Bleacher Report Football


495 Members

ስለ ሁሉም ሊግ ሚዘገብበት ፣ ጨዋታዎች በቀጥታ ስርጭት ሚተላለፉበት ፣ የዝውውር ዜናዎችም ሳይቀሩ ሚነገሩበት ምርጥ ቻናል እንዳያመልጣቹ።
#ምርጫቹ@Bleacher_Football ብቻ ይሁን

ሀሳብ አስተያየት(0924621529 ) @Yaredtg በስልክ ቁጥር


የስፖርት መረጃ ለማግኘት ትክክለኛው አማራጭ
{links} {LinksTitle}
{/links}
Today Views : 0
Yesterday Views : 0
One Year Views : 30
የ2019/20 የ UEFA የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ቨርጅል ቫንዳዬክ ሆኖ ተመርጧል።
2019/08/30 02:07
ቨርጅል ቫንዳዬክ እና አሊሰን ቤከርም ሞናኮ የዝግጅቱ ቦታ ተገኝተዋል።
2019/08/30 02:07
የ UEFA የ 2018/19 የአመቱ ምርጥ አጥቂ ሊዮናል አንድሬስ ሜሲ።
2019/08/30 02:07
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ዝግጅቱ ቦታ ደርሱዋል።
2019/08/30 02:07
ሊዮናል ሜሲ ከባለቤቱ ጋር ዝግጅቱ ቦታ ተገኝቱዋል።
2019/08/30 02:07
እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ በውሰት ውል ወደ ሮማ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሱዋል።
2019/08/30 02:07
3ቱም እጩዎች
2019/08/30 02:07
የ UEFA የአመቱ ምርጥ በረኛ አሊሰን ቤከር።
2019/08/30 02:07
የ UEFA የ 2018/19 የአመቱ ምርጥ አማካይ ፍራንኪ ዲዮንግ።
2019/08/30 02:07
የ UEFA የ 2018/19 የአመቱ ምርጥ ተከላካይ ቨርጅል ቫንዳዬከ።
2019/08/30 02:07
የ UEFA የ 2018/19 የአመቱ ምርጥ አጥቂ ሊዮናል አንድሬስ ሜሲ።
2019/08/30 02:07
🇬🇧በ 3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ። 👉FULL TIME⌚️ 🌕ኖርዊች 2⃣ - 3⃣ ቼልሲ⚪️ #ካንትዌል '6⚽️ #አብረሀም '3⚽️,68'⚽️ #ፑኪ '30⚽️ #ማውንት '17⚽️
2019/08/24 18:03
የዓርብና ቅዳሜ ጨዋታዎች ዓርብ ምሽት እንግሊዝ • አስቶንቪላ - ኤቨርተን… 4፡00 ስፔን • ግራናዳ - ሴቪያ… 3፡00 • ሌቫንቴ - ቪያሪያል… 5፡00 ቡንደስሊጋ • ኮለን- ቦሩሲያ ዶርትመንድ…3፡30 ቅዳሜ እንግሊዝ • ኖርዊች - ቼልሲ…. 8፡30 • ብራይተን - ሳውዛምፕተን….11፡00 • ማንቸስተር ዩ. - ክ.ፓላስ…11፡00 • ሼፊልድ ዩ - ሌይስተር….11፡00 • ዋትፈርድ - ዌስትሃም 11፡00 • ሊቨርፑል - አርሰናል….1፡30 ስፔን • ኦሳሱና - ኤይባር…12፡00 • ሪያል ማድሪድ - ሪ. ቫያዶሊድ • ሄታፌ - አት. ቢልባኦ…4፡00 • ሴልታ ቪዕ - ቫሌንሲያ…4፡00 ጣልያን • ፓርማ - ዩቬንቱስ….1፡00 • ፊዮሬንቲና - ናፖሊ…3፡45 ጀርመን • ማይንዝ - ቦ. ሞንቼግላድባኽ…10፡30 • ኦግስበርግ - ዩኒየን በርሊን…10፡30 • ፎ.ዱሰልዶርፍ - ባ.ሌቨርኩዘን…10፡30 • ፓደቦርን - ፍራይበርግ….10፡30 • ሆፌንሃይም - ቬ.ብሬመን 10፡30 • ሼልከ - ባየርን ሙኒክ 1፡30 ፈረንሳይ • ኦንዤ - ሜትዝ…3፡00 • ዲዦ - ቦርዶ…3፡00 • አሚዬ - ኖንት… 3፡00 • ብሬስት - ሬይንስ… 3፡00
2019/08/23 22:12
ቅዳሜ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት። ═════════════════════════ ▶️ሲውዘርላንዳዊው አማካይ ዤርዳን ሻኪሪ በሊቨርፑል ወደፊት ስላለው ቆይታ ሊያጤንበት እንደሚችል ተናግሯል በቂ የመጫወቻ እድል የማያገኝ ከሆነ።(Langenthaler Tagblatt via Daily Star) ═════════════════════════ ▶️ቶተንሀም ሆስፐር እንግሊዛዊውን አጥቂ ሀሪ ኬን የሚያጣ ከሆነ በጣም አደጋ ውስጥ ይገባል ዴኒማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከማጣት በላይ ሲል የቀድሞ የሊቨርፑል ተከላካይ ጂሚ ካራገር ተናግሯል።(Daily Telegraph) ═════════════════════════ ▶️የሬያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዜኔዲን ዚዳን በ 28 አመቱ አማካዩ ሀሜስ ሮድሪጌዝ ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል ምንም እንኩዋን ኮሎምቢያዊው አማካይ በዚህ ክረምት ከበርናበው ይለቃል ቢባልም።(Corriere dello Sport - in Italian) ═════════════════════════ ▶️ጣልያናዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ አንድሬ ኮንቴ ከኤስሚላን የሚለቅ ከሆነ የጣልያኑ ክለብ የቶተንሀሙን አይቬሪኮስታዊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ሰርጂ ኦሬርን ለማስፈረም እንደሚያጤንበት ተዘግቡዋል።(Gazzetta dello Sport - in Italian) ═════════════════════════ ▶️የፖል ፖግባ ወንድም ማቲያስ ፖግባ የ 26 አመቱ ፈረንሳያዊ አማካይ ወንድሙ ፖል ፖግባ አሁንም ከማንችስተር ዩናይትድ በመልቀቅ ሬያል ማድሪድን መልቀቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል።(El Chiringuito via Daily Mail) ═════════════════════════ ▶️ለበርካታ ግዜያት ስሙ ከኢንተር ሚላን ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረው የ 33 አመቱ ቦሲኒያዊው አጥቂ ኤደን ዤኮ በሮማ የሚያቆየውን የ 3 አመት ኮንትራት መፈረሙ ተረጋግጡዋል።(AS Roma) ═════════════════════════ ▶️የባየርሙኒክ እና የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ የነበረው የ 21 አመቱ ሆላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ስቴቨን ብሪውጂን ለፒኤስቪ ታማኝ በመሆን ለቀጣዩ 5 አመታት በክለቡ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት ደርሱዋል።(Goal) ═════════════════════════ ▶️የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረሙዋቸው ተጫዋቾች መድፈኞቹን ያጠናክሩ አያጠናክሩ እንደማያውቁ ተናግረዋል።(Mirror) ═════════════════════════ ▶️የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቲቴ በፓሪሴንዤርመን ቢቆይ ጥሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል ነገር ግን ውሳኔውም የራሱ መሆኑን አክለው ተናግረዋል።(Marca) ═════════════════════════ ▶️አርሰናል ባለፈው በጥሩ የዝውውር መስኮት ለአንገር የ 21 አመቱን አማካያቸውን ጄፍ ሬን አዴላይድን መሸጣቸው የሚታወስ ይሆናል አሁን ደግሞ አንገር ጄፍ ሬን አዴላይድን ለሊዮን መሸጡን ተከትሎ መድፈኞቹ በዚህም የዝውውሩን 20% £5m እንደሚያገኙ ተዘግቡዋል።(Evening Standard) ═════════════════════════ ▶️የቶተንሀሙ አማካይ ሙሳ ሴሴኮ ሰኔ ላይ በቻምፕዮን ሊግ በሊቨርፑል ከተሸነፉ ቡኃላ ማልቀሱን ተናግሯል።(Talksport) ═════════════════════════ ▶️ኦሊገነር ሶልሻየር፦አሌክሲስ ሳንቼዝ የዚህ ሲዝን የክለቤ አንድ እቅድ አካል ነው። ═════════════════════════ ▶️ፊሊፔ ኮቲኖ በቀጣዮቹ 24 ሰዓታት ውስጥ በውሰት ወደ ባየርሙኒክ እንደሚቀላቀል እየተዘገበ ይገኛል።ባቫሪያኖቹ በውሰት አንቀፁ ውስጥም በቀጣዩ አመት በቁዋሚነት የመግዛት አማራጭንም እንደሚያካትቱ በተጨማሪነት ተዘግቡዋል።(BILD) ═════════════════════════ @️ዛሬ በተለያዩ ሊጎች የሚደረጉ ጫወታዎች የሰዓት ጥቆማ ▶️የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ አርሰናል 8: 30 በርንሌ አስቶንቪላ 11 : 00 በርንስማውዝ ብራይተን 11: 00 ዌስትሀም ዩናይትድ ኤቨርተን 11: 00 ዋትፎርድ ኖርዊች ሲቲ 11 : 00 ኒውካስል ዩናይትድ ሳውዝሀምፕተን 11 : 00 ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲ 01 : 30 ቶተንሀም ሆስፐር ═════════════════════════ ▶️የፈረንሳይ ሊግ 1 ናንትስ 12 : 30 ማርሴ ሜትዝ 03 : 00 ሞናኮ ቱሉስ 03 : 00 ዲጆን ኒምስ 03 : 00 ኒስ አሜንስ 03 : 00 ሊል ቦርዶ 03 : 00 ሞንፔሌ ═════════════════════════ ▶️የጀርመን ቡንደስሊጋ ቦርሲያዶርትመንድ 10 : 30 ኦግስበርግ ባየርሊቨርኩሰን 10 : 30 ፓደርቦርን ወልፍስበርግ 10 : 30 ኮሎኝ ወርደር ብሬመን 10 : 30 ፎርቱን ዱሶልዶርፍ ፍራይቡርግ 10: 30 ሜንዝ 05 ቦርሲያ ሞንቸግላድባክ 01 : 30 ሻልካ 04 ═════════════════════════ ▶️የስፔን ላሊጋ ሴልታቪጎ 00 : 00 ሬያል ማድሪድ ቫሌንሺያ 02 : 00 ሬጫወታ ማስተላለፍ ብቻ ያል ሶሲዳድ ማሎርካ 03 : 00 ኢባር ሌጋኔስ 04 : 00 ኦሳሱና ቪያርያል 04 : 00 ግራናዳ
2019/08/17 11:09
አርብ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት። ═════════════════════════ ▶️ፈረንሳያዊው አማካይ ፖል ፖግባ በዚህ ክረምት ከማንችስተር ዩናይትድ ወደ ሬያል ማድሪድ ለማድረግ ያሰበው ዝውውር ላይ ተስፍ እንደቆረጠ ተዘግቡዋል።(Marca) ═════════════════════════ ▶️የ 26 አመቱ እንግሊዛዊ ተከላካይ ሀሪ ማጉዋየር ወደ ማንችስተር ሲቲ እንዲዘዋወር በሳምንት £278,000 ሳምንታዊ ደሞዝ ቢያቀርቡለትም ውድቅ በማድረግ ነበር ወደ ተቀናቃኙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ያቀናው።(Star) ═════════════════════════ ▶️የዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶሻየር ከቶተንሀሙ ዴኒማርካዊ አማካዩ ክርስቲያን ኤሪክሰን ጋር ተነጋግረው ነበር ወደ ኦልትራፎርድ ለማዘዋወር ነገር ግን የ 27 አመቱ አማካይ ወደስፔን ማቅናት ስለሚፈልግ ነው ሳያስፈርሙት የቀረው።(Manchester Evening News) ═════════════════════════ ▶️የማንችስተር ዩናይትዱ ቺሊያዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች አሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ጣልያን ለመሄድ ተዘጋጅቱዋል ጁቬንቱስ፣ናፖሊ፣ኤስሚላን እና ኢንተር ሚላን የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው።(Mirror) ═════════════════════════ ▶️ሳንቼዝ የአውሮፓ የዝውውር መስኮት መስከረም ሁለት ላይ ከመዘጋቱ በፊት ከማንችስተር ዩናይትድ መልቀቅ ይፈልጋል የልቀቁኝ ደብዳቤ አስገብቶም ቢሆን። (Times) ═════════════════════════ ▶️እንደአማራጭ ሳንቼዝ አሁን በዩናይትድ ቤት የሚከፈለውን £560,000- ሳምንታዊ ደሞዝ የሚከፍለው ገዥ ክለብ ለማግኘት መፈለግ ይኖርበታል ከኦልትራፎርድ ለመልቀቅ።(Mirror) ═════════════════════════ ▶️ጁቬንቱስ አሁንም የ 25 አመቱን አርጀንቲናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ፖል ዲባላን የአውሮፓ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት እንደሚሸጡት ተማምነዋል ነገር ግን ምንም አይነት የቀረበላቸው ጥያቄ የለም።(Independent) ═════════════════════════ ▶️የፓሪሴንዥርመኑ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሌናርዶ ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኔይማር ስህተት ሰርቱዋል ከፓርክደፕሪንስ በግድ ለመልቀቅ ሙከራ ማድረጉ ሲል ተናግረዋል።(RMC - in French) ═════════════════════════ ▶️የስቶክ ሲቲው እንግሊዛዊው በረኛ ጃክ ቡትላንድ ከስቶክ ሲቲ ለመልቀቅ የልቀቁኝ ደብዳቤ ለማስገባት እያጤነበት ነው በ euro 2020 የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በመወከል የአሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት አንድ እቅድ አካል ለመሆን።(Mail) ═════════════════════════ ▶️የብራዚሉ ክለብ ፍላሚንጎ ክለብ አልባ ከሆነው ማሪዮ ባላቶሊን ዝውውር እራሱን አግሉዋል አመታዊ £4m ደሞዝ መጠየቁን ተከትሎ።(Mail) ═════════════════════════ ▶️ናፖሊ የ 23 አመቱን ሜክሲኩዋዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሄርቬ ሎዛኖን ከሆላንዱ ክለብ ፒኤስቪ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሱዋል።(Voetbal International - in Dutch) ═════════════════════════ ▶️የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት ማንችስተር ዩናይትድ የ 28 አመቱን ሴኔጋላዊ ተከላካይ ካሊዶ ኩሊባሊን ለማስፈረም £82m ቢያቀርቡም ናፖሊ ውድቅ አድርጎባቸው ነበር።(Corriere dello Sport, via Calciomercato) ═════════════════════════ ▶️የ 23 አመቱ የበርንስማውዝ እንግሊዛዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ጆርዳን አይብን የስኮትላንዱ ክለብ ሴልቲክ ለማስፈረም ፍላጎት አለው።የጣልያኑ ክለብ ናፖሊም ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቡዋል።(Sun) ═════════════════════════ ▶️ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾቹን እየቀጣ ይገኛል በካሪንግተን የልምምድ ሜዳ መግቢያ ላይ ለደጋፊዎችም ይሆን ለአድናቂዎቻቸው የሚፈርሙ ከሆነ ምክንያታቸው ደግሞ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው።(Telegraph) ═════════════════════════ ▶️የዌስትሀሙ አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ወደ ሊቨርፑል ያቀናውን በረኛቸውን አድሪያን በለንደን እንዲቆይ ነግረውት እንደነበር ተናግረዋል።(Mail) ═════════════════════════ ▶️ዛሬ የሚካሄዱ ጫወታዎች የፈረንሳይ ሊግ 1 ኦሎምፒክ ሊዮን 03 : 45 አንገር የጀርመን ቡንደስሊጋ ባየርሙኒክ 03 : 30 ኸርታበርሊን የስፔን ላሊጋ አትሌቲኮ ቢልባኦ 04 : 00 ባርሴሎና ═════════════════════════ ▶️የ 2018/19 የ UEFA የወንዶች የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች እጩዎች 🔥ሊዮናል ሜሲ 🔥ቨርጅል ቫንዳዬክ 🔥ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሽልማቱ የሚካሄደው በፈረንጆቹ ኦገስት
2019/08/16 10:32
መፍትሔ አጥተው በማይፈታ እንቆቅልሽ ውስጥ ሳሉ የውጭው በር በድንገት ተንኳኳ፡፡ በሌላ ክፍል የነበረው ሊዮ የበሩን መንኳኳት ቀድሞ ስለሰማ ፈጠን ብሎ ሄዶ ከፈተ፡፡ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቅ በሙሉ ልብስ የዘነጠ ረጅም ሰው ከደጃፉ ቆሞ ተመለከተ፡፡….. (ይቀጥላል)
2019/08/16 10:28
የሜሲ ወላጆች ልፋት (ክፍል 5) …ሆርጌ የልጁን የምልመላ ሙከራ ጨዋታ እየተመለከተ ከሜዳው ራቅ ብሎ በስሜት ይዘላል፡፡ ሊዮ አፍታም ሳይፈጅበት በልዩ ፍጥነት ከአንደኛው ተጫዋች እግር ስር ኳሷን ቀምቶ በቁጥጥሩ ስር አዋላት፡፡ ጉድ በሚያሰኝ ቅልጥፍና የተጠጉትን ተጫዋቾች አልፎ በግቡ ፊት ለፊት ሲገናኝ በግራ እግሩ አጠማዞ ወደ መረቡ ላካት፡፡ ግብ ጠባቂው ቢንሳፈፍም ኳሷን ሊነካት እንኳን አልቻለም፡፡ ሊዮ ጎሉን ሲያስቆጥር አባቱ በታላቅ እፎይታ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ የሪቨር ፕሌት አሰልጣኞች የሊዮን ድንቅ ጥበብ በዓይናቸው፣ በብረቱ ተመለከቱ፡፡ ተማረኩበት፡፡ ታላቅ ተስፋ ላሳዩዋቸው ዕጩ ተመልማዮች እንደሚያደርጉት ሁሉ ለሊዮም ተጨማሪ 10 ደቂቃ በሜዳ ላይ እንዲቆይ ፈቀዱለት፡፡ ልጁ የዋዛ አይደለም፡፡ ሁለት ጊዜ ጎል በማስቆጠር በጭማሪ ዕድሉም ተጠቀመበት፡፡ በዚህ አላበቃም፡፡ የቡድን ጓደኛው አንድ ጎል እንዲያስቆጥር ጣጣውን የጨረሰ ኳስ አቀበለው፡፡ ኦው!... የሪቨር አሰልጣኞች በሮዛሪዮው ልጅ ብቃት እርካታ ተሰማቸው፡፡ ‹‹ይበቃል!›› ብለው የሙከራ ጨዋታውን እንዲያቆም ሲያዙት ዋናው መልማይ በሊዮኔል ሜሲ ውስጥ ያልተጠረገ አልማዝ በመመልከቱ የደስታ ስሜቱ በፊቱ ፈገግታ ላይ ይንጸባረቅ ነበር፡፡ ሊዮ ከሌሎች ታዳጊዎች ጋር በሜዳው ዳር አረፍ ብሎ የአሰልጣኞቹን ውሳኔ መጠባበቅ ጀመረ፡፡ መልማዮቹ አምስት ታዳጊዎችን በየተራ ጠሩ፡፡ ከተጠሩት አንዱ እርሱ ነበር፡፡ ‹‹ወላጆችህ አብረውህ መጥተዋል?›› ከአሰልጣኞች አንዱ ወደ ሊዮ እየተመለከተ ጠየቀ፡፡ ‹‹አባቴ ያውላችሁ›› አለ ሊዮ፣ ወዲያ ማዶ ወዳለው ሆርጌ እየጠቆመ፡፡ አሰልጣኙ በአዎንታ ጭንቅላቱን ነቅንቆ ከሌላኛው አሰልጣኝ ጋር በስኬት መንፈስ ተጨባበጠ፡፡ ‹‹እንግዲያው አባትህን ልናነጋግር እንፈልጋለን፡፡›› ሆርጌ ከመጣ በኋላ ውሳኔያቸውን በአጭሩ ነገረው፡፡ ‹‹ወደ ሪቨር ፕሌት ይዘኽው ና›› ብሎ ፊቱን ወደ ሌሎቹ ህጻናት አዞረ፡፡ * የሆርጌ ልብ ደለቀ፡፡ ሊዮ ተሳካለት፡፡ ከአርጀንቲና ታላላቅ ክለቦች አንዱ ለሆነው ሪቨር ይመዘገብ ዘንድ የምልመላ ሙከራውን በብቃት አለፈ፡፡ ቢሆንም ውሳኔያቸውን ሊዮ ገና አላወቀም ነበር፡፡ የሙከራውን ውጤት አባቱ እንዲያስረዳው ጠየቀው፡፡ ‹‹አባ!... ምን አሉህ?›› ‹‹ልጄ!.. እዚሁ እንድትቀር ፈልገዋል›› አለ ሆርጌ የተሰማው ደስታ እንዳይታወቅበት ለመደበቅ እየሞከረ፡፡ ሊዮ ፈገግ አለ፡፡ በምልመላ ሙከራው ላይ ክህሎቱን በሚገባ እንዳሳያቸው እርግጠኛ ነው፡፡ ጉራውን መንፋት ስላልፈለገ ነው እንጂ መልማዮቹም ቀልባቸው እንደወደደው አውቋል፡፡ ‹‹ግን ለኒዌልስ ኦልድ ቦይስ እየተጫወትኩ መሆኑን ነግረሃቸዋል?›› ሆርጌ የሊዮን ጥያቄ ሲሰማ ስሜቱ ተቀያየረ፡፡ ሊዮም የአባቱ ፊት መቀያየሩን አጢኖ ቀና እንዳለ ‹‹ምነው? ችግር አለ እንዴ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ በእርግጥም ሊዮ ለኒዌልስ ኦልድ ቦይስ የታዳጊዎች ቡድን እየተጫወተ መሆኑን ሆርጌ ለሪቨሮች አላሳወቃቸውም፡፡ ሪቨሮች ሊወስዱት እንደሆነ ካወቁ ኒዌልሶች እንዲሁ በቀላሉ አይለቁትም፡፡ ባይሆን ጠቀም ያለ ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ ሆርጌ አሰልጠኞቹን በአይኑ ለመፈለግ የሜዳውን ዙሪያ አማተረ፡፡ በስታዲየሙ መውጫ በር አጠገብ ዋናው አሰልጣኝ ከሌሎች ታዳጊዎች ጋር ቆሞ ተመለከተው፡፡ ‹‹ሊዮ! አንተ እዚህ ጠብቀኝ..›› ብሎ ወደ አሰልጣኙ በረረ፡፡ ‹‹ጌታዬ! አንድ ያልነገርክዎት ነገር አለ፡፡… ልጄ ለኒዌልስ እየተጫወተ ነው፡፡›› አሰልጣኙ በሰማው ነገር አልተደሰተም፡፡ ግን ተጨማሪ ማብራሪያ ፈልጎ ጥያቄውን አስከተለ፡፡ ‹‹ኒዌልስ?... ኮንትራት ፈርሟል?›› ሆርጌ ከንፈሩን እየመጠጠ እውነቱ ነገረው፡፡ ‹‹አዎ! ኮንትራት ፈርሟል፡፡›› ‹‹አየህ…! ችግር አለ ማለት ነው፡፡›› አሰልጣኙ ቀጠለ፡፡ ‹‹ልንደራደራቸው እንችላለን፡፡ ነገር ግን እነርሱ ብዙ ገንዘብ የሚጠይቁ ናቸው፡፡ የበዛ ክፍያ ይፈልጋሉ፡፡›› ሆርጌ ፈጠን ብሎ ‹‹ጥሩ ነው፡፡ በቶሎም ስምምነት ላይ እንደምትደርሱ….›› እንዳለ አሰልጣኙ ንግግሩን አቋርጦት፣ ጭንቅላቱን በአሉታ እየነቀነቀ ቁርጡን ውሳኔ አሳወቀው፡፡ ‹‹በቃ! በቃ!... ድርድሩን እርሳው፡፡ ወደ እኛ ስላመጣኽው በጣም እናመሰግናለን፡፡ በቃ! እንዲያውም አያስፈልገንም፡፡ ይዘኽው ሂድ፡፡ መልካም ቀን!›› ብሎት ከአጠገቡ ሄደ፡፡ አሰልጣኙ ርቆ ሲሄድ ሆርጌ በጸጸትና በስስት አይኑ ተመለከተው፡፡ የልጁን የህክምና ወጪ የሚሸፍን ክለብ ፍለጋ ከአራት ሰዓት በላይ የተጓዘበት ዓላማ ውሃ በላው፡፡ ከርታታው ሆርጌ አይኑን ጨፈን አድርጎ የሆነውን ለሚጓጓው ልጁ ሊነግረው ተዘጋጀ፡፡ ‹‹ልጄ!... በቃ!... ለሪቨር ፕሌት መጫወት አትችልም፡፡ አይዞህ ገና ብዙ ከዚህ የተሻሉ ዕድሎች ይጠብቁሃል፡፡›› ‹‹አባ!... ዛሬኮ ጥሩ የተጫወትኩ መስሎኝ ነበር›› አለ ሊዮ የሚናገረው ጠፍቶት፣ አይኑን ፈንቅሎ ሊወጣ ከተቃረበው እንባው ጋር እየታገለ፡፡ በድንገት ባዶነት ተሰማው፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባት ታውቃለችና በሞት የተለየችው አያቱ ሴሊያ አጠገቤ ብትሆን ብሎ ተመኘ፡፡ ‹‹ልጄ! ነገሩ ያንተ አጨዋወት ወይም የችሎታህ ጉዳይ አይደለም፡፡ የፉትቦል ቢዝነስ ጉዳይ ነው፡፡ አንተማ ድንቅ ጨዋታ ተጫውተሃል፡፡ ግን በእግር ኳስ ውስጥ የሚሽከረከረው ገንዘብ ብዙ ነው፡፡›› ‹‹እሺ! ታዲያ ምንድነው ማድረግ ያለብን?...›› ሊዮ አባቱ መፍትሔ ያለው እንደሁ ጠየቀ፡፡ ‹‹በቃ! ለእኔ ተወው፡፡ አንተ ሳትጨነቅ ዝም ብለህ ተጫወት፡፡ እኔ መፍትሔ አመጣለሁ፡፡ አይዞህ ዕድል ከእኛ ጋር ትሆናለች፡፡›› ሆርጌ ከራሱ ጋር እየታገለ ልጁን የማያስከፉ ቃላት እየፈለገ የማጽናናት ሙከራውን ቀጠለ፡፡ ‹‹አየህ! ሪቨሮች ወደውህ ነበር፡፡ ፈተናቸውን በብቃት አልፈሃል፡፡ ትልቁ ሪቨር ያለህን ከወደደው ደግሞ ሌሎችም ያንተን ችሎታ መቀበላቸው አይቀርም፡፡›› ካለ በኋላ ሆርጌ በራሱ ቃላት ተጽናና፡፡ ወደ ትንሹ ልጁ እየተመለከተ ፊቱን በፈገግታ አበራለት፡፡ ሊዮ በነገሩ ላይ ለረጅም ጊዜ አሰበ፡፡ የአባቱ በራስ መተማመን አጽናናው፣ አጠነከረው፡፡ ‹‹ከዚህ የበለጠ እንደምሆን አውቃለሁ፡፡ አሁን ደህና ነኝ›› ሲል ስሜቱን ለአባቱ አሳወቀ፡፡ ሆርጌ ‹በጣም ጥሩ›› ካለ በኋላ እጁን በሊዮ ትከሻ ላይ አኑሮ ወደ መውጫ በሩ አመሩ፡፡ * ወትሮ የወጥ ቤቱ የምግብ ጠረጴዛ በምግብና በቤተሰብ አባላት ይሞላ ነበር፡፡ አሁን ግን ከባልና ሚስቱ በስተቀር በዙሪያው ሌላ የለም፡፡ ሆርጌ ከቡዌኖስ አይረስ መልስ የአራት ሰዓት የአውቶቡስ ጉዞ አድርጓል፡፡ ከአታካቹ ጉዞና ከጸጸቱም በኋላ ተዳክሟል፡፡ ልጁ ድንቅ የእግር ኳስ ተሰጥኦ ባለቤት እንደሆነ ቅንጣት ታክል አይጠራጠርም፡፡ ግን መላ የአርጀንቲና ክለቦች ቢፈልጉት እንኳን ሊዮ ችግር አለበት፡፡ ያለ ሆርሞኑ መርፌ ቁመቱ ሊያድግ አይችልም፡፡ ህክምናው ደግሞ ከቤተሰቡ አቅም በላይ ሆኗል፡፡ የህክምናውን ግማሽ ወጪ ይሸፍን የነበረው ኒዌልስ ኦልድ ቦይስ ደግሞ ሄዶ ሄዶ፣ ወጪው ወገቡን አጉብጦት ከመሐል መንገድ ቆሟል፡፡ የሊዮ ነገር በተለይ የወላጆቹ ጭንቀት ሆኗል፡፡ ‹‹እሺ!... አሁን ምንድነው ማድረግ ያለብን?›› አለች እናት ሴሊያ ለሆርጌ ሙቅ ቡና ወደ ብርጭቆው እየቀዳችለት፡፡
2019/08/16 10:28
😂👊👏
2019/08/15 22:23
🔥ሃሙስ ምሽት የወጡ በርካታ የዝውውር ዜናዎችና ሌሎችንም መረጃዎችን ያንብቡ - Latest News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር አድርጉት! ═══════════════ ══════════ 📌አሌክሲስ ሳንቼዝ ማን.ዩናይትድን በክረምቱ የዝውውር መስኮት አለቅም በሚል አቋሙ እንደፀና ነው፤ ምንም እንኳን ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ክለቡን እንዲለቅ ካልሆነ ግን ወደ ሁለተኛው ቡድን እንደሚልከው ቢነግረውም። ሮማዎች አሁን ሌሎች አማራጮችን እያዩ ነው። (Sun) ═══════════════ ══════════ 📌የሴሪአው ክለቦች ኤሲ ሚላን፣ ጁቬንቱስ እና ናፖሊዎች የ30 አመቱን ቺሊያዊ አጥቂ ሳንቼዝ ለማዛወር አሁንም ፍላጎት አሳይተዋል። (Mail) ═══════════════ ══════════ 📌ሪያል ማድሪዶች ከፒ.ኤስ.ዤዎች በኔይማር ዝውውር ላይ የ19 አመቱን ብራዚላዊ የፊት መስመር ተሰላፊ ቪኒቺየስ ጁኒየርን እንዲያካትቱት ቢጠይቋቸውም ውድቅ አድርገውባቸዋል። (AS) ═══════════════ ══════════ 📌ከቪኒቺየስ በተጨማሪም፣ ፒ.ኤስ.ዤዎች በየትኛውም የኔይማር ዝውውር ድርድር ላይ የ33 አመቱ ክሮሺያዊ አማካይ ሉካ ሞድሪች እና የ27 አመቱ ብራዚላዊ አማካይ ካሳሜሮ የዝውውሩ አካል እንዲሆኑላቸው ይጠይቃሉ። (Marca) ═══════════════ ══════════ 📌ኔይማር ትላንትና በግሉ ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል። ክለቡ እስከሚሸጠው ድረስም በግሉ ልምምድ እየሰራ ይቆያል። (Esporte Interactivo, via Mundo Deportivo - in Spanish) ═══════════════ ══════════ 📌ብራዚላዊው የ27 አመት አማካይ አጥቂ ፊሊፕ ኩቲንዎ የኔይማር የዝውውር አካል ሆኖ ሳይሆን በቀጥታ ዝውውር የፓሪሱን ክለብ ሊቀላቀል ይችላል። (Goal) ═══════════════ ══════════ 📌የማንቸስተር ዩናይትድ እና የሲውዲኑ መሃል ተከላካይ የ25 አመቱ ቪክተር ሊንደሎፍ አሁን ከሚከፈለው ሳምንታዊ £75,000 ደሞዝ የተሻለ ከፍተኛ ደሞዝ የሚያገኝበትን አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም ነው። (Aftonbladet - in Swedish) ═══════════════ ══════════ 📌ባየር ሙኒኮች የማንቸስተር ሲቲውን የ23 አመት ጀርመናዊ የክንፍ ተጭዋች ሎሪ ሳኔን አሁንም የማዛወር ፍላጎት አሳይተዋል፤ ምንም እንኳን ተጭዋቹ በጉልበት ጉዳት ምክንያት ለሰባት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ቢታወቅም። (Bild - in German) ═══════════════ ══════════ 📌ማንቸስተር ዩናይትዶች የ24 አመቱን የስፖርቲንግ ሊዝበን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር የተውት ተጭዋቹ በተደጋጋሚ ግዜ ኳሶችን ለተቃራኒ ቡድን አሳልፎ ስለሚሰጥ ነው የሚል መረጃ ከመልማዮቻቸው ስለደረሳቸው ነው። (Mail) ═══════════════ ══════════ 📌የኤቨርተኖች ናይጄሪያዊው ክንፍ አሌክስ ኤዎቢ አርሰናልን የለቀቀው ካሁን በኃላ ተስፈኛ ታዳጊ ተጭዋች ሳይሆን የበሰለ ተጭዋች መሆኑን ለማስመስከር ነው። (Mirror) ═══════════════ ══════════ 📌ቦሩሲያ ዶርትመንዶች የ19 አመቱን እንግሊዛዊ የክንፍ ተጭዋች ጃደን ሳንቾን ለማዛወር ከበርካታ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ጥያቄ ቢቀርብላቸውም እንዳልተቀበሉት አሳውቀዋል። ተጭዋቹ የማን.ዩናይትድ የዝውውር ኢላማ እንደነበር ይታወሳል። (Ruhr Nachrichten - in German) ═══════════════ ══════════ 📌ቶተንሃሞች ሴፕቴምበር 2 የአውሮፓ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት ከ27 አመቱ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ጋር አዲስ ኮንትራት ለማፈራረም ይቀመጣሉ። ሴንማርካዊውን አማካይ ለማዛወር አሁንም ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱሶች ፍላጎት አላቸው። (Independent) ═══════════════ ══════════ 📌የቀድሞው የሊቨርፑል አጥቂ የ29 አመቱ ዳንኤል ስተሪጅ በ3m euros (£2.8m) የዝውውር ሂሳብ ወደ ቱርኩ ክለብ ትራብዞስፖር ለመዛወር ተቃርቧል። (Goal) ═══════════════ ══════════ 📌አርሰናሎች ከቀድሞው አማካያቸው ጄፍ ሪኔአዴላዴ ከአንድገርስ ወደ ሊዮን ያደረገውን የ 25m euro (£23.1m) ዝውውር ተከትሎ ከዝውውሩ 25% ድርሻቸውን ይወስዳሉ። (Ouest France, via Sun) ═══════════════ ══════════ 📌ኢቫን ፔሪሲች በባየር ሙኒክ የቁ.14 ማልያ እንደሙለብስ ተረጋግጧል። (Source: FCBayern) ═══════════════ ══════════ 📌ሊቨርፑል፣ ቶተንሃም እና ማንቸስተር ሲቲዎች የእንግሊዝ የዝውውር መስኮት በግዜ በመዘጋቱ የተነሳ ብስጭታቸውን ገልፀዋል። ሦስቱ ክለቦች የእንግሊዝ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ኤፍኤው የዝውውር መዝጊያ ቀኑን ከአውሮፓው እኩል እንዲያደርግላቸው ሲወተውቱ ቢቆዩም አልተሳካላቸውም። [The Sun] ═══════════════ ══════════ 📌ኒኮ ኮቫች (Bayern München coach): "ኩቲንዎ? የትኛውም ነገር ሊፈጠር ይችላል." ═══════════════ ══════════ 📌ሰይዶ ማኔ (Liverpool): "Ballon d'Or? ሜሲ ሊያሸንፍ ይገባል." ═══════════════ ══════════ 📌ባርቶሜው ዛሬ በሚሰረገው የአውሮፓ ክለቦች ተቌም ስብሰባ ላይ የኔይማር ዝውውርን ከፒ.ኤስ.ዤ አቻዎቻቸው ጋር በመነጋገር ሊያጠናቅቁት ይቻላሉ። [gerardromero] ═══════════════ ══════════ 📌የኔይማር ዝውውር ሰጣ ገባ በቀጣዩቹ 24 ሰአታት ውስጥ ሊቋጭ ይችላል። [md] ══════
2019/08/15 22:20
የ2018/19 የUEFA የአመቱ ምርጥ ተጫዋች የመጨረሻዎቹን 3 ተጫዋቾችን ይፋ አድርጎል። 👉 ሊዮኒዬል ሜሲ 👉 ክሪስቲያኖ ሮናልዶ 👉 ቨርጂል ቫንዳይክ
2019/08/15 22:19
✔️ የእንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ_2ኛ_ሳምንት_ጫወታዎች ሁሉንም ጫወታዎች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጠጠር 👉ቅዳሜ ቀን በኤምሬትስ አርሰናል በርንሌይን ይጋብዛል 👉ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ከሳውዝሃምፕተን ይጫወታል 👉በሳምንቱ ተጠባቂ ጫወታ ቅዳሜ ምሽት ኢትሃድ ላይ ማንችስተር ሲቲ ቶተንሃምን የሚጋብዝ ይሆናል 👉እሑድ ቀን ቸልሲ በብሪጅ ሌስተር ሲቲን ሲያስተናግድ 👉ማንችስተር ዩናይትድ ሰኞ ምሽት ከሜዳው ውጪ ወልቭስን ይገጥማል። የ2ኛ ሳምንት ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሁሉንም ጫወታዎች ከታች በኢትዮጵያ አቆጣጠር አቅርበናል። ይመቻቹ 📅ቅዳሜ ነሐሴ ➊➊ ⏰8:30 ☑️አርሰናል🆚 በርንሌይ ⏰11:00 ☑️አስቶንቪላ 🆚 በርንማውዝ ⏰11:00 ☑️ብሪንግተን🆚ዌስትሃም ⏰11:00 ☑️ኤቨርተን 🆚 ዋትፎርድ ⏰11:00 ☑️ኖርዊች 🆚 ኒውካስትል ⏰11:00 ☑️ሳ.ሃምፕተን 🆚 ሊቨርፑል ⏰1:30 ☑️ማን.ሲቲ 🆚 ቶተንሃም 📅እሁድ ነሐሴ ➊➋ ⏰10:00 ☑️ሼፊልድ🆚 ክሪስታል ፖላስ ⏰12:00 ☑️ቼልሲ 🆚 ሌስተር ሲቲ 📆ሰኞ ነሃሴ ➊➌ ⏰4:00 ☑️ወልቭስ 🆚ማን.ዩናይትድ ♻️🙏🙏🙏🙏SHARE 🙏🙏🙏🙏♻️
2019/08/15 22:07
⚽️ያው እንደቀድሞ ግዜዎች ቶሎ ቶሎ ነገሮችን ለመፖሰት እየተቻለ አደለም በኔቶርኩ ምክንያት በተለይ በፌስቡክ።እስቲ ስለማታው የሱፐር ካፕ ጫወታ አንዳንድ ነገር ልበላችሁ። በሁለት ጫወታ የአንድን ቡድን የወደፊት አጨዋወት ይሄን ይሆናል ብሎ ለመገመት ቢቸግርም በፍራንክ ላምፓርድ የሚመራው ቸልሲ ግን በፕሪምየርሊጉ አዝናኝ ቡድን እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም ከያዛቸው በክህሎት ከተሞሉ ተጫዋቾች አንፃርም ሲታይ ነገር ግን አሁንም የተከላካይ ክፍሉ ጥንካሬውን መልሶ የማያገኝ ከሆነ ከላይ ያነሳዋቸው ሀሳቦች መና ሊሆኑ ይችላሉ። ፡ ⚽️ጀርጊኖ፦አሁን እየተሰጠው ያለውን እድል በመጠቀም ጥሩ የሚባል ሲዝን እንደሚያሳርፍ ተናግሯል እንዲሁ በተጨማሪነት ጀርጊኒዮ የሚለውን ስምም መገንባት እንደሚፈልግ ተናግሯል ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ያለ ሳሪ መጫወት አይችልም የሚለውን ሀሳብ ለመምከን እንደሆነም ተናግሯል። ፡ ⚽️የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ አድሪያን የአውሮፓ ዋንጫ በማንሳት ከማንችስተር ሲቲ በላይ ሆኑዋል። ፡ ⚽️እስቲ ቲውተር ላይ የቸልሲ ደጋፊዎችን እየተነጋገሩበት ያለውን ነገር እና የ VAR ጥቅም ምንድነው ብለው እየጠየቁ ነው ምክንያቱም ደግሞ ታሚ አብረሃም ኩዋሱን ከመምታቱ በፊት የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ አድሪያን ከመስመሩ አልፉዋል በሚል ምክንያት ነው ከታች በፎቶው ላይ መመልከት ይችላሉ። ፡ ⚽️ኬፓ ትላንትና የሊቨርፑል ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ሌላ ክለቦች ላይ የመቱትን የፍፁም ቅጣት ቪዲዮ በ Youtube ሜዳ ላይ ከታች ፎቶ ላይ እንደምትመለከቱት እያየ ነበር። ፡ ⚽️ትላንትና ሜዳ ውስጥ እንደ እንዝርት ሲሽከረከር የነበረው ኒጎሎ ካንቴ በሜዳ ውስጥ ያደረገው ቁጥራዊ እንቅስቃሴ : 120 minutes played 58 passes completed 92% pass accuracy 11 duels won 8(!) dribbles completed 4 chances created 1 big chance created Deserved a winners medal.
2019/08/15 14:45
MOMENTS: ሮናልዶ በመጀመሪያዋ ቀን (ክፍል 4) በዚያ ዓመት ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ኮንትራቱን ፊርማ በስፖርቲንግ ውል ላይ አኖረ፡፡ ኮንትራቱ በወር 2ሺህ ዩሮ የሚያስገኝለት ሲሆን የአራት ዓመት ርዝመት ነበረው፡፡ የማዴይራው ወጣት በኮንትራቱ ላይ በውል ማፍረሻነት 20 ሚሊዮን ዩሮ የተቀመጠለት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሆነ፡፡ ያን ጊዜ ከጎኑ የማይጠፋው ጆዜ ቬይጋ ወኪሉ ነበር፡፡ በዚያ ሰሞን በወደፊት ትልቅነቱ ላይ ብሩህ ተስፋ የተመለከተ አንድ ሰው ክሪስቲያኖና እናቱን ራት ሊጋብዛቸው ቀጠሮ ያዘ፡፡ የሰውየው የቢዝነስ ሸሪክ አብሮት ነበር፡፡ ሮናልዶና ራት ጋባዡ የዕድሜ እኩዮች አይደሉም፡፡ የ19 ዓመት ታላቁ ነው፡፡ ልጅና አዋቂ ቢሆኑም ቅሉ፣ ገና ከተዋወቁባት የመጀመሪያዋ ደቂቃ ጀምሮ ከወጣቱ ሮናልዶ ጋር ልብ ለልብ ተጣጥመዋል፡፡ ያ ሰው ጆርጌ ሜንዴዝ ይባላል፡፡ በራት ግብዣው ላይ የጆርጌ ፍልቅልቅ አቀራረብ ምሽቱን አደመቀው፡፡ ዦርጌ ከእናቱ ዶሎሬስ ጋር በጥሞና ሲወያይ፣ የቢዝነስ ሸሪኩ ደግሞ ሮናልዶን በወሬ ጠመደው፡፡ ምግቡ ሲያበቃ ዦርጌ ለሸሪኩ የመጡበት ዓላማ መሳካቱን አበሰረለት፡፡ ‹‹ክሪስቲያኖ ደንበኛችን ሆኗል›› አለው፡፡ ልጅዋ ወኪል እንዲቀይር ዶሎሬስን ማግባባት ተቻለ፡፡ * በአዲሱ የውድድር ዘመን እንደገባ፣ በሴፕቴምበር 2002 የክሪስቲያኖ እና የእናቱ ፊርማ ያረፈበት የፋክስ መልዕክት በጆዜ ቬይጋ ኤጀንሲ ቢሮ ደረሰ፡፡ ወኪሉ በመካከላቸው ያለውን የኮንትራት ግንኙነት ለማሻሻል ፍላጎት ማጣት ስለተስዋለበት የኤጀንትነቱ ኮንትራት እንደማይታደስ መልዕክቱ ያረጋግጣል፡፡ ከፋክሱ መልዕክት በኋላ ሜንዴዝ በሮናልዶ ዙሪያ ያለውን ሁሉ የማስተዳደሩን ስልጣን ተረከበ፡፡ ከጆዜ ቬይጋ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ሮናልዶ ከአዲሱ ኤጀንቱ ጋር በጥልቀት መከረ፡፡ በሜንዴዝ አይኖች ውስጥ ሃቀኝነትን ተመለከተ፡፡ አመነው፡፡ ስለእኔ ይጨነቅልኛል ብሎ የሚተማመንበት ሰው ሆነለት፡፡ ሁለተኛ አባት አገኘ፡፡ የሜንዴዝ ነገር ለእናት ዶሎሬስም ትርጉሙ ተለየ፡፡ እናትና ልጅ ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው ሜንዴዝ አለሁ ባይ፣ ፈጥኖ ደራሽ ሆነ፡፡ የቤተሰቧ አንድ አካል የሆነላት ዶሎሬስ ጓደኛ፣ ከጓደኛም በላይ አደረገችው፡፡ ሜንዴዝ ጓዳቸውን የሚያውቅ፣ ገመናቸውን የሚረዳ ቤተኛ ሆነላቸው፡፡ ለወጣቱ ተስፈኛ እግር ኳስ ተጨዋች ቤተሰብ ታመነለት፣ እነርሱም ከልብ አመኑት፡፡ ሜንዴዝ አባትም፣ ጓደኛም፣ ወኪልም ሆኖ ከሮናልዶ ቤተሰብ ጋር ይበልጥ መቅረቡን ቀጠለ፡፡ ክሪስቲያኖ ከእኩዮቹ በታች እንዳይሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ያሟላለታል፡፡ የሚጠይቀውን ይመልስለታል፡፡ ህይወቱ ዋልታ ሆነለት፡፡ ዕድሜው ገና ከጉርምስና ሳይወጣ መኖሪያ አፓርትመንት ገዛለት፡፡ እንደ ታላቅ ወንድም ይገስጸዋል፡፡ ያድግ ዘንድ ይቆጣዋል፡፡ ሜንዴዝ በሮናልዶ ሃዘን ጊዜ አብሮት አልቅሷል፡፡ በደስታውም ጊዜ በአንድ ላይ ፈንድቋል፡፡ ሌሎች እኩያ ደንበኞቹን እስከሚያስከፋ ድረስ ሜንዴዝ ለሮናልዶ በጣም ቅርብ ሆነ፡፡ * ፕሮፌሽናል ኮንትራቱን ፈርሞ ሜንዴዝን በወኪልነት ከቀጠረ በኋላ ክሪስቲያኖ የታላቅነቱን ጉዞ አውራ ጎዳና ተያያዘው፡፡ የስፖርቲንግ አሰልጣኝ ቦሎኒ በጃርዴል መልቀቅና ክለቡም ተተኪ ተጫዋች እንደማይገዛ ሲያውቁ ጎረምሳውን ሮናልዶ ለመጠቀም ተገደዱ፡፡ በቅድሚያ ሮናልዶ የወደፊቱ እንጂ የዛሬው ተጫዋች አለመሆኑን ቢያምኑም፣ የቡድኑ ተጠባባቂ ቡድን አሰልጣኝ አሁኑኑ እንዲጠቀሙበት አግባባቸው፡፡ ‹‹አዎን! ገና 17 ዓመቱ ነው›› አለ ፍሬይታስ፡፡ ነገር ግን ‹‹ከሮማኒያ ወይም ከቡልጋሪያ የመጣ ተጫዋች ቢሆን ኖሮ እንደዚያ ትል ነበር?›› ለዚህ ጥያቄ ቦሎኒ አሳማኝ መልስ አልነበራቸውም፡፡ ጥቂት ካመነቱ በኋላ ሮናልዶን በስፖርቲንግ ሊዝበን ዋናው ቡድን ውስጥ ሊጠቀሙበት ወሰኑ፡፡ በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ጨዋታዎች ላይ የማዴይራው ልጅ ተሞከረ፡፡ በበርካታ የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ታየ፡፡ ከፓሪ-ሰን-ዠርመ ጋር ለአንድ ሰዓት ተጫወተ፡፡ በአካዳሚ ቆይታው በፊት አጥቂነትና በተደራቢ አጥቂነት የሚቻል አልነበረም፡፡ በዋናው ቡድን ግን አብዶኛ የክንፍ ተጫዋች ሆኖ መጣ፡፡ ክንፍ ክንፉን እየበረረ፣ በቴክኒካዊ ተሰጥኦው ተመልካቹን ሁሉ እያስደመመ አዲስ አብሪ ኮከብ ሆነ፡፡ ቦሎኒ ተገረሙ፡፡ ክሪስቲያኖ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሁለት ዓመት ዕድገትና እመርታ ያሳየ ተጫዋች መሆኑን አመኑ፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት በብዙ እጥፍ ተሰጥኦውን ሲያጎለብት መቆየቱና ዕድገቱም ፈጣን መሆኑ ገባቸው፡፡ ከዚያ በኋላ በዝግጅት ጨዋታዎች ላይ ያሳየውን አስገራሚ ተሰጥኦ በዋናው ቡድን የነጥብ ፍልሚያ ላይ አይደግምም የሚል ጥርጣሬ አልገባቸውም፡፡ ተማመኑበት፡፡ ለሌሎች እኩዮቹ ቢሆን ኖሮ የማያሳልፉትን ውሳኔ ለእርሱ ወስነው ወደ ፍልሚያው ሪንግ አስገቡት፡፡ በውስጥ እምነታቸው ብቻ ሳይበቁ በጋዜጣዊ መግለጫ አደባባይ ላይ አንደበታቸውም በይፋ መሰከረ፡፡ ‹‹ታያላችሁ!... ከዩዞቢዮም ሆነ ከሉዊስ ፊጎ የላቀ ተጫዋች ይሆናል!›› በማለት በፖርቱጋል ጋዜጠኞች ፊት ታላቁን ትንቢት ተናገሩ፡፡ ሮናልዶ በዋናው ቡድን ተቀባይነት ያገኘ ተጫዋች ሆነ፡፡ የቡድኑ ተጫዋቾች ቦታው እዚያ እንደሆነ አምነው ተቀበሉት፡፡ እርሱም ገና በማለዳው ለራሱ የሚሰጠውን ከፍ ያለ ግምት ያሳያቸው ያዘ፡፡ ከትልቁ ጎል አስቆጣሪ ጃርዴል ይበልጥ እንደሚዘል በመናገር ጉራውን ይነፋ ጀመር፡፡ የተጫዋችነት ህይወቱን ከጃርዴል ጋር እያነጻጸረ፣ የግል ህይወቱንም ከጃርዴል ቤተሰብ ጋር አስተሳሰረ፡፡ ክሪስቲያኖ ዕድሜው ደርሶ በራስ መተማመኑ ሲጎለብት ለመጀመሪያ ጊዜ ከጃርዴል እህት ጆርዳና ጋር በፍቅር ወደቀ፡፡ የዝግጅት ጨዋታዎች ቀጠሉ፡፡ ከሊዮን ጋር ከተጫወቱ በኋላ የአድናቆት ቅጽል ተመረጠለት፡፡ በችሎታው ተደምሞ ለጠየቀው የፖርቱጋል ሚድያ ክሪስቲያኖ ልባምነቱን ገልጾ አሳየ፡፡ ‹‹ገና ምን አያችሁና! ሰዎች እውነተኛውን ሮናልዶ መች ተመለከቱና! ይህ ገና መጀመሩ ነው›› እያለ ሲናገር በራስ መተማመኑ አስገራሚ ነበር፡፡ ኦገስት 3 ቀን በሌላ የከፍታ ማማ ላይ ወጣ፡፡ ተጋጣሚው ሪያል ቤቲስ ነበር፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ውጤቱ 2-2 ሳለ ሮናልዶ ተቀይሮ ገባ፡፡…. (ይቀጥላል)
2019/08/15 13:41
ባየር ሙኒክ ኢቫን ፔሪሲችን በአንድ አመት የውሰት ውል ማስፈረሙን አስታወቀ፡፡
2019/08/13 15:02
✍OFFICIAL፦ኢላኪዩም ማንጋላ በነፃ ዝውውር ማን ሲቲን ለቆ ቫሌንሲያን ተቀላቅሏል።
2019/08/13 09:05
ጁዤንቱስ ከክለቡ የሚለቁ 7 ተጫዋቾችን ይፋ አርጓ - Dybala - Manzukich - HIguain - Rugani - Matudi - Perin - Pyatsa
2019/08/13 09:05
🤝(DEAL DONE) ባየርን ሙኒክ ክሮሺያዊዉን የኢንተር ሚላን መስመር ተመላላሽ Ivan Perisic በ £5 Million የዉሰት ዉል ወማስፈረም ከስምምነት ደረሰ ተጨዋቹም የጤና ምርመራዉን ለማከናወን በ 24 ሰአታት ዉስጥ ጀርመን ይደርሣል።
2019/08/11 10:34
🤝(DEAL CLOSE) ሪያል ማድሪድ Donny Van De Beek ለማስፈረም ከአያክስ አምስተርዳም ጋር የመጨረሻ ስምምነቱን ተፈራርሞ ዝዉዉሩን አጠናቀቀ ማድሪድ ለ 22 አመቱ ተጨዋች £55 Million ወጪ ያደርጋል።
2019/08/11 10:34
👉ትላንት በ➊ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤት፦ ✅ተጠናቀቀ ☑️ዌስትሀም 0-5 ማን.ሲቲ ✅ተጠናቀቀ ☑️በርንማውዝ 1-1 ሼፊልድ ✅ተጠናቀቀ ☑️ዋትፎርድ 0-3 ብራይተን ✅ተጠናቀቀ ☑️በርንሌይ 3-0 ሳውዛምፕተን ✅ተጠናቀቀ ☑️ክርስታል ፖላስ 0-0 ኤቨርተን ✅ተጠናቀቀ ☑️ቶተንሀም 3-1 አስቶንቪላ 🔰 #ዛሬ_የሚደረጉ🔰 📅እሁድ ነሐሴ ➎ ⏰10:00 ☑️ኒውካስተትል 🆚 አርሰናል ⏰10:00 ☑️ሌሲስተር 🆚 ወልቭስ #የሳምንቱ_ታላቅ_ጨዋታ ⏰12:30 ☑️ማን.ዩናይትድ🆚ቼልሲ
2019/08/11 10:33
✅ቅዳሜ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ – Latest Transfer News Update! 👉ሮማ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እየተነጋገረ ነው የ 30 አመቱን ቺሊያዊ የፊት መስመር ተጫዋች አሌክሲስ ሳንቼዝን በአንድ አመት የውሰት ውል ለማስፈረም።(Telegraph) ═════════════════════════ 👉ፓሪሴንዥርመን የጁቬንቱሱን አርጀንቲናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ፖል ዲባላን ማስፈረም ይፈልጋሉ በመጨረሻው የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የዝውውር ቀን ወደ ቶተንሀም ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ሳይሳካ ከቀረ ቡኃላ።(Mail) ═════════════════════════ 👉ጁቬንቱስ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማስተካከል አሁንም ፖል ዲባላን ለመሸጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ ለመስማት ዝግጁ ናቸው ኢንተር ሚላን ሲቀር። የቱሪኑ ክለብ ይህን አርጀንቲናዊ ተጫዋች ለኢንተርሚላን በጭራሽ የመሸጥ ፍላጎት የላቸውም።(Calciomercato) ═════════════════════════ 👉አርሰናል ለ 27 አመቱ ጀርመናዊ ተከላካይ ሹኩርዳን ሙስጣፊ እና ለ 27 አመቱ አማካይ መሀመድ አሌኔኒ ከአውሮፓ ክለቦች የሚቀርብላቸውን ጥያቄ ለመስማት ዝግጁ ናቸው። (Evening Standard) ═════════════════════════ 👉ሮማ ከሊቨርፑል ጋር እየተወያዩ ነው £18.6m በማውጣት የ 30 አመቱን ክሮሺያዊ ተከላካይ ዲጄን ሎቭረን ለማስፈረም። (Football Italia) ═════════════════════════ 👉ሬያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ከፓሪሴንዥርመን የ 27 አመቱን የፊት መስመር ተጫዋች ኔይማርን ለማስፈረም ሁለትሙ የዝውውር ጦርነት ውስጥ ገብተዋል።(AS) ═════════════════════════ 👉ቸልሲ ለዚህ የዝውውር መስኮት £200m መድበው ነበር ተጫዋቾችን ለማዘዋወር የዝውውር እገዳ ሳይጣልባቸው በፊት። (Goal) ═════════════════════════ 👉ቸልሲ ለእንግሊዝ ከ 21 አመት በታች እየተጫወተ የሚገኘውን የ 21 አመቱን ተከላካዩን ፊካዮ ቶሞሪን አዲስ ኮንትራት ለማስፈረም አቅርበውለታል ኤቨርተን በውሰት ለመውሰድ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ካደረጉ ቡኃላ።(Goal) ═════════════════════════ 👉አርጀንቲናዊው የ 29 አመት ተከላካይ ማርኮስ ሮሆ በውሰት ኤቨርተን የመቀላቀል ፍላጎት ነበረው ነገር ግን ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በቁዋሚነት ብቻ የመሸጥ ፍላጎት ስለነበረው ነው ዝውውሩ ሳይሳካ የቀረው።(Liverpool Echo) ═════════════════════════ 👉ማንችስተር ዩናይትድ የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት የ 25 አመቱን ስፔናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ኢኛኪም ዊልያምን ለማስፈረም ሲያጤኑ ነበረር። (El Chiringuito, via Manchester Evening News) ═════════════════════════ 👉አይቬሪኮስታዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች ዊልፍሬድ ዛሀ በክሪስታል ፓላስ ቢያንስ እስከጥሩ የዝውውር መስኮት በማቆየት ከአውሮፓ ክለቦች ውጪ የመሸጥ ፍላጎት አላቸው የክለቡ ሀላፊ ስቴቨን ፓሪሽ እየተባለ ነው።(Express) ═════════════════════════ 👉የቀድሞ የአርሰናል እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ማርቲን ኪዮን የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ዋንጫ ቶተንሀም ሆስፐር ያሸንፋል ሲል ተናግሯል።(Talksport) ═════════════════════════ 👉የኤልኤ ጋላክሲው አጥቂ ዛላታን ኢብራሂምኦች በጠንካራ ቃላት የሜጀርሊግ ሶከርን አዲሱን የጥሎ ማለፍ ጫወታ ሲስተም ተችቱዋል።(ESPN) ═════════════════════════ 👉የ 28 አመቱ ቤልጄማዊ የፊት መስመር ተጫዋች ኤደን ሀዛርድ የሬያል ማድሪድ ሌጀንዶች ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ራውል ጎንዛሌዝ የለበሱትን 7 ቁጥር ማለያ እንደሚለብስ ተዘግቡዋል።(Mail) ═════════════════════════ 👉ባየርሙኒክ ከኢንተር ሚላን ጋር ከስምምነት ደርሱዋል ክሮሺያዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ኢቫን ፔሪሲችን በአንድ አመት የውሰት ውል ለማስፈረም እንደአማራጭም በቁዋሚነት በ €30m የማስፈረም መብት አላቸው በአመቱ መጨረሻ ተጫዋች የሚመቻቸው ከሆነ።(Source: BILD) ═════════════════════════ ⚠️DEAL DONE: አትላንታ ከፌነርባቼ ከለቀቀ ቡኃላ ክለብ አልባ የነበረውን የቀድሞ የሊቨርፑል ተከላካይ የሆነውን ማርቲን እስከርትልን በአንድ አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው አረጋግጠዋል።(Source: Atalanta Bergamasca Calcio ) ═════════════════════════ ⚠️DEAL DONE:የአርሰናል ኢላማ የነበረው ሞሮኩዋዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች ሀኪም ዚያችን በአያክስ እስከ 2022 የሚያቆየውን አዲስ የ 4 አመት ኮንትራት አስፈርመውታል።(Source: AFC Ajax ) ═════════════════════════ ⚠️DEAL DONE: ሉካ ሚሊዮቪች በክሪስታል ፓላስ እስከ 2023 የሚያቆየውን የ 4 አመት ኮንትራት ፈርሟል።(Source: Crystal Palace Football Club) ═════════════════════════ ▫️DEAL DONE:ሉካስ ሞራ በቶተንሀም እስከ 2024 የሚያቆየውን የ 5 አመት ኮንትራት መፈረሙ ተረጋግጡዋል።(Source: Tottenham Hotspur ) ═════════════════════════ 👉ሮሚዮ ሉካኮ በኢንተር ሚላን የማውሮ ኢካርዲ 9 ቁጥር ማለያ ተሰቶታል።(Source: Inter ) ═════════════════════════ ⚠️DEAL DONE:ሺንጂ ካጋዋ ከቦርሲያዶርትመንድ በመልቀቅ የስፔን ሁለተኛው ዲቪዚዮን ተሳታፊ ወደሆነው ሬያል ዛራጎዛል በሁለት አመት ኮንትራት ተቀላቅሉዋል።(Source: Real Zaragoza ) ═════════════════════════ ⚠️DEAL DONE:ኢካይ ጉንዱጋን በማንችስተር ሲቲ እስከ 2023 የሚያቆየውን የ 5 አመት ኮንትራት መፈረሙ ተረጋግጡዋል።(Source: Manchester City ) ═════════════════════════ 👉ባለፈው ግንቦት በልብ ህመም ምክንያት በልምምድ ሜዳ ፌንት ሰርቶ የነበረው የ 38 አመቱ ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ኢከር ካሲያስ ከእግርኩዋስ ይገለላል ቢባልም ፖርቶ ለአዲሱ ሲዝን እንዳስመዘገበው ተነግሯል። (ESPN) ═════════════════════════ 👉አሊሰን ቤከር ሊቨርፑል በሱፐር ካፕ ቸልሲ ረዕቡ ሲገጥሞ  ትላንትና ባስተናገደው ጉዳት እንደማይሰለፍ አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ ተናግረዋል። ═════════════════════════ 👉ነገ አርሰናል ኒውካስልን በሚገጥምበት ጫወታ ሚሱት ኦዚል እና ሲያድ ኮላሲናች ላይሰለፉ እንደሚችል ተገልፁዋል ባለፈው በደረሰባቸው የዝርፍያ ሙከራ ምክንያት ለደህንነታቸው ሲባል። ═════════════════════════
2019/08/10 15:28
ዛሬ የሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች 📅ቅዳሜ ነሐሴ 4 ⏰8:30 ዌስትሃም ከ ማን.ሲቲ ⏰11:00 በርንማውዝ ከ ሼፊልድ ⏰11:00 ዋትፎርድ ከ ብራይተን ⏰11:00 በርንሌይ ከ ሳውዝሃምፕተን ⏰11:00 ክሪ.ፖላስ ከ ኤቨርተን ⏰01:30 ቶተንሃም ከ አስቶንቪላ
2019/08/10 15:25
🧤የአውሮፓ ሻምፒዮኑ አሊሰን ቤከር ጉዳት አስተናግዶ በ39ነኛው ደቂቃ በአድሪያን ተቀይሮ ከሜዳ ተወጥቷል። በርካታ የሊቨርፑል ደጋፊዎች በሶሻል ሚዲያ ጉዳቱ ቀላል እንዲሆን እየተመኙ ይገኛሉ።
2019/08/10 11:15
✔ ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት አመሻሹን ጅማሮውን ሲያደርግ አንፊልድ ደግም የመክፈቻውን ድግስ በስኬት ጀምሯል። ቀዮቹ አዲስ መጭውን ኖርዊች ያለ ርህራሄ ❹ -❶ አሸንፈው ሸኝተውታል። መሀመድ ሳላህ ፣ ቫን ዳይክ እና ዲቦክ ኦርጊ ኳስና መረብን ያገናኙ የየርገን ክሎፕ ልጆች ናቸው። #ሊቨርፑል 4-1 # ኖርዊች (ተጠናቀቀ) ኦሪጊ በሊቨርፑል 100ኛ ጫወታውን በጎል አክብሯል ኖርዊች በፕ.ሊግ በብዛት የተሸነፈው በሊቨርፑል ነው ቀዮቹ በአንፊልድ ከተሸነፉ 838 ቀናት አልፈዋል አርኖልድ ለ4 አመታት በፕ.ሊጉ ያልታየ ሪከርድን ፅፏል ኩባዎች በፕ.ሊጉ ለመጀመሪያ ግዜ ተወካይ አግኝተዋል ሊቨርፑል ለ13 አመታት በፕ.ሊጉ ያልታየ ሪከርድን ፅፏል ይህ ግንኙነት በርካታ ጎል በማስተናገድ ሪከርድ ሆኗል ለቀዮቹ ሳላህ ፣ ኦሪጊና ቫንዳይክ አስቆጥረዋል የመክፈቻ ጎል በራስ መረብ ላይ ሲቆጠር ለ2ኛ ግዜ ነው አሊሰን ቤከር በጉዳት ጫወታውን ሳይጨርስ ወጥቷል። 👉ባለፉት 4 ተከታታይ ሲዝኖች በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 5 ተከታታይ ጫወታዎች ላይ ጎል የሆነ ኳስን ማቀበል የቻለው ተጫዋች አሌክሳንደር አርኖልድ ብቻ ሆኗል። ለመጨረሻ ግዜ ይህን ማድረግ የቻለው ሜሱት ኦዚል ሲሆን ግዜው በ2015 ነበር። 👉በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ የሲዝኑ የመክፈቻ ጫወታ ላይ የመጀመሪያው ጎል በራስ መረብ ላይ ሲቆጠር ለሁለተኛ ግዜ ነው። በ2015-16 ሲዝን የቶተንሃሙ ኬይል ዎከር ለማንችስተር ዩናይትድ ያስቆጠረበት ሌላኛው አጋጣሚ ነበር። 👉ከዚህ ጫወታ በፊት ለመጨረሻ ግዜ በፕሪምየር ሊጉ የመክፈቻ ጫወታ ከእረፍት በፊት 4 ጎል ማስቆጠር የቻለ ቡድን የታየው ከ13 አመት በፊት ሲሆን ቡድኑ ማንችስተር ዩናይትድ ነበር። ዛሬ ሊቨርፑል ይህን ማድረግ ችሏል። 👉ኖርዊች ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ የተሳትፎ ታሪኩ እንደ ሊቨርፑል በርካታ ግዜ ያሸነፈው ክለብ የለም (12 ግዜ) እንዲሁም በርካታ ጎል ያስቆጠረበት ክለብም ሊቨርፑል ነው። (49 ጎል) 👉ይህን ያውቃሉ? ሊቨርፑል በፕሪምየር ሊጉ አንፊልድ ላይ ለመጨረሻ ግዜ ከተሸነፈ 838 ቀናት አልፈዋል። ከዛ በኋላ 41 ጫወታ ላይ አልተሸነፈም። 31 አሸንፎ 10 አቻ ወጥቶ 107 ጎል አስቆጥሮ 21 ጎል ብቻ ተቆጥሮበታል ለመጨረሻ ግዜ የተሸነፈው በሳም አላርዳይሱ ክሪስታል ፓላስ ሲሆን ግዜው በአፕሪል 23-3017 ነበር። DWWWDDWWDDDWWWD WWWWDWWWWDWWWWWW 👉በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከ10 ግዜ በላይ ከተገናኙ ክለቦች ውስጥ በርካታ ጎል በማስተናገድ የሊቨርፑልና ኖርዊች ግንኙነት በሪከርድነት ተመዝግቧል። (በ16 ጫወታ 68 ጎል የተቆጠረበት ሲሆን በአማካይ በጫወታ 4 ጎል) 👉በዚህ ጫወታ ላይ ቀዮቹ 2 ጎል በጭንቅላት አስቆጥረዋል። ካለፈው ሲዝን ጀምሮም ከየትኛውም የፕሪምየር ሊግ ቡድን በላይ 21 የጭንቅላት ጎል ያስቆጠሩ ሲሆን ከተከታዩ ክለብ ቢያንስ በ7 ጎል ይበልጣሉ። 👉የኖርዊች ሲቲው ኦኔል ሄርናንዴዝ በፕሪምየር ሊግ ኩባን የወከለ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ስሙን ያስመዘገበ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ ታሪክም 114 የተለያዩ ሃገራት ተጫዋቾች ታይተውበታል። 👉ሞሐመድ ሳላህ ወደ ሊቨርፑል ከመጣ በኋላ 12 የፕሪምየር ሊግ ጫወታዎች ላይ ጎል በማስቆጠርና ለጓደኞቹ አመቻችቶ በማቀበል ቀዳሚ ሲሆን በአውሮፓ 5ቱ ታላላቅ ሊጎች ውስጥም የሚበለጠው በኔይማር ብቻ ነው። 👉እውነታ:- ኖርዊች ሲቲ ባለፈው ሲዝን በሻምፒየንስ ሺፑ ከሜዳው ውጪ አነስተኛ ጎል ያስተናገደ ቡድን ሆኖ የጨረሰ ሲሆን አሁን ግን ገና በመክፈቻ የፕሪምየር ሊግ ጫወታው ከእረፍት በፊት በቀዮቹ በተቆጠሩበት 4 ጎሎች ተሸንፎ ወጥቷል። ✅ ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬም ሲቀጥል ቀን 8:30 ላይ ዌስትሀም ከማንቸስተር ሲቲ በለንደን ስታዲየም ጠንካራውን ጨዋታ ያከናውናሉ። ማኑኤል ፔሌግሪኒ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው የሚገጥም ሲሆን ውሀ ሰማያዎቹ አጀማመራቸውን ለማሳመር ወደ ሜዳ ይገባሉ። መዶሻዎቹ ደግም ተፎካካሪ ሆነው ለመቆየት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። --------------------------------------------- ----------------------------- 🔼ሴባስቲያን ሀለር ከሰርጅዮ አጉዌሮ 🔼ፊሊፔ ንደርሰን ከራሂም ስተርሊንግ 🔼አንቶኒዮ ከበርናንዶ ሲልቫ 🔼ማኑኤል ፔሌግሪኒ ከፔፕ ጋርዲዮላ 🔼 መዶሻዎቹ ከውሀ ሰማያዎቸቹ
2019/08/10 10:18
ሊዮ ሜሲ ሊቨርፑል ላይ ያስቆጠራት የቅጣት ምት ጎል የ2018/19 የውድድር ዓመት ምርጥ ጎል ተብላ ተመርጣለች። ✔️
2019/08/09 18:18
የሜሲ ወላጆች ልፋት (ክፍል 4) ‹‹ሊዮ ታላቅ ተስፋ ያለው ልጅ ስለሆነ መርዳት እንፈልጋለን…›› ካሉ በኋላ ፕሬዚዳንቱ ከወንበራቸው ተነስተው በጠረጴዛው ማዕዘን ላይ መቀመጫቸውን አሳረፉ፡፡ የክለቡን ውሳኔ ሊነግሯቸዉ ሲዘጋጁ የሊዮ ወላጆች ከተቀመጡበት ወንበር ወደኋላ ገፋ ብለው ከፕሬዚዳንቱ አንደበት የሚወጣውን ለመስማት በጉጉት ስሜት ውስጥ ተዋጡ፡፡ ሴሊያ ቀድሞም የያዘችውን የባለቤቷን እጅ ይበልጥ ጥብቅ አድርጋ ተጫነችው፡፡ ‹‹እንዲህ እናድርጋ..›› አሉ ፕሬዚዳንቱ ቁርጠኛ ምላሻቸውን ለመስጠት እየተዘጋጁ፡፡ ‹‹የወጪውን ግማሽ መሸፈን ከቻላችሁ የተቀረውን ግማሽ ኒዌልስ ሊከፍል ዝግጁ ነው›› ሲሉ የሴሊያ ዕጢ ዱብ አለ፡፡ ለቅጽበትም ቢሆን የተሰማት የተስፋ ስሜት ቦታውን ለጭንቀት ትቶ በነነ፡፡ ‹‹ግማሽ?›› አለች ሴሊያ፡፡ በምናቧ ስታሰላው ክለቡ ከሁለት መርፌዎቹ ለአንዱ የሚከፍለው በወር 500 ዶላር መሆኑን ተረዳች፡፡ ቃል ሳትተነፍስ ባለቤቷ ለክለቡ ፕሬዚዳንት ፈጠን ያለ መልስ ሰጠ፡፡ ‹‹እሺ! ይሁን እንቀበላለን ጌታዬ!›› በማለት እጅ ነሳ፡፡ ከተጨባበጡ በኋላ ዝርዝር ጉዳዮችን እንደሚያሳውቋቸው፣ በቅርቡም የክፍያ ቼክ እንዲጠብቁ ፕሬዚዳንቱ ቃል ገብተውላቸው ተሰነባበቱ፡፡ የኒዌልስ ፕሬዚዳንት እንዳሉት የሊዮ የህክምና ከፊል ወጪ የሚሸፈንበት ክፍያ ቼክ ወደእነሜሲ ቤት ይመጣ ጀመር፡፡ ለተከታታይ የክፍያ ቀናት መከፈሉ ቢቀጥልም አልዘለቀም፡፡ በመጀመሪያ ቼኩ ሲዘገይ ሆርጌና ሴሊያ እምብዛም አልተጨነቁም ነበር፡፡ በኋላ የቼኩ ነገር የውሃ ሽታ እየሆነ ሄዶ ከዚያም ከእነጭራሹኑ ቆመ፡፡ የክፍያው ምንጭ ሲነጥፍ በሜሲ ቤት ቀውስ ገባ፡፡ * የቤታቸው የምግብ ጠረጴዛ የሆርጌና ሴሊያ የብሶት መተንፈሻ አደባባይ ነው፡፡ በምሳም ይሁን በራት ሰዓት፣ ምግቡ ከተበላ በኋላ የችግር ዶሴዎች እየተከፈቱ መፍትሔ ይፈልጉለታል፡፡ ከኒዌልስ ክፍያ መቅረት በኋላም በድጋሚ የማዕድ ዙሪያው አጀንዳ የሊዮ የሆርሞን ህክምና ሆነ፡፡ በዚያም ቀን ውይይታቸው የታዳጊ ልጆቻቸውን ቀልብ ስቦ በህጻናቱ መኝታ ቤት በር በኩል ይሰማ ነበር፡፡ ሆርጌ መፍትሔ ነው ያለውን ለባለቤቱ አጫወታት፡፡ ‹‹ኒዌልስ ኦልድ ቦይስ ወጪውን የማይሸፍን ከሆነ፣ የህክምና ክፍያውን የሚከፍልልንን ሌላ ክለብ እንፈልጋለን›› ሲል ቁርጠኝነቱን በድጋሚ አረጋገጠላት፡፡ ሆርጌና ሴሊያ ያሉ አማራጮችን ሁሉ እስከ እንጥፍጣፊው ድረስ ሊጠቀሙ ቆረጡ፡፡ በመጨረሻ ሊዮ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች እንደሚሆን አባቱ እርግጠኛ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን የሆርሞኑ መርፌ ጉዳይ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡ እዚያ መፍትሔ አለ ከተባለ የማይገባበት ጉድጓድ እንደማይኖር ሰውየው ቆርጧል፡፡ በዚያች ምሽት ሴሊያ የሊዮና የአባቱን አነስተኛ ሻንጣ ሸክፋ አዘጋጀችላቸው፡፡ በማግስቱ ጠዋት አባትና ልጁ ወደ ዋና ከተማዋ ቡዌኖስ አይረስ ተጓዙ፡፡ * አውቶቡሱ መነሳት ካለበት አምስት ደቂቃ ያህል ዘግይቷል፡፡ ለጉዞ በሚሆን መልኩ ለብሰው ሊዮና አባቱ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በሚወስደው መንገድ መጨረሻ ጫፍ ላይ ቆመዋል፡፡ የአራት ሰዓት ጉዞ ይጠብቃቸዋል፡፡ አውቶቡሱ እርጅና ተጭኖት በአንድ በኩል የመስኮቱ መስተዋት ግማሽ ተሰብሯል፡፡ ሊዮ ሊዘጋው ቢታገል አልንቀሳቀስልህ አለው፡፡ ወንበሮቹ በቢጫ፣ ግራጫማና ብርቱካናማ ፕላስተሮች ለጥገና ተለጣጥፈዋል፡፡ ለግማሽ ሰዓት ያህል በአውራ ጎዳናው ጉዟቸው በራሪው ንፋስ ወደ ውስጥ እየገባ ጆሮ ግንዳቸው ስር አፏጨ፡፡ በመጨረሻ ሆርጌ ኮቱን አውልቆ ያለመስተዋት በቀረው መስኮት በኩል የሚገባውን ንፋስ ጋርዶ አቆመው፡፡ ቡዌኖስ አይረስ በጤዛ ተሸፍና ጠበቀቻቸው፡፡ የወረዱበት አውቶቡስ ተራ ከሪቨር ፕሌት ስታዲየም ብዙም አይርቅም፡፡ በከተማዋ ትልቁ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ስፍራ አለ ከተባለ ይኼው የሪቨር ስታዲየም ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው፡፡ ካሉበት ቦታ አንስቶ ሪቨር ስታዲየም የሚያደርሳቸውን ታክሲ ተሳፈሩ፡፡ ታክሲው ወደ ስታዲየሙ እየተቃረበ ሲመጣ ሊዮ ፊቱን በመስተዋቱ በኩል አዙሮ በአትኩሮት ተመለከተ፡፡ ጋብርኤል ባቲስቱታ እና ሄርናን ክሬስፖ ውብ ጎሎችን እያስቆጠሩ ደጋፊዎችን ባስጨፈሩበት ስታዲየም ለክለብ አትሌቲኮ ሪቨር ፕሌት ቢጫወት ምን ያህል ደስ ባለው! ሆርጌ የልጁ ሃሳብ ስለገባው ትከሻውን መታ መታ በማድረግ ‹‹አይዞህ! የምትጫወትበት ስታዲየም የምታገኝበት ቀን ቀርቧል›› አለው፡፡ ይህን የሰማው የታክሲ ሾፌር ‹‹የሪቨር ደጋፊዎች ናችሁ?›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ከድንገተኛው ጥያቄ በኋላ ሊዮና አባቱ ዓይን ለዓይን ተያዩ፡፡ ‹‹አይ የሮዛሪዮ ሰዎች ነን›› ሆርጌ መለሰለት፡፡ ‹‹ሃሃሃ…. የሌፐርስ ደጋፊዎች ናችኋ!? ሁልጊዜ የሚሸነፉ….፣ ኧረ ኤዲያ እነርሱስ!…›› ሆርጌ ከማያውቀው ሰው ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት አልፈለገም፡፡ ‹‹ቤተሰቤን ለባዕድ ሰው አምቼ አላውቅም፡፡ ሃሜት አልወድም›› ካለ በኋላ ሁለቱም ሰዎች እኩል ተሳሳቁ፡፡ *** ሊዮ እንዲህ የሚመች የመጫወቻ ሜዳ አይቶ አያውቅም፡፡ ሳሩ ፍጹም አረንጓዴ ሲሆን በልኩ ተከርክሞ ታጭዷል፡፡ የሜዳ መስመሮቹ አልፈዘዙም፡፡ የጎሉ መረቦችም አዲስ ናቸው፡፡ ሊዮ በበሩ በኩል ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ፈነደቀ፡፡ በሜዳው መሃል እኩዮቹ የሚሆኑ ልጆች ተደርድረው ተመለከተ፡፡ እንደ እርሱ ሁሉ ለሙከራ የተዘጋጁ ነበሩ፡፡ ከቆሙት ከመጨረሻው ልጅ ጀርባ በመሰለፍ ታዳጊዎቹን ተቀላቀለ፡፡ ሆርጌ ለልጁ ቅርብ መሆን ቢፈልግም ከሽቦው አጥር በስተጀርባ መጠበቅ ነበረበት፡፡ ፊቱን በሽቦው ላይ ለጥፎ የሊዮን የሙከራ ፈተና መመልከት ጀመረ፡፡ ትልልቅ የወረቀት ቁጥሮች በሙከራ ላይ በሚገኙት ታዳጊዎች ማሊያ ላይ ተለጥፈዋል፡፡ በሁለት ቡድኖች ለይተዋቸውና ቢጫና ቀይ አልብሰዋቸው አጫወቷቸው፡፡ ወደ 70 የሚጠጉ ህጻናት በክለቡ ለመመልመል ይሞክራሉ፡፡ እያንዳንዱ ተጫዋች ተሰጥኦውን ያሳይ ዘንድ የአምስት ደቂቃ ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ከተጫዋቾች ሁሉ የላቀ ባለተሰጥኦ ከተገኘ ደግሞ 10 ደቂቃ ያገኛል፡፡ ሊዮ በትዕግስት ጠበቀ፡፡ ብዙ ጠበቀ፡፡ ወደ ሜዳ ገብቶ ኳስ ለመንካት ተቻኩሎ ሳለ እርሱና ሌሎች ጥቂት ታዳጊዎች ተራቸው ደርሶ በአሰልጣኙ ተጠሩ፡፡ ሆርጌ ራቅ ብሎ ከቆመበት ሊዮ ወደ ታዳጊዎቹ ይበልጥ ተጠግቶ በነጻነት እንዲጫወት እጁን እያወራጨ አበረታታው፡፡ ሊዮም ቀና ብሎ ወደ አባቱ ከተመለከተ በኋላ የሙከራ ጨዋታው ተጀመረ፡፡… (ይቀጥላል)
2019/08/09 15:15
✅​​የዛሬዉን መክፈቻ ጨዋታ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ። ​​🔴ሊቨርፑል 🆚 ኖርዊች ሲቲ🌕 ▫️የእንግሊዝ ክለቦች ዝውውር መስኮት ተዘግቷል፡፡ በዝውውር መስኮቱ ብዙም እንቅስቃሴ ያላደረገው እና ያለፈውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በአንድ ነጥብ ብቻ ያጣው ሊቨርፑል አዲስ አዳጊዎችን አንፊልድ ላይ በማስተናገድ አመቱን ይጀምራል፡፡ እያንዳንዱ ነጥብ ወሳኝ በሆነው የፕሪሚር ሊግ ውድድርን ሊቨርፑሎች በድል ለመጀመር ተዘጋጅተዋል፡፡ ▫️ኖርዊቾች 3 አመታትን በታችኛው ዲቪዚዮን ከሳላፉ በኋላ ነው የተመለሱት፡፡ እንሱም ቢሆኑ ፕሪሚየር ሊጉን በመልካም ሁኔታ ለመጀመር እና ከአንፊልድ ነጥብ ይዘው ለመመለስ ይፋማሉ፡፡ 👉 የሁለቱ ቡድኖች እውነታ። ▫️ሊቨርፑል ከኖርዊች ጋር ባደረገው ያለፉት 12 ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡ 10 ጊዜ አሸንፎ 2 ጊዜ አቻ ወጥቷል፡፡ ▫️ኖርዊች ሊቨርፑልን ለመጨረሻ ጊዜ አንፊልድ ላይ ያሸነፈው በ1994 1 ለ 0 ነበር፡፡ ▫️ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት ያለፉት 6 ጨዋታዎች 34 ጎሎች ተቆጥረዋል፡፡ ▫️ሊቨርፑል ከዚህ በፊት በመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኖርዊችን ያስተናገደው በ1976 ነበር፡፡ በጊዜው አንድ ለ 0 በማሸነፍ ውድድሩን ጀምሮ በመጨረሻም የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ ▫️ለመጨረሻ ጊዜ በ2016 ሲገኛኙ አንፊልድ ላይ አንድ አቻ ነበር የተለያዩት፡፡ ካሮው ሮድ ላይ በተደረገው ጨዋታ ግን 9 ጎሎች ተመዝግበዋል፡፡ ጨዋታውን ሊቨርፑል 5 ለ 4 ነበር ያሸነፈው፡፡ ሁለት ጎሎች የተቆጠሩት ደግሞ መደበኛው 90 ደቂቃ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡ ▫️ሊቨርፑሎች በሜዳቸው ያደረጉትን ያለፉት 40 ጨዋታ አልተሸነፉም፡፡ 30 አሸንፈው 10 ጊዜ አቻ ወጥተዋል፡፡ ▫️ከታች ካደጉ ክለቦች ጋር ባደረጉት ያለፉት 25 የአንፊልድ ጨዋታ አልተሸነፉም፡፡ 20 ጊዜ አሸንፈው 5 ጊዜ አቻ ወጥተዋል፡፡ ▫️የርገን ክሎፕ ካደጉ ቡድኖች ጋር ባደረገው ያለፉት 10 ጨዋታ በአስሩም ድልን አስመዝግቧል፡፡ ▫️ለመጨረሻ ጊዜ ሲገናኙ ሮበርት ፌርሚኖ 2 ጎሎችን አስቆጥሮ አንድ ደግሞ ለጎል የበቃ ኳስ አቃብሏል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ 50 ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው ብራዚላዊ ለመሆን 2 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል፡፡
2019/08/09 15:01
🗣 የናፖሊ ፕሬዝዳንት ኦሬልዮ ደ ላውራኒስ እንዲህ በማለት ሃሪ ማጔየርን ከካሊቱ ኮሉቢሊያ ጋር ያነፃፅራሉ- ለምሳሌ ፣ በእንግሊዝ ለአንድ ተጫዋች £ 85 ሚሊዮን ፓውንድ ይከፈለዋል ፡፡ በናፖሊዮ ውስጥ ግን ከ30-35 ሚሊዮን ፓውንድ እከፍላለሁ ፡፡ “ይህንን እንዳለ ይዘን ለዚያ ሰው ለማጔየር ይህንን ያህል ከከፈሉ ለኮሉቢሊያ 250 ሚሊዮን ፓውንድ መክፈል አለባቸው ብዬ አስባለሁ በማለት አስገራሚ አስተያየቱን ገልጿል::
2019/08/09 14:42
ዛሬ ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲጀመር ምሽት 4:00 ላይ ሊቨርፑል ከኖርዊች የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
2019/08/09 14:42
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ አማካዮች ስም ዝርዝር ፦ 👉 ጃርዳን ሄንደርሰን ከ ሊቨርፑል 👉 ፍሬንኪ ዲዮንግ ከ አያክስ 👉 ክርስቲያን ኤሪክሰን ከ ቶተንሀም
2019/08/09 09:29
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ ተከላካዮች ስም ዝርዝር ፦ 👉 አሌክሳንደር ትሬንት አርኖልድ ከ ሊቨርፑል 👉 ቨርጅል ቫንዳይክ ከ ሊቨርፑል 👉 ማቲያ ዲላይት ከ አያክስ
2019/08/09 09:29
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ በረኞች ስም ዝርዝር፦ 👉 አሊሰን ቤከር ከ ሊቨርፑል 👉 ቴሪስ ቴገን ከ ባርሴሎና 👉 ሁጎ ሎሪስ ከ ቶተንሀም
2019/08/09 09:29
ዛሬ ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲጀመር ምሽት 4:00 ላይ ሊቨርፑል ከኖርዊች የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
2019/08/09 09:29
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ አጥቂዎች ስም ዝርዝር ፦ 👉 ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ ጁቬንቱስ 👉 ሊዮኔል ሜሲ ከ ባርሴሎና 👉 ሳዲዮ ማኔ ከ ሊቨርፑል
2019/08/09 09:29
በዚሁ ❻ቱ ትልልቅ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ የነበራቸውን ተሳትፎ እንመልከት 👉አርሰናል 6 ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሎ 8 የሚደርሱ ተጫዋቾች ከኤምሬትስ ወጥተዋል። 👉ቸልሲ 2 ተጫዋቾችን በብሪጅ ሲያስፈርም 3 ተጫዋቾችን አጧል። 👉ማንቸስተር ሲቲ 5 ተጫዋቾችን ሲቀላቅል በአንጻሩ 4 ተጫዋቾችን አሰናብቷል። 👉ማንቸስተር ዩናይትድ 3 ተጫዋቾችን የኦልትራፎርድ ንብረት ሲያደርግ በተመሳሳይ 3 ተጫዋቾችን ግልጋሎት አጧል። 👉ቶትንሀም 3 ተጫዋቾችን ሲያስፈርም 3 ተጫዋቾችን ከክለቡ ተሰናብተዋል።
2019/08/09 09:29
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ አጥቂዎች ስም ዝርዝር ፦ 👉 ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ ጁቬንቱስ 👉 ሊዮኔል ሜሲ ከ ባርሴሎና 👉 ሳዲዮ ማኔ ከ ሊቨርፑል @Bisrat_Sport_Fm
2019/08/09 09:27
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ አማካዮች ስም ዝርዝር ፦ 👉 ጃርዳን ሄንደርሰን ከ ሊቨርፑል 👉 ፍሬንኪ ዲዮንግ ከ አያክስ 👉 ክርስቲያን ኤሪክሰን ከ ቶተንሀም @Bisrat_Sport_Fm
2019/08/09 09:27
በዚሁ ❻ቱ ትልልቅ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ የነበራቸውን ተሳትፎ እንመልከት 👉አርሰናል 6 ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሎ 8 የሚደርሱ ተጫዋቾች ከኤምሬትስ ወጥተዋል። 👉ቸልሲ 2 ተጫዋቾችን በብሪጅ ሲያስፈርም 3 ተጫዋቾችን አጧል። 👉ማንቸስተር ሲቲ 5 ተጫዋቾችን ሲቀላቅል በአንጻሩ 4 ተጫዋቾችን አሰናብቷል። 👉ማንቸስተር ዩናይትድ 3 ተጫዋቾችን የኦልትራፎርድ ንብረት ሲያደርግ በተመሳሳይ 3 ተጫዋቾችን ግልጋሎት አጧል። 👉ቶትንሀም 3 ተጫዋቾችን ሲያስፈርም 3 ተጫዋቾችን ከክለቡ ተሰናብተዋል። @Bisrat_Sport_Fm @Bisrat_Sport_Fm
2019/08/09 09:27
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ ተከላካዮች ስም ዝርዝር ፦ 👉 አሌክሳንደር ትሬንት አርኖልድ ከ ሊቨርፑል 👉 ቨርጅል ቫንዳይክ ከ ሊቨርፑል 👉 ማቲያ ዲላይት ከ አያክስ @Bisrat_Sport_Fm
2019/08/09 09:27
ዛሬ ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲጀመር ምሽት 4:00 ላይ ሊቨርፑል ከኖርዊች የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። @Bisrat_Sport_Fm
2019/08/09 09:27
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 3 ምርጥ በረኞች ስም ዝርዝር፦ 👉 አሊሰን ቤከር ከ ሊቨርፑል 👉 ቴሪስ ቴገን ከ ባርሴሎና 👉 ሁጎ ሎሪስ ከ ቶተንሀም @Bisrat_Sport_Fm
2019/08/09 09:27
🚨BRAKING NEWS ✍(OFFICAL) ናይጄሪያዊዉ የአርሰናል አጥቂ Alex Iwobi ከልጅነት ክለቡ አርሰናል ለቆ የመርሲሳይዱን ክለብ Everton በ £40 Million ተቀላቀለ።
2019/08/09 04:02
▫️አርሰናል በ OFFICAL ቲዉተር ገፁ ላይ ዳቪድ ሉዊስን ማስፈረሙን ይፋ አርጓል።
2019/08/09 04:02
👉ማንችስተር ዩናይትድ ሲፈልገዉ የከረመዉን ክሮሺያዊዉን የ33 አመት አጥቂ Mario Mandzukic ላይ ያለዉን ፍላጎት ገታ። (SKY SPORT)
2019/08/09 04:02
🚨Alex Iwobi|Medical አሌክስ አዬቢ ወደ ኤቨርተን የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የህክምና ምርመራውን ለንደን እያደረገ ይገነፈኛል ዝውውሩን በ£40 ሚሊየን ይጠናቀቃል ✍David Orenstein|BBC
2019/08/08 21:55
ኬራን ቴሪኒ OFFICIAL በአርሰናል ቤት ''3'' ቁጥር ማልያ ያደርጋል
2019/08/08 21:55
አርሰናል ኬራን ቴርኒን ከ ሴልቲክ በ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን አስታወቀ።
2019/08/08 21:52
በርንሌይ ዳኒ ድሪንክ ወተርን ከ ቼልሲ በ 6 ወር የውሰት ውል ማስፈረሙን አስታወቀ።
2019/08/08 21:52
በተጨማሪም የተጠናቀቁ ዝውውሮች DEAL DONE ዋትፎርድ በክለቡ ሪከርድ በሆነ ዋጋ €33ሚ በመክፈል ሴናጋላዊው የሬንሱ የክንፍ መስመር ተጫዋች Ismaila Sarr በይፋ አስፈርሟል። DEAL DONE Aaron Mooy በአንድ አመት የውሰት ውል Huddersfield ን በመልቀቅ Brighton ንን ተቀላቅሏል። DEAL DONE ብራይተን የፒኤስጂው ወጣት ተከላካይ Romaric Yapi ን አስፈርመዋል። DEAL DONE Romelu Lukaku ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቅ በይፋ ኢንተርን ተቀላቅሏል። DEAL DONE Charlie Austin ሳውዝአምፕተንን በመልቀቅ በ £4ሚ ዌስትብሮምን ተቀላቅሏል። የ 2 አመት ኮንትራትም ፈርሟል። DEAL DONE ኒውካስትል Emil Krafth ን ከ Amiens በ £5ሚ አስፈርሟል። የ 4 አመት ኮንትራትም ፈርሟል። DEAL DONE Eddie Nketiah በአንድ አመት የውሰት ውል አርሰናልን በመልቀቅ ሊድስ ዩናይትድን ተቀላቅሏል። DEAL DONE Nathan Redmond እስከ 2023 ጋር የሚያቆየው አዲስ ኮንትራት ከ ሳውዝአምፕተን ጋር ተፈራርሟል። DEAL DONE Aubamyang እና Lacaette ከአርሰናል ጋር የሚያቆያቸውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርመዋል።
2019/08/08 21:52
👉 ዋትፎርድ ኢብራሂም ሳርን ከ ሬንስ በክለቡ ሪከርድ ዋጋ(35 ሚሊዮን ዩሮ በ 5 ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታወቀ።
2019/08/08 21:52
. ሰበር ዜና ላካዜቲ እና ኦባምያንግ ኮንትራታቸውን አራዝመዋል። 👉 Lacazette እስከ 2022 👉 Aubamyang እስከ 2021
2019/08/08 21:52
👉የእንግሊዙ ኤቨርተን የሞናኮዉን መስመር ተመላላሽ Djibril Sidibe ለረጅም ግዜ የዉሰት ዉል አስፈረመ።
2019/08/08 21:52
👉የሊቨርፑሉ አጥቂ መሀመድ ሳላህ ካይሮ ለሚገኘው የናሽናል ካንሰር ኢንስቲቲዩት የ2.5 ሚ.ፓውንድ ገንዘብ እርዳታ አደረገ። ሳላህ ይህ እንርዳታ ያደረገው በአካባቢው በሽብር ጥቃት 20 የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸው ከተሰማ በኃላ ነው።
2019/08/08 21:52
የ #አውሮፖ_ሊግ የአመቱ ምርጥ 3 ተጫዋቾች ይፋ አደረገ። ቼልሲ #ሀዛርድ እና #ጅሩድን ሲያስመርጥ #ፍራንክፈርት ደሞ #ሉካ_ጆቪችን አስመርጦአል።
2019/08/08 21:48
በተጨማሪም የተጠናቀቁ ዝውውሮች ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE ዋትፎርድ በክለቡ ሪከርድ በሆነ ዋጋ €33ሚ በመክፈል ሴናጋላዊው የሬንሱ የክንፍ መስመር ተጫዋች Ismaila Sarr በይፋ አስፈርሟል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE Aaron Mooy በአንድ አመት የውሰት ውል Huddersfield ን በመልቀቅ Brighton ንን ተቀላቅሏል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE ብራይተን የፒኤስጂው ወጣት ተከላካይ Romaric Yapi ን አስፈርመዋል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE Romelu Lukaku ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቅ በይፋ ኢንተርን ተቀላቅሏል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE Charlie Austin ሳውዝአምፕተንን በመልቀቅ በ £4ሚ ዌስትብሮምን ተቀላቅሏል። የ 2 አመት ኮንትራትም ፈርሟል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE ኒውካስትል Emil Krafth ን ከ Amiens በ £5ሚ አስፈርሟል። የ 4 አመት ኮንትራትም ፈርሟል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE Eddie Nketiah በአንድ አመት የውሰት ውል አርሰናልን በመልቀቅ ሊድስ ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE Nathan Redmond እስከ 2023 ጋር የሚያቆየው አዲስ ኮንትራት ከ ሳውዝአምፕተን ጋር ተፈራርሟል። ═══════════════════════════ ✔️DEAL DONE Aubamyang እና Lacaette ከአርሰናል ጋር የሚያቆያቸውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርመዋል። ═══════════════════════════ ✔️ አርሰናል ኬራን ቴርኒን ከ ሴልቲክ በ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን አስታወቀ። ═══════════════════════════ ✔️ ቶትንሀም ሆትስፐር የ19 አመቱን የፉልሀሙን የግራ መስመር ተመላላሽ ሪያን_ሲሴኞንን በ25M£ በ5 አመት ውል ማስፈረሙን አረጋግጧል ! ═══════════════════════════ ♻️🙏🙏🙏🙏SHARE 🙏🙏🙏🙏♻️
2019/08/08 21:47
♨ Breaking news ♨ ✍ ቶትንሀም ሆትስፐር የ19 አመቱን የፉልሀሙን የግራ መስመር ተመላላሽ #ሪያን_ሲሴኞንን በ25M£ በ5 አመት ውል ማስፈረሙን አረጋግጧል ❗
2019/08/08 21:47
✍ በዚ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ስሙ ከአርሰናል ከኤቨርተን እና ከጀርመኑ ክለብ ባየርሙንሽን በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረው የክሪስታል ፓላሱ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሀ በመጨረሻም ክሪስታል ፓላሶች ከክለባቸው ለቆ ወዴትም እንደማይሄድ ዛሬ ከከሰአት ይፋ አድርገዋል (SKY)
2019/08/08 21:47
♨ BREAKING NEWS ♨ ✍ ቤልጂየማዊው የፊት መስመር አጥቂ "ሮሜሎ ሉካኩ" ማን ዩናይትድን በመልቀቅ በ 80M£ የጣልያኑን ክለብ ኢንተር ሚላንን መቀላቀሉን ብዙ የጣልያን ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ይገኛሉ ❗
2019/08/08 21:47
♨ BREAKING NEWS ♨ ✍ ቶትንሀም ሆትስፐር አርጀንቲናዊውን የሪያል ቤቲሱን የመሀል ሜዳ ኮከብ "ጂዮቫኒ ሎ ሴልሶን" በረጅም ጊዜ የውሰት ውል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ❗
2019/08/08 21:47
የዴቪድ ሉይዝ ዝውውር ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ለዝውውር ከ£5 እስከ £8 ሚሊየን ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል
2019/08/08 09:11
👉ታማኙ የስፖርት ማህደር Mirror ከደቂቃዎች በፊት ሰበር ዜና ብሎ ይጦት እንደወጣዉ መረጃ ከሆነ ሪያል ማድሪድ ኔይማርን ወደ በርናባዉ ለማስኮብለል Luca Modric እና £110 Million ማቅረቡን ገለፀ። (Mirror)
2019/08/08 09:09
👉ኤቨርተን ጂብሪል ሲዲቤን ከ ሞናኮ በአንድ ዓመት የውሰት ውል ከዛ በኋላ ከመግዛት መብት ጋር ማስፈረሙን አስታወቀ።
2019/08/08 09:09
🔥ትላንት ምሽት RB ሳልዝበርግን የገጠመዉ ሪያል ማድሪድ በ Eden Hazard ብቸኛጎል 1-0 ሲረታ Hazard በአዲሱ ክለቡ ማድሪድ የመጀመሪያዉን ጎል አስቆጥሯል።
2019/08/08 09:08
✍ጁቨንቱሶችም ከሲቲ የተሰጣቸውን ዳኒሎን ለ5 አመት ኮንትራት አስፈርመውታል።
2019/08/08 09:08
✍(OFFICIAL) ማንችስተር ሲቲ በ £30 Million እና በ Danilo ቅያሪ የጁቬንቱሱን ተጨዋች Joao Cancelo ለ 6 አመት ኮንትራት አስፈረመ።
2019/08/08 09:08
የሜሲ ወላጆች ልፋት (ክፍል 4) ‹‹ሊዮ ታላቅ ተስፋ ያለው ልጅ ስለሆነ መርዳት እንፈልጋለን…›› ካሉ በኋላ ፕሬዚዳንቱ ከወንበራቸው ተነስተው በጠረጴዛው ማዕዘን ላይ መቀመጫቸውን አሳረፉ፡፡ የክለቡን ውሳኔ ሊነግሯቸዉ ሲዘጋጁ የሊዮ ወላጆች ከተቀመጡበት ወንበር ወደኋላ ገፋ ብለው ከፕሬዚዳንቱ አንደበት የሚወጣውን ለመስማት በጉጉት ስሜት ውስጥ ተዋጡ፡፡ ሴሊያ ቀድሞም የያዘችውን የባለቤቷን እጅ ይበልጥ ጥብቅ አድርጋ ተጫነችው፡፡ ‹‹እንዲህ እናድርጋ..›› አሉ ፕሬዚዳንቱ ቁርጠኛ ምላሻቸውን ለመስጠት እየተዘጋጁ፡፡ ‹‹የወጪውን ግማሽ መሸፈን ከቻላችሁ የተቀረውን ግማሽ ኒዌልስ ሊከፍል ዝግጁ ነው›› ሲሉ የሴሊያ ዕጢ ዱብ አለ፡፡ ለቅጽበትም ቢሆን የተሰማት የተስፋ ስሜት ቦታውን ለጭንቀት ትቶ በነነ፡፡ ‹‹ግማሽ?›› አለች ሴሊያ፡፡ በምናቧ ስታሰላው ክለቡ ከሁለት መርፌዎቹ ለአንዱ የሚከፍለው በወር 500 ዶላር መሆኑን ተረዳች፡፡ ቃል ሳትተነፍስ ባለቤቷ ለክለቡ ፕሬዚዳንት ፈጠን ያለ መልስ ሰጠ፡፡ ‹‹እሺ! ይሁን እንቀበላለን ጌታዬ!›› በማለት እጅ ነሳ፡፡ ከተጨባበጡ በኋላ ዝርዝር ጉዳዮችን እንደሚያሳውቋቸው፣ በቅርቡም የክፍያ ቼክ እንዲጠብቁ ፕሬዚዳንቱ ቃል ገብተውላቸው ተሰነባበቱ፡፡ የኒዌልስ ፕሬዚዳንት እንዳሉት የሊዮ የህክምና ከፊል ወጪ የሚሸፈንበት ክፍያ ቼክ ወደእነሜሲ ቤት ይመጣ ጀመር፡፡ ለተከታታይ የክፍያ ቀናት መከፈሉ ቢቀጥልም አልዘለቀም፡፡ በመጀመሪያ ቼኩ ሲዘገይ ሆርጌና ሴሊያ እምብዛም አልተጨነቁም ነበር፡፡ በኋላ የቼኩ ነገር የውሃ ሽታ እየሆነ ሄዶ ከዚያም ከእነጭራሹኑ ቆመ፡፡ የክፍያው ምንጭ ሲነጥፍ በሜሲ ቤት ቀውስ ገባ፡፡ * የቤታቸው የምግብ ጠረጴዛ የሆርጌና ሴሊያ የብሶት መተንፈሻ አደባባይ ነው፡፡ በምሳም ይሁን በራት ሰዓት፣ ምግቡ ከተበላ በኋላ የችግር ዶሴዎች እየተከፈቱ መፍትሔ ይፈልጉለታል፡፡ ከኒዌልስ ክፍያ መቅረት በኋላም በድጋሚ የማዕድ ዙሪያው አጀንዳ የሊዮ የሆርሞን ህክምና ሆነ፡፡ በዚያም ቀን ውይይታቸው የታዳጊ ልጆቻቸውን ቀልብ ስቦ በህጻናቱ መኝታ ቤት በር በኩል ይሰማ ነበር፡፡ ሆርጌ መፍትሔ ነው ያለውን ለባለቤቱ አጫወታት፡፡ ‹‹ኒዌልስ ኦልድ ቦይስ ወጪውን የማይሸፍን ከሆነ፣ የህክምና ክፍያውን የሚከፍልልንን ሌላ ክለብ እንፈልጋለን›› ሲል ቁርጠኝነቱን በድጋሚ አረጋገጠላት፡፡ ሆርጌና ሴሊያ ያሉ አማራጮችን ሁሉ እስከ እንጥፍጣፊው ድረስ ሊጠቀሙ ቆረጡ፡፡ በመጨረሻ ሊዮ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች እንደሚሆን አባቱ እርግጠኛ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን የሆርሞኑ መርፌ ጉዳይ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡ እዚያ መፍትሔ አለ ከተባለ የማይገባበት ጉድጓድ እንደማይኖር ሰውየው ቆርጧል፡፡ በዚያች ምሽት ሴሊያ የሊዮና የአባቱን አነስተኛ ሻንጣ ሸክፋ አዘጋጀችላቸው፡፡ በማግስቱ ጠዋት አባትና ልጁ ወደ ዋና ከተማዋ ቡዌኖስ አይረስ ተጓዙ፡፡ * አውቶቡሱ መነሳት ካለበት አምስት ደቂቃ ያህል ዘግይቷል፡፡ ለጉዞ በሚሆን መልኩ ለብሰው ሊዮና አባቱ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በሚወስደው መንገድ መጨረሻ ጫፍ ላይ ቆመዋል፡፡ የአራት ሰዓት ጉዞ ይጠብቃቸዋል፡፡ አውቶቡሱ እርጅና ተጭኖት በአንድ በኩል የመስኮቱ መስተዋት ግማሽ ተሰብሯል፡፡ ሊዮ ሊዘጋው ቢታገል አልንቀሳቀስልህ አለው፡፡ ወንበሮቹ በቢጫ፣ ግራጫማና ብርቱካናማ ፕላስተሮች ለጥገና ተለጣጥፈዋል፡፡ ለግማሽ ሰዓት ያህል በአውራ ጎዳናው ጉዟቸው በራሪው ንፋስ ወደ ውስጥ እየገባ ጆሮ ግንዳቸው ስር አፏጨ፡፡ በመጨረሻ ሆርጌ ኮቱን አውልቆ ያለመስተዋት በቀረው መስኮት በኩል የሚገባውን ንፋስ ጋርዶ አቆመው፡፡ ቡዌኖስ አይረስ በጤዛ ተሸፍና ጠበቀቻቸው፡፡ የወረዱበት አውቶቡስ ተራ ከሪቨር ፕሌት ስታዲየም ብዙም አይርቅም፡፡ በከተማዋ ትልቁ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ስፍራ አለ ከተባለ ይኼው የሪቨር ስታዲየም ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው፡፡ ካሉበት ቦታ አንስቶ ሪቨር ስታዲየም የሚያደርሳቸውን ታክሲ ተሳፈሩ፡፡ ታክሲው ወደ ስታዲየሙ እየተቃረበ ሲመጣ ሊዮ ፊቱን በመስተዋቱ በኩል አዙሮ በአትኩሮት ተመለከተ፡፡ ጋብርኤል ባቲስቱታ እና ሄርናን ክሬስፖ ውብ ጎሎችን እያስቆጠሩ ደጋፊዎችን ባስጨፈሩበት ስታዲየም ለክለብ አትሌቲኮ ሪቨር ፕሌት ቢጫወት ምን ያህል ደስ ባለው! ሆርጌ የልጁ ሃሳብ ስለገባው ትከሻውን መታ መታ በማድረግ ‹‹አይዞህ! የምትጫወትበት ስታዲየም የምታገኝበት ቀን ቀርቧል›› አለው፡፡ ይህን የሰማው የታክሲ ሾፌር ‹‹የሪቨር ደጋፊዎች ናችሁ?›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ከድንገተኛው ጥያቄ በኋላ ሊዮና አባቱ ዓይን ለዓይን ተያዩ፡፡ ‹‹አይ የሮዛሪዮ ሰዎች ነን›› ሆርጌ መለሰለት፡፡ ‹‹ሃሃሃ…. የሌፐርስ ደጋፊዎች ናችኋ!? ሁልጊዜ የሚሸነፉ….፣ ኧረ ኤዲያ እነርሱስ!…›› ሆርጌ ከማያውቀው ሰው ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት አልፈለገም፡፡ ‹‹ቤተሰቤን ለባዕድ ሰው አምቼ አላውቅም፡፡ ሃሜት አልወድም›› ካለ በኋላ ሁለቱም ሰዎች እኩል ተሳሳቁ፡፡ *** ሊዮ እንዲህ የሚመች የመጫወቻ ሜዳ አይቶ አያውቅም፡፡ ሳሩ ፍጹም አረንጓዴ ሲሆን በልኩ ተከርክሞ ታጭዷል፡፡ የሜዳ መስመሮቹ አልፈዘዙም፡፡ የጎሉ መረቦችም አዲስ ናቸው፡፡ ሊዮ በበሩ በኩል ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ፈነደቀ፡፡ በሜዳው መሃል እኩዮቹ የሚሆኑ ልጆች ተደርድረው ተመለከተ፡፡ እንደ እርሱ ሁሉ ለሙከራ የተዘጋጁ ነበሩ፡፡ ከቆሙት ከመጨረሻው ልጅ ጀርባ በመሰለፍ ታዳጊዎቹን ተቀላቀለ፡፡ ሆርጌ ለልጁ ቅርብ መሆን ቢፈልግም ከሽቦው አጥር በስተጀርባ መጠበቅ ነበረበት፡፡ ፊቱን በሽቦው ላይ ለጥፎ የሊዮን የሙከራ ፈተና መመልከት ጀመረ፡፡ ትልልቅ የወረቀት ቁጥሮች በሙከራ ላይ በሚገኙት ታዳጊዎች ማሊያ ላይ ተለጥፈዋል፡፡ በሁለት ቡድኖች ለይተዋቸውና ቢጫና ቀይ አልብሰዋቸው አጫወቷቸው፡፡ ወደ 70 የሚጠጉ ህጻናት በክለቡ ለመመልመል ይሞክራሉ፡፡ እያንዳንዱ ተጫዋች ተሰጥኦውን ያሳይ ዘንድ የአምስት ደቂቃ ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ከተጫዋቾች ሁሉ የላቀ ባለተሰጥኦ ከተገኘ ደግሞ 10 ደቂቃ ያገኛል፡፡ ሊዮ በትዕግስት ጠበቀ፡፡ ብዙ ጠበቀ፡፡ ወደ ሜዳ ገብቶ ኳስ ለመንካት ተቻኩሎ ሳለ እርሱና ሌሎች ጥቂት ታዳጊዎች ተራቸው ደርሶ በአሰልጣኙ ተጠሩ፡፡ ሆርጌ ራቅ ብሎ ከቆመበት ሊዮ ወደ ታዳጊዎቹ ይበልጥ ተጠግቶ በነጻነት እንዲጫወት እጁን እያወራጨ አበረታታው፡፡ ሊዮም ቀና ብሎ ወደ አባቱ ከተመለከተ በኋላ የሙከራ ጨዋታው ተጀመረ፡፡… (ይቀጥላል)
2019/08/08 08:59
1