሱም የልቡን ሃሳብ ለልጆቹ የሚሳውቅ አምላክ ነው እንደሚል ቃሉ ያናግረን ይጀምራል፤ ይሰማን ይጀምራል። ከዚያ ያንን ድምፅና ሰላሙን በተለማመድነው ቁጥር ሁከት ሲመጣ ከሌላው ጋር ከመዋከብ ወደሚያረጋገን ወደ እግዝያብሄር መንበርከክ የመጀመሪያ የመፍትሄ ሃሳባችን መሆን ይጀምራል፤ ከዚያም ለኛ በተሰጠው ሰላም በሁከት ውስጥ ያሉ ሰዎች የእግዝያብሄርን ሰላም ማየት ይጀምራሉ፤ ከእርሱ ጋር መሆን ያለውን ልዩነት በኛ ውስጥ ያያሉ። ከመፅሀፍ ቅዱሳችን ጋር በዋለን ባደርን ቁጥር፤ ቃሉን ባነበብን ቁጥር ጌታችን በመጀመሪያ ደረጃ በቃሉ ስለሚናገር እያንዱንዱ ቃል ለኛ የእግዝያብሄር ድምፅ ይሆናል፤ በወረቀት ላይ ከተደረደሩ ቃላት ይልቅ የየሚያረጋጋን አለት ሆኖ ይቀመጣል። ስለዚህ የእግዝያብሄር ድምፅ ያረጋጋል፤ ያስደስታል፤ ያረካል ነገርግን መጀመሪያ ልንሰማው ይገባል፤ ስለዚህ ከጌታ ጋር ያለንን ጊዜ በደንብ እንጨምር፤ ከእርሱ ጋር ጊዜ ሳናሳልፍ ቀኑ መሽቶ እንዳይነጋባቹ ባይ ነኝ። @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/05/27 22:37
📖Today's Message📖 ደግ ወይስ መልካም?? ብዙ ሰዎች ደግ እና መልካም የሚሉትን ቃላት ያምታቱታል። ኤኔም ከዛሬ በፊት ከነዚያ ሰዎች አንዱ ነበርኩ፤ ግን አንድ ቀን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ስከፍት ፍፁም የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ተረዳው። ደግ ማለት አንድ ነገር ስጠይቁት የተጠየቀው ነገር በእጁ ላይ ካለ ሳያንገራግርና ጥያቄዎችን ሳይጠይቅ አሳልፎ የሚሰጥ ሰው ነው። መልካም ሰው ማለት ለእናንተ ጥሩ የሚያስብ ሰው ማለት ነው፤ ስለዚህ መልካም ሰውን የሚጎዳችሁን ነገር ብትጠይቁት በትክክል ይከልካለቸኋል፤ ምክንያቱም የጠየቃችሁት ነገር ለእናንተ ጥሩ ስላልሆነ ነው። ይህንን ሁሉ ነገር ለምን አነሳቹ ልትሉ ትችላላቹ፤ ለእርሱም መልስ ከዚህ በኋላ ተከታተሉ። " ልያም። እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።" (ኦሪት ዘፍጥረት 30:20) " ሚካም። ሌዋዊ ካህን ስለ ሆነልኝ እግዚአብሔር መልካም እንዲሠራልኝ አሁን አውቃለሁ አለ። " (መጽሐፈ መሳፍንት 17:13) " ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤" (መዝሙረ ዳዊት 116:7) " እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። " (ትንቢተ ናሆም 1:7) ስለዚህ ከነዚህ ጥቅሶች የምትረዱት እግዝያብሄር ደግ አይደለም መልካም ነው እንጂ፤ ለዚያ ነው የምትጠይቁት ሁሉ የማይሰጣቹ ፤ ምክንያቱም እርሱ መልካም ነውና የማይጠቅማችሁን ይሸሽገዋል፤ የሚጠቅማችሁን ደግሞ ይሰጣችኋል። ስለዚህ እግዝያብሄር መልካም መሆኑን የምታምኑ ከሆነ አገኘሁ ብላቹ ለምትሉት ነገር ብቻ ሳይሆን አጣሁ ለምትሉት ነገርም አመስግኑ፤ ለምን እውነት እግዝያብሄር መልካም መሆናችሁን ካመናቹ አጣን ያላችሁት ነገር በመጀመሪያ ነገር ለእናንተሰየማይጠቅም ስለሆነ ነውና እግዝያብሄር የወሰደው። @jesusfreakmotivations
2019/05/16 17:22
📖Sunday Motivation📖 እግዝያብሄር በህይወታቹ የጀመረው ነገር አለ። አንዳንዶቻቹ ብዙም በኔ ህይወት እየሰራ አይደለም ብላቹ የምታስቡ እንዳላቹ አውቃለሁ፤ ግን በዚህም መንገድ እርሱ ነገር ልክ እንዳልሆነ ልነግራቹ እፈልጋለሁ። እግዝያብሄር እናንተ ላይ የጀመረው ነገር በእናንተ ጥረት የተገኘም አይደለም፤ በእናንተ ጥረት የሚቀጥልም፤ በእናንተ ጥረት እስከፍፃሜ የሚደርስም አይደለም። ስለዚህ በእናንተ ህይወት ውስጥ እየሰራ ያለው ነገር ካላወቃቹ፤ ሳይሰስት ጥበብን ለሚሰጠው ለእግዝያብሄር ማስተዋል እንድትችሉ እና እናንተ ላይ የጀመረውን ስራ እስከፍፃሜ የሚያደርስ አምላክ ከዚህ በላይ ፀጋን እንዲያበዛላቹ የልባችሁ ፍላጎት ካለ፤ ከፀሎት ልመናቹ ጋር ወደ ጌታ አቅርባችሁት ክርስቶስ በህይወታቹ ሊሰራው ያለውን መንፈሳዊ አይናቹ እንዲያይ ለእርሱ አብዝታቹ ፀልዩ። @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/05/12 11:20
📖Motivation of the Day📖 (ወደ ዕብራውያን ምዕ. 12) ---------- 1-2፤ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። 3፤ በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ። Lift yourself up with this word The word has power And all you need to know is that God is with you and he will give you the grace you need to overcome the world. Just pray 🙇🙇 @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/05/10 16:45
📖Motivation Of the Day📖 🤔ላገልግል ወይ?🤔 ብዙዎቻቹ በእግዝያብሄር መንግስት ቦታችሁን ማግኘት ያቃታቹ እንደሆናቹ እገምታለሁ። ምንም አይነት ነገር መስራት አልችልም፤ ምንድነው የተሰጠኝ ፀጋዬ ብላቹ ልትጠይቁ ትችላላቹ። ከጥቂት ቀናት በፊት አንዲች ሴት በመንግስቱ ያላትን ስራ ምን እንደሆነ ማወቅ አቅቷት ግን እግዝያብሄርን ለማገልገል ካላት ጉጉት የተነሳ በብዙ ስራዎች ውስጥ ገብታ እያቃታት ማቆም ሲበዛባት ያኔ እግዝያብሄር በቃ እኔ እንዳገለግለው አይፈልግም ማለት ነው ብላ በስራ ውስጥ የነበራትን እንቅስቃሴ አቆመቹ። ይህ ትክክል ናት ብዬ ብናገር ውሸት ይሆንብኛል። ማንም ሰው በመንግስት ውስጥ ስራ ይሰጠዋል፤ ማንኛውም ሰው እግዝያብሄርን ማገልገል እንደሚፈልገው ሁሉ እግዝያብሄርም ያ ሰው ቢያገለግለው ይወዳል፤ ነገር ግን የትኛው ይቀድማል ነው ጥያቄው! አንድ ሰው ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት ከእግዝያብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ማጥበቅ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ። አገልግሎት ለእግዝያብሄር መስዋዕት ነው፤ ነገር ግን መፅሀፍቅዱሳችንም እንደሚናገረው መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል፤ ስለዚህ እውነት ከእግዝያብሄር ጋር ያለን የግል ግንኙነትና የመታዘዝ ህይወታችን የጠነከረ ነው ብለን ካሰብን ለማገልገል ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን በእርሱ ፈቃድ ስለሆነ አገልግሎት የሚሳካው ፤ ፈቃዱን ለልጆቹ ማሳወቅ የሚፈልግ አምላክ ስለሆነ ያለን፤ አገልግሎታችን እንዲሳካ ከእርሱ ያለንን ህይወት በመጀመሪያ እንገንባ ባይ ነን! 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/05/05 20:59
MY PEACE ☮☮ Peace, the thing we all look for But it seems so hard to find that door Panic seems to come so easy to us It is so simple to rather make a fuss. Many people have many theories On how to find their peace They run around here and there For them, I have a secret I should share. ☮☮ Some believe peace comes with money So they get rich until they're filthy But then worrying always follows What will happen if my export blows? You think you can buy peace? Newsflash, all your plans will cease I got no money but I'm peaceful I got jesus, he is free and full. ☮☮ Others go and get insurance Thought "If I crash my car, I'll have a chance" But still drive with absolute fear Knowing no help will do if their vessels tear. I got no insurance and never will I have a protection that keeps me still I dont worry that I might crash Jesus is not an insurance on a paper stash. ☮☮ I dont care what people say Jesus is the one that keeps me at bay Eventhough the lions roar around me I'm sure not one will ever touch me. What more could I need? My peace is not just a seed It is like the trees filling the jungle Wide and deep, I will never stumble. ☮☮ For all, I really want to show My peace is like a clear river flow A spring from high up in the sky Trust me, my peace will never dry. Stop hearing what others say If they tell you there is another way Jesus is our shephard, we are his sheep He is the peace that never sleeps. ☮☮ The thing you gave me money cant buy Telling the the world I'll never be shy My faith in you made me peacefull For all that you are I am thankful I love you God for this peace I feel safe because you are fierce No matter what I face you're by my side I'm just in the backseat enjoying the ride ☮☮ 🔊🔊#JFMPoems @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪💪
2019/05/01 00:49
እምነት ማለት ይሄ ነው! አንድ ታሪክ ትላንት ሰምቼ እንዴት ደስ እንዳለኝ። በድሮ ጊዜ አንድች አሮጊት ነበረች ብለው ታሪኩን ጀመሩልኝ፤ ይህች አሮጊት በድህነቷ በጣም የወረደች በቀን ውስጥ ለምግብ ራሱ የማታገኝ ባንዲች ደሳሳ አንዲች ክፍል የቀበሌ ቤት ውስጥ የምትኖር ናት። ይህች ሴትዮ ምንም ያህል በድህነቷ ብትጣወቅም በአንድ ተጨማሪ ነገር ታዋቂ ናት፤ እግዝያብሄርን በማመስገን። በሰፈር ውስጥ፤ በመንገድ ላይ፤ በገብያ ውስጥ በሁሉም ስፍራ ሀገር እየሰማት የእግዝያብሄርን ክብር መናገር የዘወትር ስራዋ ነው። ከዚያም አንድ ቀን የሰፈሩን ፀጥታ እየረበሸች ነው በማለት ያለምክንያት ከሚጠሏት ጎረቤቶቿ የቀበሌ ክስ ይደርስባታል። የቀበሌ ሰዎች እቤቷ ድረስ መተው ይህ በየቦታው አየዞረች የእየሱስን ስም እየጠራች የምትጮኸውን ነገር እንድታቆም ነገሯት፤ እርሷ ደግሞ ምን ያህል ውስጣቸው ያለውን ሴጣን እየረበሸ መሆኑን ስታውቅ ባሰባት። ከዚያ አንድ ቀን ካዋረድናት ዝም ትላለች ብለው የቀበሌ ባለስልጣኖቹ 50ኪሎ ነጭ ጤፍ አስፈጭተው በሯ ላይ አስቀመጡላት። እርሷም እንደለመደባት ወደ ውጪ ሄዳ የጌታን ክብር ልትናገር ስትወጣ በሯ ላይ ጤፉን ስታየው በጩኸት ቀወጠችው። ከዚያ ከወትሮው ለየት ስላለባቸው የሰፈር ሰው በሙሉ ወተው ያዩዋት ጀመሩ፤ "ምን መጣ?" ብለው ጎረቤቶቿ ጠየቋት እርሷም "እዩ እግዝያብሄር ያደረገልኝን!" ብላ ወደ ጤፉ እያጠቆመች በደስታ አሳየቻቸው። ከዚያም ከቀበሌ ሰዎቹ አንዳቸው ከተሰበሰበው ህዝብ ብቅ አለና "እግዝያብሄር አይደለም ጤፉን የሰጠንሽ እኛ ነን!" ይላታል አሮጊቷም ሳቅ አለችና "እኮ እግዝያብሄር ይገዛል ሰይጣን ይሸከማል" ብላቸው አረፈችው። እንደዚህ አይነት እምነት ይስጠን አሜን?? 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/25 14:15
#worshiptheworld Let your life worship him not just your mouth አፋቹ ብቻ ሳይሆን ህይወታቹ ያምልከው 🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/21 14:15
(ኦሪት ዘዳግም ምዕ. 11) ---------- 1፤ እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፥ ሕጉንም ሥርዓቱንም ፍርዱንም ትእዛዙንም ሁልጊዜ ጠብቅ። 2፤ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ተግሣጽ፥ ታላቅነቱንም፥ የጸናችም እጁን፥ የተዘረጋውንም ክንዱን፥ 3፤ በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ሥራውን፥ 4፤ በተከተሉአችሁም ጊዜ በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ በግብፅ ጭፍራ በፈረሶቻቸውም በሰረገሎቻቸውም ያደረገውን፥ 5፤ ወደዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥ 6፤ በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ላላወቁትና ላላዩት ልጆቻችሁ አልነግራቸውምና እናንተ ዛሬ እወቁ። 7፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረጋትን ታላቂቱን ሥራ ሁሉ ዓይኖቻችሁ አይተዋል። 8፤9፤ እንግዲህ እንድትጠነክሩ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሻገሩባት ምድር እንድትገቡ እንድትወርሱአትም፥ እግዚአብሔርም ለእነርሱና ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ።
2019/04/18 23:34
🎙Motivation of the Day🎙 🙋አዲሱ ማንነቴ🙋 በህፃንነታቹ ገና ከእናታቹ ሆድ ስትወጡ እናታቹ ወይም አባታቹ ነበሩ ለእናንተ ማንነት ለመስጠት የሚችሉት፤ ማንም ሰው የመጀመሪያ ስሙን እርሱ እራሱ መርጦ ያወጣ ያለ አይመስለኝም። 🕴🕴 ስለዚህ እናንተ ስትወለዱ፤ በስጋ ሆናቹ ይህችን ምድር ስትቀላቀሉ፤ ምንም ያህል ከመወለዳቹ በፊት እንኳን ቢሆን ስማቹ የተወሰነው የተወለዳቹ ቀን ነው ወረቀት ላይ የሚሰፍርላቹ። 🕴🕴🕴 ይህንን ሁሉ ነገር ለመናገር የፈለኩት እናንተ ጌታን ከመቀበላቹ በፊት የነበራቹ ማንነት እናንተ መርጣችሁት ያገኛችሁት አይደለም። ከጌታ በፊት የነበራቹ ማንነት ገና በእናታቹ ማህፀን እየነበራቹ እንደወጣላቹ ስም፤ በትክክል ያልሰፈረ፤ በትክክል ያልተፃፈ፤ እውነት መታወቂያቹ ያልሆነ ነው። 🕴🕴🕴 በጌታ ስትመጡ ያኔ ማንነታቹ በእርሱ ይወሰናል። እውነት እናንተ በእየሱስ ክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ናቹ፤ 🕴🕴🕴🕴 " ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17) 🕴🕴🕴 ስለዚህ እውነት ድሮ የነበራችሁን ማንነት እርሱትና በአዲስ ማንነት ጌታን አገልግሉ፤ ምክንያቱም ከማይረባው ህይወት አውጥቶ ስለመረጣቹ ለእናንተ ክብር ነውና። 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/16 16:04
🎙Motivation Of the Day🎙 🔌Plug In🔌 Jesus used parellels and metaphors to explain different things in his time to make sure they understood what he was talking about.....so now the things this generations understands is technology so I am going to explain certain things with a technology. Imagine you are your phone that you have on you right now. 😂U have a creator.....as the phone has a creator( apple, samsung, tecno etc) 😂U were created with a purpose.....as the phone was created with a purpose( calling, internet etc). 😂U are beautifully n wonderfully made as the phones in ur hands right now......(the edges, the speakers, the color etc) 😂U have the ability to reach the entire world as you can call america from here and you can easily see whats going on there by your phone. 😂U are full of potential as you can do anything with your phone right now and as there are apps in your phone u have never used before, there are many things inside you that you havent even started to experience. 😂U were chosen......as we chose the phones we have right now God chose us 😂U were bought with a price as no phones in your hands right now are free. 😂 But always remember for you to experience what ever your phone can do, it has to be connected with a power source for it to be charged.....as you have to have holyspirit as your power source to experience everything that you are purposed to do. 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/15 13:58
#IloveGod #IloveGod #IloveGod ..... 🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/15 00:57
🎙our chains are gone 🎙Our debt is paid 🎙The cross has overthrown the grave #Hillsongs 🔊#JFMVidoes @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/13 19:05
🤔Full life Or Fool Life??🤔 All of us got a different version of definition for beauty, different thinking towards places and races and religion...what makes us all the same is that none of us got to choose which race we want to be born in, what place we want to live in, what kind of color and posture and height we want to have except for those who undergo plastic surgery and work really hard in gyms😆😆 with it's own consequences but we all have the same definition of success if we think like a normal person and that is to be able to help others through our life, to make our parents proud, to be good parents ourselves and above all to make God proud. 💪💪💪 If this is success for you the most important thing you need to work on is your mind and heart because out of them comes hardwork, motivation, courage, confidence and strength. 📖📖📖 Also that the soul be without knowledge is not good. (proverbs 19: 2) 📖📖📖 Feed your soul with good knowledge so that you can live full life not fool life! Because it's the fool who spends his/her time thinking about miscellaneous things. It's the wise who sees life beyond just physical. 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/09 23:01
📖 Motivation Of the Day 📖 👂ምስጢር ልንገራቹ?👂 በተጣርንበት መንገድ መራመድ ብዙ ሰዎች እንፈራለን፤ ብዙዎች አገልጋይ ፈተና ይበዛበታል ብለው በጌታ ቤት ያላቸውን ስራ ከመስራት ወደ ኋላ ለመቅረት ገራሚ ሰበብ ሆኖላችኋል። እውነት እናንተ አገልጋይ አይደሉም ብሎ ጠላት ላንተ ያለውን ሀሳብ ችል የሚለው ከመሰላቹ እውነት በሃሳባቹ ብቻ አጠውልጎ ይዛችኋል ማለት ነው። 🔷🔶🔷 ጠላት እየሱስ ክርስቶስ በህይወታቹ ያሰበውን ነገር እንዳይሳካ ቀን ከሌሊት ያለእረፍት እንደሚሰራ እወቁ፤ በቤቱ አገልጋይ ሆናቹ አልሆናቹ፤ ፈተናን ፈርታቹ ተደበቃቹ አልተደበቃቹ እርሱ እንደሆነ ጌታ ካሰበላቹ ነገር ማዘግየቱን አያቆምም። 🔷🔶🔷 ማዘግየት ለምን አልሽ ብትሉኝ ማቆም እንደማይችል ጠንቅቆ ስለሚያቀው ነው። ጠላት ተሸናፊ እንደሆነ ስለሚያቅ በተቻለው መጠን ባለው በሌለው አቅም እናንተን ለማዘግየት ነው የሚጥረው፤ በብዙዎቻችን ህይወት ውስጥ ደግሞ የማዘግየቱ ስራ እየተሳካለት ያለው እርሱ አሸናፊዎች መሆናችንን እኛ ከምናውቀው በላይ ስለሚያውቅ። 🔷🔶🔷 ኧረ ነውር ነው፤ በአዳነን በእየሱስ ክርስቶስ ያገኘነውን አሸናፊነት እርሱ አውቆ እኛ ካልገባን፤ ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ነውር አለ? 🔷🔶🔷 ኧረ እንነሳ!!!! በቃ ለማለት የሚያችለንን አቅም ጌታ እንዲሰጠን፤ በብዙ ነገሮቻችን ብንደክምም ጠላት አውቆት እኛ የረሳነውን ነገር እናስታውስ " በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37) " ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13) 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/05 22:17
📖Motivation Of the Day📖 😣ደከማቹ?😥 እያንዶቻቹ በብዙ አይነት ድካም ውስጥ የምታልፉ ናቹ። አንድ ሰው ምንም ድካም የለብኝም ቢል ወይ ድካም አለብኝ ብሎ የማያምን ነው ወይም ደካማ መሆን የክብር ጉዳይ ሆኖበት እየዋሸ ነው የሚሆነው። 🔷🔶🔷 ድካም ምንድነው? ድካም ማለት በማንኛውም ነገር ላይ የነበረን የስራ ብቃት በሆነ መጠን ሲቀንስ፤ በአንድ ነገር ላይ መተግበር እንዳለብን መጠን ወይም አይነት መተግበር ሲያቅተን ነው። 🔷🔶🔷 ለክርስቲያኖች ለኛ ደግሞ በብዙ ድካሞች ውስጥ ልንኖር እንችላለን። ✅በመንፈሳዊ ድክመት ✅በስጋዊ ድክመት ✅በግንኙነት ድክመት በብዙ ድካሞች ልንገኝ እንችላለን። 🔷🔶🔷 እኔም ሰሞኑን በብዙ አይነት ድካም ውስጥ ሳልፍ መፅሀፌን ከፈት ሳደርግ አንድ ቃል ጌታ አስቀመጠልኝ 📖📖📖 " ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:10) ይህ በአለማዊና በማያምን ሰው ሲነበብ በጣም የሚጣረዝ ሀሳብ ነው፤ ግን ለኛ አቅም አጣን ካልንበት ቦታ ሊያነሳን ሃይል ያለው ቃል ነው። 🙏🙏 በድካም ውስጥ ሀይል የሚሰጥ ክርስቶስ ነው፤ እውነት ያላችሁበት ድካም ላያቹ ላይ በታከከ ቁጥር እየሞረዳቹ ሊያሾላቹ ነውና፤ በውስጣቹ አለበለዚያ የማይመጣውን እልህ ሊጨምር ፤ ለወደፊት የሚገጥማችሁን ነገሮች የምታሸንፉበትን አቅም ሊሆናቹ፤ ወደፊት በተመሳሳይ ነገር ውስጥ እያለፈ ላለ ሰው ተስፋ እንድትሆኑ የሚያደርግ ነውና በድካም ውስጥ ሀይለኞች ናቹ። ስለዚህ ድካማቹ 💪አያዝላቹ ያጠንክራቹ እንጂ 💪አያስለቻቹ እልህ ያዝይዛቹ እንጂ 💪ተስፋ አያስቆርጣቹ ያስጨክናቹ እንጂ ለምን?? በእውነት እግዝያብሄርን የምታምኑ ከሆነ በድካማቹ ሀይለኞች ስለሆናቹ። 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/04/03 21:29
#bethelmusic #JFMWorship #worshiptheking #jesus #singalong @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/03/31 23:13
🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/03/25 23:48
📖Daily Bible Verse📖 🗣የእግዝያብሄር መንፈስ በኛ ውስጥ ምን ያረጋል??🤔 (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 8) ---------- 9፤ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። 10፤ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው። 11፤ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል። 12፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም። 13፤ እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። 14፤ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። 15፤ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። 16፤ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። 🔊🔊#JFMDailyBibleVerses @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/24 11:32
📖📖Daily Bible Verse📖📖 (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ. 4) ---------- 4፤ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። 5፤ ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። 6፤ ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። 7፤ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። 8፤ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ 9፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። 🔊🔊#JFMDailyBibleVerse @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/03/23 12:10
📖Motivations of the Day📖 🗣ያለፈውን መተው🗣 ብዙዎቻቹ ባለፈው ነገር ሀዘን ወይም ፀፀት ላይ ትሆናላቹ፤ ወይም እኔም ሆነ ሌላ ሰው ሊገልፀው የማይቻለው ነገር ሊሰማቹ ይችላል። ግን ማንኛውም ነገር ቢሆን አንድ የሚያደርጏቸው ሁለት ባህሪዎች አላቸው። 🔷🔶🔷 1, ያለፉት ነገሮች መቀየር አይችሉም ምንም አይነት ስሜት ቢሰማን አንድ ነገር ማወቅ ያለብን፤ ምንም ያህል ነገሮችን የምንችል ቢመስለንም ምንም ያህል እውቀትና ገንዘብ ቢኖረን ሁላችንም የማንችለው ነገር ትላንትናችንን መቀየር ነው። 2, ወደፊት እንዳንሄድ አሳስሮ ይይዘናል " ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:13) 🔷🔶🔷 መፅሀፋችንም እንደሚነግረን እግዝያብሄር ከፊታችን ያስቀመጠልንን ለመያዝ የኋላችንን መተው መማር አለብን። 🔷🔶🔷 እንደአፍ ቀላል በሆነ እያላቹ ነው አይደል?? መልሱም ይህ እየሱስ ክርስቶስ በአብ ፊት ለናንተ ማልዶ ይቅር ካላቹ፤ መቼም ጌታን እንደበደልነው ራሳችንን አልበደልንምና ራሳችንን ይቅር ማለት መማር አለብን። እየሱስ ክርስቶስ በኔ ካላቹ ኩነኔ የለባችሁም ያለንን እያሰብን እርሱ አሁን እንደሚያየን ራሳችንን የምናይበትን አይን እንዲከፍትልን በፊቱ እንንበርከክ። ከዚያ በኋላ ወደዳችሁም ጠላችሁም ነገሮች ሲቀየሩ ታያላቹ። ፀሎት 🙏ፀሎት🙏 ፀሎት ስለዚህ ፅሁፍ አስተያየት ካላቹ የሚገናኝ ጥቅስ መፃፍ ከፈለጋቹ 👇👇👇👇👇👇 ከታች commemt ይጠቀሙ 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/03/22 15:30
🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/19 20:43
📖Bible Verse Of the Day📖 (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 1) ---------- 16፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። 17፤ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። 18፤ እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ 🔊🔊#JFMDailyBibleVerses @jesusfreakmotivations
2019/03/19 20:42
📖Motivation Of the Day📖 ⛪ቤተክርስቲያን ምን ይሆን??⛪ ቤተክርስቲያን በአጭሩ የእግዝያብሄር ቤት ናት። በአለም ሳለች የአለም ብርሃን፤ እግዝያብሄር በእርሷ ምክንያት ለምድር ምህረትን ያበዛ፤ ለአለም የምትማፀን ናት። ማንኛውም ሰው ወደ እርሷ ሲመጣ ችግሩ የሚቀልበት፤ ፀሎት የሚበረታበት ፤ ህብረት የሚጠነክርበት፤ ፍቅር የሚማርበት፤ ሰው የሚምርበት ፤ በዚህች አለም ውስጥ ያለውን መከራ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን የሚረሳበት ቦታ ነው። ⛪⛪ በመፅሀፍቅዱስ ውስጥ በብዙ መልኩ ተገልፃለች 1 የክርስቶስ ሙላት (ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ. 1) ---------- 22፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። 23፤ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት። 2 የፀሎት ቤት " ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ። " (ትንቢተ ኢሳይያስ 56:7) ግን እነዚህን ነገሮች ካነበብኩ በኋላ አሁን እያንዳንዳችን የምናገለግልበት ቤተክርስቲያን እውነት መፅሀፍቅዱስ ላይ የተጠቀሰችው አይነት ናት? ለኔ አይደለም ለማለት አልሸማቀቅም! እናንተስ? ሁሉንም ባልል ግን በአብዛኛው ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ህልውና ጠፍቷል፤ በወንድሞች ህብረት መካከል እባብ ገብቶ እንደፈለገ ሲጫወት በቃህ የሚለው አቷል፤ በህብረት ውስጥ ከመደጋገፍ ይልቅ ለጠፋው ጥፋት ሰበብ መፈለግ ቀሏል፤ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ በርትቷል፤ መተሳሰብ ተሸርሽሯል፤ ሰው መምጣት ከሚፈልግበት በላይ ለመቅረት የሚሰጠው ሰበብ በዝቷል። ታዲያ ያቺ መፅሀፍቅዱስ ላይ የተፃፈቹ ቤተክርስቲያን የት ሄደችብን?? ክርስቶስ ለቤተ መቅደሱ የነበረው ቅንአት ከኛ ውስጥ ወዴት ጠፋ?? ⛪⛪⛪ የፀሎት ቤት ያለውን በብዙ ቦታ ላይ የሌቦችና የወንበዴዎች መጠራቀሚያ እንደሆነ ክርስቶስ በ3 ወንጌሎች ደጋግሞ ነግሮናል! " ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።" (የማቴዎስ ወንጌል 21:13) " አስተማራቸውም። ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።" (የማርቆስ ወንጌል 11:17) " እርሱም። ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 19:46) ስለዚህ የዛሬ መልእክቴ አንዳንዶቻችን የቤተክርስቲያንን ምንነት ክብር እንረዳ፤ የክርስቶስ ሙላቱ ናት እና ይህ አገላለፅ ምን ያህል ንፁህ መሆን እንዳለባት ይነግረናል፤ እርሱ በሁሉ ነገር ፃድቅና ንፁህ ነውና። ⛪⛪⛪ አሁን ከምታነቡት አንዳንዶቻቹ ለቤተክርስቲያን ህልውና መጥፋት አስተዋፅኦ ላይኖራቹ ይችላል፤ መታቹ በሙሉ መንፈስ የምታመልኩ፤ የእግዝያብሄርን ህልውና መገኘት የምታከብሩ ብዙዎች ናቹ፤ ግን የምታገለግለሉበት ቤተክርስቲያን በእግጠኝነት የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር ይኖረዋል፤ ስለዚህ "እኔ አንድ ሰው ነኝ በምን ይህን የሚያክል ችግር ልቀይር እችላለሁ?"በማለት እጅን አጣጥፎ መቀመጥ በራሱ ጥፋት እንደሆነ ማወቅ አለባቹ። ⛪⛪⛪ ስለዚህ አቅም እንደሌለው ጥግ ይዛቹ መቀመጥ ይብቃ! በፀሎት፤ በአካባቢያቹ ካሉት እራሱ በመጀመር ቤተክርስቲያንን ወደ ቀድሞ ክብሯ እንመልሳት የዛሬው መልእክት ነው። ⛪⛪⛪ እንደ ስሟ የአለም ብርሃን እንድትሆን በፀሎት ለጌታችን እንማልድ፤ ለኛም ሆነ ለመሪዎች አቅም እና መነቃቃት የሚገኘው በእርሱ ስለሆነ! 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/16 12:59
📖Motivations Of the Day📖 🤔ለመድነው መሰለኝ🤔 አንድ ስብከት ላይ የሰማሁትን ነገር ትንሽ ነገር ላካፍላቹ እፈልጋለሁ። የሆነ ቀን ዝምብላቹ የጌታን በረከት ብዛት አስባችሁት ታውቃላቹ?? እውነት ምን ያህል እንደሆነ አሰላስላችሁት ታውቃላቹ?? 🙏🙏🙏 እውነት እናውራ ከተባለ ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ነገሮች ከማስተዋል አእምሮአችን የዘገየ ይመስለኛል። አሁን ቁጭ ብለን ልባችን መምታቱ ፤ ሳንባችን መተንፈሱ ፤ እግራችን መዝለሉ፤ እጃችን ማጨብጨቡ፤ አፋችን ለእርሱ ምስጋና ማቅረቡ፤ አእምሮዋችን በትክክል ማሰቡ ፤ ይህ ሁሉ እውነት የእግዝያብሄር በረከት ነው ብላቹ አመስግናቹ ታውቃላቹ?? 🙏🙏🙏 የድሮ የኢትዮጲያ መንግስት በእኛ ሃይማኖት ላይ የነበራቸው ጥላቻና መቅረቱ፤ በፈለግንበት ጊዜ በፈለግንበት ቦታ እግዝያብሄርን ማምለክ መቻላችን፤ "እየሱስ ያድናል" ብለን ስንናገር የማንታሰርበት ዘመን መምጣቱ፤ በፈለግንበት ቦታና ጊዜ መፅሀፍቅድሳችንን በማንኛውም ቋንቋ እና ትርጉም መግዛት መቻላችን ይሄ የእግዝያብሄር በረከት እና የበዛ ፀጋው ካልሆነ ከሌላ ቦታ ከየት እንደመጣ መገመትም አልፈልግም። 🙏🙏🙏 ነገርግን ይህ ሁሉ ነገር ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ፤ ግማሾቻችን ጌታን እራሱ ሳንቀበል በፊት የነበሩ ነገሮች ስለሆኑ ፤ የሆነ ሽታ ሲረብሻቹ ቆይቶ ከዚያ እንደምትለምዱት፤ ናላችንን ሲያዞር የነበረውን ድምፅ ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደምንለምደው ፤ እንደዚያው የጌታ እጅ የሚታዩበትን ትንሽ የሚመስሉ ነገሮችን ለመድናቸው መሰለኝ። ስለዚህ በሆነ መጠን ለነሱ ነገሮች የምናመሰግንበት ጊዜ የቀነሰ ይመስለኛል። 🙏🙏 ስለዚህ የእለቱ መልዕክት እግዝያብሄርን ትንሽ ለሚመስሉ ነገሮች አመስግኑት ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግልን ከብዙ ቸርነቱ ነው እንጂ እኛ ተገብቶን ግዴታ ስለሆነበት አይደለም። 🙏🙏 " መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ። እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው። " (መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 5:13) 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/14 14:42
የለም እንዳንተ
AudioTrim
Worship with us 👆👆👆👆👆👆👆👆👆 Jimma University Fellowship Live Worship Singer: Gelu 🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻 Sing Along🙏 🔊🔊JFMSongs @jesusfreakmotivations
2019/03/13 15:45
📖Motivation Of the Day📖 🙏የጣኦት መልክ መቀየር🙇 በአሁን ጊዜ በተለይ በኢትዮጲያ ሀገር ቢሆንም በሌሎች ሃገራት ድሮ በግሪክና በባቢሎን ዘመን የነበሩ የጣኦት ብዛት በአሁን ሰአት ቀንሰዋል ብለን ለመናገር ብዞዎቻችን እንደፍር ይሆናል፤ ለኔ ግን ትንሽ ይከብደኛል። 🤔🤔 እውነት ሊሆን ይችላል፤ አዎ በጥንት ጊዜ ትንፋሽ የሌላቸውን ምስል አቁመን ህይወታችንን ሰተን እስከ ሞት ድረስ ታዘን በቀን ስድስቴ ደም እየረጨን አንሰግድ ይሆናል። በዚያ ከሆነ ጣኦት አምላኪ አይደለሁም ብለን ራሳችንን የምንገመግመው ሲጀመር የጣኦት ትርጉም አልገባንም ማለት ነው። 🤔🤔 ጣኦት ማለት በኢንግሊዘኛ ዲክሽነሪዎች ሲተረጎም ማንኛውም በህይወታችን ትልቅ ቦታ የያዘ ነገር ነው ተብሎ ይነገራል። ጣኦት ማለት እርሱ ሲኖር ህይወታቹ ሙሉ እንዲመስል የሚያደርጋቹ ግን እርሱን በቀን አንዴ እራሱ ሳትገናኙ ስትውሉ ያቺ ቀን እስክታልቅ እንዲጨንቃቹ የሚያደርግ ነው ብዬ አስባለሁ። 🤔🤔 ስለዚህ ይህን ያህል ስለጣኦት ካልኳቹ ወደ ራሳችን ህይወት መለስ ብለን ህይወታችን በምን ወይም በማን እንደሚተመን እንገምግም ባይ ነኝ። እውነት እኛ ክርስቲያኖች ሆነን እንደተጣርንበት ጥሪ መጠን ነው እየኖርን ያለነው በለን እራሳችንን እንጠይቅ ባይ ነኝ። 🤔🤔🤔 ቀናችን በምን እያለፈ ነው፤ ግማሾቻችን የፊልም ጣኦት አጠናውቶን የቲቪ መስኮት ሱሰኞች ሆነን ለእግዝያብሄር ቃል የምንሰጠው ጊዜ ተመናምኖ ዜሮ ሊደርስ ምንም አልቀረም። ግማሾቻችን የማይሆን ግንኙነቶች ውስጥ ገብተን ያንን ሰው ማስደሰት ለኛ ጣኦት ሆኖብን እግዝያብሄርን ከማስደሰት ይልቅ እነርሱን ማስደሰት ሚዛን የሚደፋበን የሆንን ሰዎች ሞልተናል። አንዳንዶቻችን ደግሞ ገንዘብ ጣኦት ከመሆኑ የተነሳ ራሳችንን ክርስቲያን ነን ብለን ለማሳመን ከምንንበረከክባት ትንሽ ደቂቃ ያህንን ጣኦት እግዝያብሄር ከሰማይ እንዲያወርድልን የምንፀልይበት ሰአት በዝቶ ለምስጋና ጊዜ አተን ጉልበታችንን አራግፈን እንነሳለን። ይህን ሁሉ ምሳሌ ጠቅሼ በእንደዚህና በአንዱ አይነት ዘመናዊ የጣኦት አምልኮ ውስጥ ያላቹ አንድ ጥቅስ ላካፍላቹ 🤔🤔🤔 " በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥ " (ኦሪት ዘዳግም 32:16) ይህንን ጥቅስ ሳነብ አንድ ነገር ብልጭ አለብኝ፤ እግዝያብሄር ሰው ሲጠላኝ እኔን የወደደ፤ ለእኔ ብሎ በልጁ ላይ እስከሞት የጨከነ፤ በእውነት እርሱ ከወደደኝ በላይ የወደደኝ ሰው አለ ብለን እስከማናስብ ድረስ ወረት በሌለው ፍቅሩ የወደደን ታዲያ ይህን አምላክ ቃስቀናነው ታዲያ እዚች ምድር ላይ አላማችን ምንድነው። 🤔🤔🤔🤔 ከዚያ የሚገርመኝ ምንም ያህል በማቴዎስ ወንጌል እርሱንና የመንግስቱን ፅድቅ አስቀድመን ብንፈልግ ሌላው ነገር እንደሚጨመርልን ተነግሮን፤ ሁልጊዜ አንድ እርምጃ ከኛ የሚቀድመውን እንደ ንፋስ ሆኖ ልንይዘው የማንችለውን ነገር እያባረንን ጌታ ሆይ ለምን ተውከኝ ብለን እርሱን እናማርራለን። ለእርሱም መልስ አለው 🤔🤔🤔 (ኦሪት ዘዳግም ምዕ. 32) ---------- 20፤ እርሱም አለ። ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፥ ያልታመኑም ልጆች ናቸው። 21፤ አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ ስለዚህ ለማይሳኩት ነገሮች እግዝያብሄርን ማማረር ትተን የራሳችንን ህይወት ዞር ብለን እንመልከት እላለሁ። የሰማይ አባታችሁን አታስቀኑት፤ ህይወታችሁን በደሙ ስለገዛ እያንዳንዱ ትንፋሻቹ የእርሱ ንብረት እንደሆነ መጠን ስገዱለት። 🙇🙇🙇🙇🙇 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/03/12 22:24
🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/12 22:20
📖Motivations Of the Day📖 🗣🗣የእግዝያብሄር ቃል🗣🗣 አንድ ቀን አንድ ሰባኪ የሆነ ነገር ሲናገር ሰምቼ ከጭንቅላቴ አልወጣም አለኝ። ሰባኪው ከስብከቱ መሃል ተነስቶ ስለ መፅሀፍ ቅዱስ የአለም ቢዝነስ ማውራት ጀመረ። እኔ ደግሞ ይሰብክ ከነበረው ነገር ጋር ሊገናኝልኝ ስላልቻለ በአትኩሮት መስማቴን ቀጠልኩ፤የዛኔ አንድ እውቀት ቀሰምኩ። 🔶🔷🔶🔷 ምን ?? ማለት ጥሩ። አለም ላይ በመጀመሪያ ደረጃ የግዢ ብዛት ያለው መፅሀፍ ቅዱስ ነው። እስካሁን በአለማችን አንደኛ የተባሉ የታሪክና የልብ- ወለድ መፅሀፎች እንደ መፅሀፍቅዱስ በብዛት አልተሸጠም። ለእርሱ አመስግኜ ሳልጨርስ ሰባኪው መናገሩን እንዲህ ብሎ ቀጠለልን፤ በብዙ ጊዜያት በተደረጉ ጥናቶች ደግሞ ታትሞ በደንብ ያልተነበበ መፅሀፍ እንደ መፅሀፍቅዱስ እንደሌለ ነገረን። ሁለቱ ነገሮች አይጣረዙም እንዴ? ስለዚህ ይህንን ነገር ለመፃፍ የተነሳሁት መፅሀፍቅድስ ገዢ ሆነን ለማንበቡ ጊዜ ላጣን ሰዎች ነን። መፅሀፍቅድስ ማለት የእግዝያብሄር ቃል፣ተስፋ ፣ ማንነት የተፃፈበት፤ ለክርስትና ዋና ነገሮች ያሉበት እራሱ በራሱ ለክርስትና ዋነኛና መሰረታዊ መሰረት የሆነ መፅሀፍ ነው። 🔷🔶🔷🔶 መፅሀፍቅዱስ ማለት የዳንበት ወንጌል የተፃፈበት፤ እለት እለት የሚያስፈልገን ምክሮች የሰፈረበት፤ እና የክርስትና ህይወትን የሚያጣፍጡ እግዝያብሄር ከእኛ ጋር የገባው ኪዳንና የሰጠን ተስፋ የተቀረፀበት መፅሀፍ ነው። 🔷🔶🔷🔶 መፅሀፍቅዱስ በአጭሩ የእግዝያብሄር ቃል እውቀት የተቀመጠበት ነው። ከእግዝያብሄር ቃል የሚገርመኝ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ግን ጥቂቱን ላካፍላቹ። 🔷🔶🔷🔶 በዚች ምድር እያለን ሴይጣን እምነታችንን ሊያሸረሽርና ካለንበት ህይወት ወደኋላ ሊመልሰን የማይሞክረው ነገር የለም፤ የእግዝያብሄር ቃል ደግሞ የእርሱን ሃይል የምንዋጋበትና ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የምንለወጥበትና ሴይጣንን የምናስፈራራበትና የምናሸንፍበት ሰይፋችን የእግዝያብሄር ቃል ነው። 🔷🔶🔷🔶 " የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:17) ሌላ ከእግዝያብሄር ቃል የሚገርመኝ ነገር ምንም ያህል ከዘመናት በፊት ቢፃፍም በአሁን ዘመን ላሉ ሰዎች ዛሬ የተፃፈ ያህል የሚያናግረን መሆኑ፤ ለእያንዳንዱ ሰው ለየራሱ የሚሆን መልእክት ከመናገሩ የተነሳ እኔ በበኩሌ ለእኔ ለግሌ የተፃፈልኝ እስኪመስለኝ ድረስ የደረስኩበት ቀናቶች አሉ። ዛሬ የተነበበ ቃል ነገ ሌላ ትርጉም ይዞ ነፍሳችንን ያስደስታል። 🔷🔶🔷🔶 " የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤" (ወደ ዕብራውያን 4:12) ስለዚህ ይህ የህይወት ቃል ቤታችን ገዝተን አስቀምጠን ለምን ብለን ህይወትን ያለጥበብ፣ ያለምክር፣ ያለተስፋ ደረቅ በሆነ የክርስትና ህይወት እንኖራለን፤ ስለዚህ የዛሬ መልእክቴ መፅሀፍቅድሳችሁን ከመደርደሪያ አንሱና ለክርስትና ህይወታቹ በእግዝያብሄር ቃል ህይወት ዝሩ። 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/10 14:25
#asterabebe #childrenofGod #adorable #blessed 🔊🔊#JFMVideos @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/09 21:29
የተለየ ነው
AudioTrim
🎼🎵🎶♩🎙🎤🎧🎷🎸 🏤Jimma University🏤 👬Fellowship👬 Live Worship Singer: Bethel Sing Along🙏 🔊🔊JFMSongs @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/08 09:42
#Hillsongs #Amazinggrace #Worship #Jesus 🔊🔊#JFMSongs @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/07 15:53
💪Motivation of the Day💪 🙋እንዴት ላመስግነው?🙋 ቁጭ ብዬ ሳስበው ጌታን ለስንቱ አመስግኜው ለስንቱ እንደምተወው ይጨንቀኛል። አንዱን በረከት አመስግኜ ሳልጨርስ ሌላው ባርኮቱ ፊቴ ድቅን ይላል። ከዚያ በራሴ አንድ ነገር ገባኝ፤ ሁሉን እየጠራው ተመስገን ማለት እልችልም። ለምን ? በሉኝ። 🙇🙇 ትላንት ወዲያ ከነውጥ ላወጣኝ ባመሰግነው የትላንትናው ሰላም ትዝ ይለኛል፤ ከዚያም ለእርሱ ተመስገን ብዬ ሳበቃ ቅድም በእርሱ ምህረት እንደሆነ ቆሜ የሄድኩት እገነዘባለሁ። ከዚያ አይ በቃ ለእርሱ አመስግኜ እጨርሳለሁ ብዬ ሳስብ "አሁን በማን ብርታትና ፀጋ መስሎሽ ነው ቁጭ ብለሽ ይህንን ፅሁፍ የምትፅፊው?" ይለኛል ውስጤ፤ የማመሰግንበትን ቃል እንዳወጣ ልቤ የሚመታው፤ የምትነፍሰው በእርሱ ምህረት እንደሆነ ሲገባኝ አመስግኜው ልጨርስ እንደማልችል ገባኝ። 🙇🙇 ዘላለማችንን፥ በህይወታችን የምታለፈዋን እያንዳንዷን ሰከንድ ተመስገን ብንለው አይበቃውም፤ የእርሱ ውለታ ማብቂያ የለውምና። 🙇🙇 ምንም የምጠራው ውለታ የለም ለማለት የምትደፍሩ ካላቹ ፤ትላንት በነውጥ ውስጥ ጌታ ያልደረሰላችሁ ቢመስላቹ እንኳን፤ ቅድም በሽታ መቷቹ መቆም አቅቷቹ ቢሆን እራሱ፤ እውነት ምንም የማመሰግንበት ነገር በህይወቴ አልሆነም ብላቹ ለመናገር የምትደፍሩ ካላቹ አንድ ነገር ልበላቹ 🙇🙇 ከሞተ ህይወታቹ አውጥቶ ወደ ዘላለም ህይወት መጥራቱ ከጨለማ አለም ወደሚደነቅ ብርሃን ማሻገሩ ከትልቅ ክብሩ ወርዶ ስለእናንተ መሞቱ 🤔🤔 ሌላ የምትጠሩት ውለታ ባይኖር እንኳ (እቺን ፅሁፍ ለማንበብ መቻላቹ በእርሱ ምህረት ቢሆንም) የመስቀል ውለታው ዘላለም አንበርክኮ በእያንዳንዷ እስትንፋስ ተመስገን የሚያስብል ስለሆነ ለማማረር ሰበብ ከመፈለግ በማለዳ በቀትር በሌሊት ምስጋናችሁን እያሰማቹ አስደስቱት 🙇🙇 👆የሚገባው አምላክ ነውና።👆 🔊🔊#JFMotivations @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪
2019/03/06 10:07
. መፈለግን እፈልጋለሁ ቤዛ መስፍን 🏫Jimma University🏫 🙏 fellowship🙏 🙎 Girl🙎 🕐-10:38min| 💾-10MB share💯share💯share @jesusfreakmotivations
2019/03/06 09:32
🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪
2019/03/05 13:56
ጆሮዬን ልብሳ
AudioTrim
Worship with us 👆👆👆👆👆👆👆👆👆 Jimma University Fellowship Live Worship Singer: Bethel 🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻 Sing Along🙏 🔊🔊JFMSongs @jesusfreakmotivations
2019/03/05 10:41
📖📖Today's Bible Study📖📖 🗣መንፈሳዊ ልባችን 🗣 " እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:14-15) በዚህ ቁጥር ላይ ከእግዝያብሄር እቃ ጦር ውስጥ ማተኮር የፈለኩት የፅድቅ ጥሩር ላይ ነው። የወታደር ጥሩር የሚጠብቀው የወታደሩን ህይወቱን የሚወስነውን የሰውነት ክፍሉን ነው፤ ልቡን። 🔷🔶🔷🔶 በህይወት እንድንኖር ልባችን መምታቱ ግድ ነው። ከልብ ምት ነው ሁሉ ለህይወት የሚያስፈልገን ሃይል የሚነሳው። ልባችን ለስጋዊ አካላችን የህይወት ምንጭ ነው። 🔷🔶🔷🔶 እንደዛው መንፈሳዊ ልባችን ደግሞ ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሃይል ምንጭ ነው። መንፈሳዊ ልባችንን መጠበቅ የምንችለው ደግሞ ፅድቅ ነው። ስለዚህ መንፈሳዊ ልባችንን ለመንከባከብ በቅድስና መኖር አለብን፤ ለእርሱ ደግሞ የመንፈስ ሃይል ስለሚያስፈልግ ተግተን ለጌታ መፀለይ አለብን። 🔶🔷🔶🔷 መንፈሳዊ ልባችን አራት ነገሮችን እንደሚያካትት አምናለሁ ✅ሃሳብ ስሜት✅ ✅አላማ/ግብ ንቁ እኛነታችን✅ ስለዚህ በቅድስና መኖር አቅቶን የፅድቅ ጥሩራችን በወረደ ጊዜ ሰይጣን እነዚህን ሁሉ ነገር ለመንካት እና ለመቀየር ይመቸዋል፤ ይህ ደግሞ ለኔ ለጅምላ ጭፍጨፋ መንገድ የከፈትንለት ይመስለኛል። 🤔🤔🤔 እናንተስ??? ☞በቅድስና ለመኖር ፍቃዳችሁን አሳውቁ ☞ለአለም እምቢ በሉ ☞ለሚጠፋት የሞት ሽታ ሁኑ ☞በአለም ብርሃናቹ ይብራ ☞በቅድስና ነሩ 🙏ፀልዩ🙇 🔊🔊JFMDailyBibleVerses @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
2019/03/02 18:47
📖📖Today's Bible Study📖📖 🗣እንፍቀድለት🗣 እግዝያብሄር በመፅሀፋ ውስጥ በብዙ ቦታ ላይ ቃል የገባልን ብዙ ነገሮች አሉ፤ ለኛ እነዚህ ነገሮችን ተስፋ የሚሰጡንና ክርስትናን የሚያጣፍጡልን ናቸው። አንድ ነገር የምናውቀው እርሱ መቼም እንደማይተወን ነው። እርሱ በህይወታችን ትልልቅ ነገሮችን ለማረግ ይፈልጋል፤ ነገር ግን እኛ በብዙ ወደ እኛ የሚመጣውን በረከት የምናዘገየው ይመስለኛል። ስለዚህ ይህንን ነገር ለመቀየርና ጌታ በህይወታችንን በየእለቱ የሚሰራውን ለማስተዋል ከፈለግን ሙሴ ቀይ ባህር ፊታቸው ሆኖ የሚያደርጉት ሲጠፋቸው ምን እንዳላቸው እናስታውስ። 🔷🔶🔷🔶 (ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 14) ---------- 13፤ ሙሴም ለሕዝቡ። አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። 14፤ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው። ስለዚህ ከዚህ ጥቅስ ላይ 4 ነገሮችን አድርጉ ይላቸዋል። እኛም ፊታችን ያለውን ቀይ ባህር ለመሻገር ማድረግ የሚገባን ስለሚመስለኝ ትንሽ ነገር ልበላቹ 💪💪💪 1. አትፍሩ ---------- ጢሞቴዎስ ላይ እንደሚናገር የፍርሃት መንፈስ አልተሰጠንም፤ ስለዚህ በጌታችን በመታመን በምንም መፍራት የለበንም። 💪💪💪 2. ቁሙ (በፅናት) ----------------- እየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ከአሸናፊዎች በላይ እንደሆንና እርሱ በሚሰጠን ሃይል ሁሉን እንደምንችል የነገረንን እያስታወስን በገባልን ቃል ላይ ፀንተን እንቁም፤ በፊታችን ያለውን ባህር አይተን ተስፋ አንቁረጥ፤ ከፍሎ የሚያሻግረን አምላክ ስላለን ፀንተን እንቁም። 💪💪💪 3. የእግዝያብሄርን ማዳን እዩ ----------------------------- ጌታችን በህይወታችን አሁን በዚች ሰአት ብዙ ነገር እያደረገ ነው፤ ነገር ግን አይታየንም። ለምን ቢባል ከተደረገልንና እየተደረገልን ካለው ነገር ይልቅ ያልሆነልን ነገር ጎልቶ ስለሚታየን፤ ወይም በእኛ ህይወት ውስጥ ከሚያደርገው ነገር ይልቅ በሌሎች ሰዎች ህይወት ውስጥ ያለውን ነገር ስለምናይ ነው። ስለዚህ አሁን በዚች ሰአት ያቆመንን አምላክ ምህረቱን እያሰብን አሁን እያደረገ ያለውን ማዳን እንይ። 💪💪 4. ዝም በሉ ------------ እግዝያብሄር በህይወታችን የሚያደርገውን ነገር እንዲታየን ወይም ሊያደርግ ያሰበውን ነገር እንዳናዘገይ የአፋችንን ቃል መጠንቀቅ አለብን። ከአፋችን ለጠላት መሳሪያ ሊሆን የሚችል ማንኛውም የተስፋ መቁረጥ ወይም የመነጫነጭ የማማረር ቃላት ከአፋችን እንዳይወጣ እንጠንቀቅ። 🔷🔶🔷🔶 እነዚህን ነገሮች በህይወታችን እንድነከተል በሚፈራውና በሚጠራጠረው ስጋችን ልናደርገው ስለማንችል እየሱስ ክርስቶስ ለላከልን ለመንፈሱ ለእግዝያብሄር ዘወትር እንፀልይ። 🔊🔊#JFMDailyBibleVerse @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
2019/03/01 12:28
🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
2019/02/28 20:59
🔊🔊#JFMPhotos @jesusfreakmotivations 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
2019/02/27 09:14
📖📖Today's Bible Study📖📖 የእግዝያብሄር የእቃ ጦር (ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ. 6) ---------- 12፤ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። 13፤ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። 🔷🔶🔷🔶 ስለዚህ ሴጣን በማናያቸው ነገሮች የሚዋጋን ከሆነ እኛም ደግሞ የማይታዩ ግን በመንፈሳዊ ህይወት ስጋችን እድል ፈንታ በሌለበት ቦታ ለመስራት ተዘጋጅተን መቀመጥ አለበን። ስለዚህ አንድ ወታደርን እስር ቤት ውስጥ ተቀምጦ እያየው ይህንን መልዕክት ለመፃፍ ተነሳ፤ የእግዝያብሄር የእቃ ጦር ምንድነው? 🔷🔶🔷🔶 (ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ. 6) ---------- 14-15፤ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ 16፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ 17፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። 🔷🔶🔷🔶 መንፈሳዊ ድል እንድንነሳ ይህንን የእግዝያብሄር እቃ ጦር መልበስ አለብን። በዚህ አይነት ህይወት እንድንኖር፤ እምነታችንን የሚገነባ፤ በፅድቅ መንገድ እንድንራመድ የሚረዳን፤ የእግዝያብሄርን ቃል አንብበን በሉክ ላይ ቀለም ብቻ እንዳይሆንብን የእግዝያብሄርን ድምፅ የምንሰማበት አንድ መንገድ ቢኖር መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ለእርሱ ደግሞ መፀለይ አለብን። " በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:18) 🔷🔶🔷🔶 ስለዚህ ጠላት አመለጡኝ በቃ ብሎ ተስፋ የመቁረጥ ሃሳብ እንደሌለው እየነገርኳቹ፤ ሁልጊዜ ለሚያመጣባቹ ፈተና የምትቋቋሙ ብቻ ሳይሆን በድል ማለፍ እንዲሆንላቹ የእግዝያብሄርን የእቃ ጦር ለብሳቹ የሚያሴርባችሁን ጠላት ድል ንሱት። 🔊🔊#JFMDailyBibleVerses 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/27 09:13
#meski #leyunewselame #insta #share 🔊🔊#JFMSongs 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/25 14:43
📖📖Daily Bible Verse 📖📖 ብርሃን ሁኑ ሁላችንም የምንስማማበት አንድ ጉዳይ ቢኖር እየሱስ ወደ ህይወታችን ከመምጣቱ በፊት እና በኋላ ልዩነት እንዳለው ፤ ነገር ግን ዛሬ ጠዋት ልጠይቅ የምፈልገው ይህ ልዩነት ምን ያህል ለሰው እየተገለጠ እንደሆነ ነው። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5) ---------- 14፤ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። 15፤ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። 16፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ውስጣችን የተገለጠለንን ነገር ይዘን ልክ እንደድሮ ከነበርንበት ህይወት ተስማምቶ መኖር ሊሳንን። አንድ ብርሃን ያለው ክፍል ውስጥ ገብታቹ መብራት ሲጠፋ እየዳበሳቹ እንደምትራመዱ ትሄዳላቹ። ልክ እንደዛው፤ ህይወታችን መለወጡን እኛ ብቻ ማወቃችን በቂ አይደለም፤ ላልዳኑት መታየት አለብን። ይህንን ስናደርግ፤ እነርሱ ካሉበት ገንጠል ባልን ቁጥር ፤ በንግግራችን ሆነ በድርጊታችን ለየት ማለት ስንጀምር ያሉበት ህይወት በሚያስጠላቸው ጊዜ ምስጢሩ ምንድነው የምትለዩበት ተብለን ስንጠየቅ የዛኔ የጌታን አዳኝነት ለመናገር እድል አገኘን ማለት አይደለምን? (ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ. 5) ---------- 7፤ እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤ 8፤ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ 9-10፤ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ 11፤ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ 🔊🔊#JFMDailyBibleVerses 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/23 09:07
📖📖Today's Bible Study📖📖 👇👇👇 ህይወትን እንዳሰበልን መኖር 💪💪💪 በዚች አለም ላይ ስንኖር በብዙ ነገር ከምንኖርበት አካባቢ ጋር እንገናኛለን። ለኛ ክርስትያኖች ደግሞ ከበድ ይላል። እንዴት ልትሉኝ ትችላላቹ? 🔶🔷🔶🔷 በአለም ላሉ ሰዎች ብዙም ላይከብድ ይችላል። በአለም ላይ ሳሉ በአለም ላይ ላላቸው ነገር በጥልቀት መስራት ይችላሉ፤ ምክንያቱም አለም ላይ ከሚያካብቱት ክብር የላቀ ነገር ስለሌላቸው። አንድ አለማዊ ሀብታም ለመሆን ሙስና መስራት ቢኖርበት ለመስራት ላይቸግረው ይችላል፤ ለኛ ግን ያስቸግረናል ምክንያቱም እስር ቤት ከመግባት ሌላ ውስጣችን ያለው መንፈስ ልክ እንዳልሆነ ስለሚነግረን ነው። 🔷🔶🔷🔶 ስለዚህ አሁን እያለፋችሁበት ባለው አለም እግዝያብሄር ምን አይነት ኑሮ እንድትኖሩ የሚፈልግ ይመስላችኋል? የቅድስና ኑሮ !! የመገንጠል ኑሮ !! የመለየት ኑሮ!! " ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16) ምን ምን?? እንዴት?? እንዴት ነው በየጊዜው ከምንኖርበት አለም መገንጠል የምንችለው? እንዴት ብለን እቺ አለም በእንጀራና በት/ት ምክንያት እያንከራተተችን መለየት የምንችለው? አለም በተለያየ ሁኔታ እርኩሰት በአይን በጆሮዋችን እያስገባ፤ የማይሆነውን እየሰማንና እያየን እንዴት ብለን ነው በቅድስና መኖር የምንችለው?? 🔷🔶🔷🔶 ጥሩ ጥያቄ ነው፤ መልሱን በጥቂቱ እናውራ! መፅሀፍ ሲናገር እንዲህ ይለናል " እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።" (ወደ ዕብራውያን 12:1-2) 🔷🔶🔷🔶 በቅድስና መኖር የምንችለው ሃጥያትን አስወግደን ነውርን ንቀን ነው። እየሱስን ለመምሰል የተጠራን ነን ደግሞም እርሱ ተቀብሎ ያላለፈው ምንም ፈተና አልደረሰብንም ግን እርሱ በዚያ ውስጥም ቢሆን ለአለም እንዴት እምቢ ማለት እንደሚቻል በአፉ ቃል ብቻ ሳይሆን በህይወቱ መስክሮ አሳይቶናል። 🔷🔶🔷🔶 እንዴት ነው እስከ ሞት ድረስ የመታዘዝ አቅም ያገኘው?? እዚሁ ይነግረናል የሚጠብቀውን ደስታ በማሰብ፤ በሰማይ ስፍራ በአባቱ ቀኝ የመቀመጥን ደስታ፤ እኛን ከአባቱ ጋር ከማስታረቅ የሚያገኘው ደስታ ፤ ለኛ የዘላለም ህይወት የመስጠትን ደስታ እያሰበ በመስቀሉ ላይ በትዕግስት ፀና። 🔷🔶🔷🔶 እና እርሱ እኮ ክርስቶስ እኮ ነው፤ እኔ እንደሱ አይነት አቅም እንዴት ይኖረኛል? እንኳን ለአለም ለአንድ ጏደኛዬ እምቢ ማለት አቅም ያጣው ሰው ያን ያህል ትዕግስት ከየት አመጣለሁ? ለምትሉ መልሱ ይኸው 🔷🔶🔷🔶 ለአንድ ሰው ህይወትን ለመስጠት የሚያደርሰን በፍቅሩ ሲገዛን ነው። እና እየሱስ ክርስቶስ ፍቅሩን ህይወቱን በመስጠት አሳይቶናል። እና ይህንን ጌታ ለማምለክ ህይወታችንን ብንሰጥ ምን ይገርማል?? እንዴትስ ይከብደናል?? 🔷🔶🔷🔶 ፍቅሩን አሰላስሉ፤ የሆነላችሁን አስቡ፤ ከየት እንደወጣቹ አስታውሱ ያኔ ፍቅሩ ሰርፆ ሲገባ ልዩነቱ መገለጥ ይጀምራል። በጊዜ ደግሞ ይህንን ፍቅር ወደ ትጋት የመለወጥ አቅም እርሱ ራሱ ስለሆነ የሚሰጠን ለእርሱ ደግሞ እንፀልይ! 🔷🔶🔷🔶 " በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3:16-17) 🔊🔊JFMDailyBibleVerses 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/21 17:17
Feeling down?👇👇 🗣🗣 IT IS FINE! When you mess up it's fine, When you break things it's fine, When you annoy people around you it's fine, When you make mistakes it's fine, When you think you ruined your life it's fine. 💪💪 But It's fine doesnt mean It's right. All the wrongs we do in our life all the mistakes we commit everytime doesnt mean we are the worst people to exist because even the phrase it's fine started because those people who are saying it's fine to you have been there too or they know what you went through has happend before. So it's fine means it happens but you can change it because it's wrong to do wrong, it's wrong to walk on the same shitty road everytime... ❌❕❌❕ It's fine means it can be repaired It's fine means it's not totally damaged It's fine means there is still hope It's fine means you can still be happy It's fine means it's not over. It's fine means it's not right but dont repeat it! John chapter 8: she sinned but jesus told her sin no more! Whatever is eating you inside now it's fine but dont let it get to you again.. Motivated??💪💪 🔊🔊#JFMotivations 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/19 08:44
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/18 10:40
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/17 10:03
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/14 12:03
🔊🔊JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/13 15:28
🗣መንፈስቅዱስ ማነው?🗣 📖📖 ክፍል 2 : መንፈስቅዱስ በአዲስኪዳን መንፈስቅዱስን መቀበልና መሞላት With:- Letu 🔊🔊#JFMTeachings 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/11 12:25
🗣መንፈስቅዱስ ማነው?🗣 📖📖 ክፍል 2 : መንፈስቅዱስ በብሉይ ኪዳን With:- Letu 🙈🙈 🙇ልዩ የሰንበት ትምህርት🙇 🔊🔊#JFMTeachings 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/10 08:57
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/10 08:52
🗣መንፈስቅዱስ ማነው?🗣 📖📖 ክፍል 1 : የመንፈስቅዱስ ማንነት With:- Letu 🙈🙈 🙇ልዩ የሰንበት ትምህርት🙇 🔊🔊#JFMTeachings 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/09 14:35
🗣መንፈስቅዱስ ማነው?🗣 💫💫 ልዩ የሰንበት ትምህርት 🙋🙋 አነሆ አሁን ተጀመረ 📖መፅሀፍቅድስ ይዛችሁ📖 🎧ተከታተሉት 💫ይባረኩበታል 🔊🔊#JFMTeachings 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/09 14:34
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/09 13:49
🔥መንፈስቅዱ ማነው??🔥 #weekendteaching #whoisholyspirit #askquestions #getanswers #knowtheholyspirit #bibleverses ነገ ከሰአት በኋላ ክፍል 1 ይጠብቁን እንዳያመልጥዎ ሰንበት በJFM 🔊🔊#JFMTeachings 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/09 00:35
📖📖 Daily Bible Verse 📖📖 💫 በህልውናው መገኘት💫 መፅሀፍ ሲናገር " መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:18) ለምንድነው መንፈስ ቅዱስ ከወይን ጠጅ ጋር የተነፃፀረው? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን። 🤔🤔 መልሱም ይህ ነው! ✅✅ ሁለቱም ሲቆይበት ተመሳሳይ አይነት ለውጥ ይኖራቸዋል። ወይን ጠጅ ሲጠጣ ለዋለ ሰው ወደ ስካር ሲሄድ በፍፁም ራሱን መሆን አይችልም። ኖሮት የማያቀውን አይነት ድፍረት ይኖረዋል፤ አስጨነቁኝ የሚላቸው ነገሮች ሁሉ ይረሳሉ፤ እንደ ሌላ ሰው ያደርገዋል፤ አረማመዱ፣ አነጋገሩ፣ ማንነቱ ሁሉ ይቀየራል። 👆👆👆 (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 23) ---------- 29፤ ዋይታ ለማን ነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው? 30፤ የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈትኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን? በወይን ጠጅ ለሚዘገዩ እና በእርሱ ቁጥጥር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ያላቸው ህይወት የላይኛው ጥቅስ አብራርቶ ነግሮናል። 💥💥💥 በእግዝያብሄር መንፈስ በቆየን ቁጥር ይቆጣጠረን ይጀምራል። ልክ ወይን ጠጅ በአንድ ብርጭቆ ማስከር እንደማይችል ሁሉ መንፈስና በህልውናው ለመኖር በቤቱ፤ በፀሎት፤ በቃል ማንበብ እና በዝማሬ መቆየት ያስፈልጋል። 🔥🔥🔥 አንዳንዶቻቹ መንፈስቅዱስን መጠበቅ ከሌሎች የዘገያቹ ሊመስላቹ ይችላል፤ እኔ ልንገራቹ አይደለም። እግዝያብሄር በራሱ ጊዜ ወደ ህይወታቹ ሃይሉን ይገልጣል፤ ግን ጊዜው በደረሰ ጊዜ ጌታ ከመሰውያቹ ወታቹ እንዳያገኛቹ ተጠንቀቁ። 🔥🔥🔥 ሰበብ በመፍጠር ከእርሱ አንራቅ አይጠቅመንም። መንፈሱ አይሰማኝም፤ ፀሎት ደረቀብኝ፤ የቃላት ጋጋታ ሆነብኝ ፤ መፅሀፍ ቅዱስ እጅ እጅ አለኝ የምትሉ ትኖራላቹ። እኔ ዛሬ አንድ ነገር ልንገራቹ 🔥🔥🔥 እንደ ባልአምሳ ቀን መንፈስ የመጣው ሲፀልዩ ነው አንጂ መንፈሱ ስለመጣ አይደለም የፀለዩት። ለማለት የፈለኩት በእርሱ ህልውናው በቆየን ቁጥር፤ ዝማሬ አፋችንን ሁሌ በያዘው ቁጥር፤ በፀሎት በዘገየን ቁጥር ፤ ቃሉን በማንበብ በዋልን ቁጥር ውጤታችንን ሳይሆን መንገዳችንና መሻታችንን የሚያይ አምላክ ስላለን መንፈሱን በኛ ላይ ማፍሰስና ሃይሉን በኛ ላይ መግለጥ ይጀምራል። 🔥🔥🔥 ሰለዚህ በመሰዊያችን ሆነን እንጠብቀው፤ ጌታ ሊመጣ ባሰበ ጊዜ ዘይታችንን ይዘን እንጠብቀው፤ ብልቃታችንን አጉለን በረፈደ ጊዜ ለመሙላት ስንፋጨረጨር ጌታችን እንዳያመልጠን። 🔥🔥🔥 መንፈሱን እንጠብቀው፤ ለምኑ ይሰጣችኋል ያለን አምላክ ለቃሉ ታማኝ ነው። 🔥🔥🔥 መንፈሱ ይመጣል፤ ነገር ግን የእናንተን ፀሎት ስለሚፈልግ 🙇 ፀልዩ🙏 ፀልዩ 🙏ፀልዩ🙇 🔊🔊#JFMDailyBibleVerses 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/08 10:55
🔊🔊JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/07 21:13
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/06 19:08
የህይወት ምንጭ እየሱስ__ዘማሪት ማህሌት
AudioTrim
🎙🎺🎹🎸🎻🎺🎙🎧🔊 የህይወት ምንጭ እየሱስ 🗣 ዘማሪት ማህሌት🎙 Jimma University Fellowship Live Worship 👆👆👆👆👆👆 🔊🔊#JFMSongs 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/05 18:45
🔊🔊#JFMPhotos 💪@jesusfreakmotivations💪
2019/02/05 18:33
1