አንድሮሜዳ(ወግ፣ቀልድ፣ግጥም፣ተረብ፣ፍልስፍና)


1660 Members

@ ወግ
@ ግጥም
@ ቀልድ
@ ተረብ
@ ፍልስፍና
ለበለጠ መረጃ 0919354832

እንማማር
@anederomada
{links} {LinksTitle}
{/links}
Today Views : 0
Yesterday Views : 0
One Year Views : 24
ለውብ ቀን 💚💚💚 በትንሹ ትልቁን አትጋርድ በእውቀታቸው የተከበሩትና በትህትናቸው የሚወደዱት መንፈሳዊው መምህር የማለዳውን ትምህርት ለተማሪዎቻቸው ሰተው እንደጨረሱ ተማሪዎቻቸውን አሰናብተው በጥሞና ቆመው አድማሱን አሻግረው በሃሳብ እያስተዋሉ እያለ ከተማሪዎቻቸውአንዱ "መምህር አንድ ጉዳይ አስጨንቆኝ ልጠይቅ ነው የመጣሁ" በማለት ከሄዱበት የሃሳብ አለም መለሳቸው መምህሩም ወደ ተማሪያቸው ዞር ብለው እያዩት "ጉዳዩ አስጨንቆህ ሳይሆን በጉዳዩ አንተ ተጨንቀህ ነው ፡፡ የሆነስ ሆነና ምን እንደሆነ ንገረኝ" ተማሪውም "እንዴት መሰሎዎ መምህር የቅዱስ ቃሉ ሚስጥር እንዲገለጥልኝ እሻለሁ ይሁን እንጂ እለት በእለት እንዳላጠና እንቅፋት ገጥሞኛል . . ." መንፈሳዊው መምህር በጣቶቻቸው ጢማቸውን ሳብ ሳብ እያደረጉ "እንቅፋት እንደገጠመህ አመንክ ፡፡ መልካም እንቅፋቱ ምንድነው? ተማሪው ቀጠለ "የምኖረው ከወንድም እህቶቼ ጋር እናትና አባቴን ጨምሮ በአንድ ትንሽ ጎጆ ቤት ውስጥ ነው እናም ቃሉን ለማጥናት ጥሞናና ጸጥታ የማገኝበት የአፍታ ጊዜ ስለሌለተቸግሬያለሁ ፡፡ ምን ባደርግ ይሻላል? ችግሩን በደንብ አድምጠው የተረዱት መምህርም የተማሪያቸውን ትከሻ በፍቅር አሸት አሸት እያደረጉ "እስቲ አንድ አፍታ ወደጉዋሮ ዞር ዞር እንበል ምናልባት አንዳች ነገር ይገለጥልን ይሆናል" ብለው ወደ ውጭ አብረው ወጡ ፡፡ "እስቲ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት" አሉት "ምን ይታይሃል? " "ወሰን የሌለው ሰፊ ሰማይ" ተማሪው መለሰ "አሁን ደሞ እጅህን አይኖችህ ፊት ጋርደህ ወደላይ ተመልከት ምንድነው የሚታይህ? እጄ ብቻ በደንብ አይተህ ንገረኝ ብለው በቆመበት ትተውት ጥቂት እርምጃ እንደተራመዱ መምህር ከእጄ መዳፍ እና ጣት ውጭ ምንም አይታየኝም እርምጃቸውን ሳያቋርጡ አየህ ልጄ ወሰን አልባውን ትልቁን ሰማይ ማየት ያልቻልከው በትንሿ እጅህ አይንህን ስለሸፈንክ ነው ልክ እንደዚሁ ከቤተሰባችህ ጋር በትንሽ ጎጆ መኖርህን መንፈሳዊውን እውቀት ልብህ እንዳትረዳ ጋረድክ ፥ በነሱ ጨዋታና አንድ ላይ አብሮ በመኖር ፍቅር ውስጥ የቅዱስ ቃሉን ፍቺ መገለጥ ፈልግ . . . በትንሹ ትልቁን አትጋርድ ውብ ቀን!💚
2019/08/24 23:33
ስለ ኑብያ ማለትም ኢትዮጵያ ( እግዚአብሔር ራሱስ ሕዝቦቹ የሆኑትን እሥራኤላዉያን ‹ለእኔ እናንተ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁንምን?› አይደለም እንዴ ያላቸው? ከሀገራችን ታሪክ ጸሐፊዎች ግንባር ቀደም የሆኑት ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ ምንም እንኳን በአሁኑ ዘመን የታሪክ ሊቃውንት ተቀባይነት የለውም በማለት ቢያጣጥሉትም በጥንት የታሪክ ጸሐፊዎች የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከግብፅ ይቀድማል ተብሎ መመዘገቡን ገለጽዋል፡፡ ማጣጣላቸውን የአመለካከት ጉዳይ ስለሆነ ብንተወዉ የሚባለውን ግን እንደሚከተለው ነው ያቀረቡት፡- ነገር ግን የታሪክ አባት የሚባለው ስመ ጥሩው ሔሮዱትስ ወደ ግብፅ መጥቶ ዓባይንም ጎብኝቶ በጻፈው የታሪክ መጽሐፉ እንደዚሁ ዲዮዶር የሚባለው የሮማ ታሪክ ጸሐፊ ከግብፅ በፊት ሥልጡንና ገናና የነበረችው ኢትዮጵያ መሆኗን፤ እሷም ግብፅን ወራ መያዟን ግብፅንም Ú¥(18) የኢትዮጵያ ነገሥታት እንደገዟት፤ ራሷ ኢትዮጵያ ግን በማንም ተገዝታ የማታውቅ አገር መሆኗን፤ ነገሥታቱም ሕዝቡም በጣም ሥልጡን፣ ደግ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰላማዊ፣ በጦርነት ጊዜ ዠግና ጎበዝ መሆናቸውን እያጋነኑ ጽፈዋል፡፡ ኢትዮጵያም በአገር (ጊኦግራፊ) አቀማመጧ ከፍተኛ (ላዕላይ) ግብፅግን ወደታች (ታሕታይ) ዓባይም ከላይ ከኢትዮጵያ ወደ ታች ወደ ግብፅ እየፈሰሰ እንደሚያጠጣት አፈርም እያቀበለ እንደሚመግባት፣ እንደዚሁ እንደ ውሃው አወራረድ ሥልጣኔን ለግብፅ የሠጠጭ ኢትዮጵያ መሆኗን እነዚሁ የታወቁት የጥንት ጸሐፊዎች እነሱንም የተከተሉት ሁሉ አስፋፍተው ጽፈዋል፡፡ በኋላ ግን ግብፅ ደግሞ ከኢትዮጵያ ያገኘችውን ሥልጣኔ አስፋፍታ እንደገና የ፲፰ና የ፲፱ኛው ዲናስቲ ነግሥታት ኢትዮጵያን መልስው እንደገዙ ከዚያ ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያውያን አይለው እንደገና ግብፅን ይዘው የ፳፭ኛውን ዲናስቲ (ሥርወ መንግሥት) እንደመሠረቱና እንደገዙ ተጽፏል፡፡› ብለው አስቀምጠዋል፡፡ ባንድ ወቅት የግብፅ ጥናት ሊቅ የኾነው ፀጋዬ ገ/መድኅን በጦቢያ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ፡ ‹አፍሪካ የመጀመሪያዊቱ የሰው ዘር መገኛ ብቻ ሳትኾን፤ የቋንቋና የፊደል፣ የጽሑፍና የአሐዝ፣ የሙዚቃና የዳንስ፣ የቅርጻቅረፅና የሥዕል፣ ወዘተ መፈጠሪያ ምድር እንደመሆኗ የመጀመሪያይቱ የዓለም ባህል እናትነቷም ዛሬ በማያፈናፍን ማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ዛሬ፣ የማንነቷ ጥያቄም ግልጥ ያለ መልስ ያገኘው በዚህ በሳይንሳዊ እውነታ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ … ቅድመ-ታሪክ ጻሐፍት (antiquity historians) እንደነ ፕሉታርክ እንደነ ፕሊኒ ያሉ፣ ኋላም እንደነ ዲዮርዳኖስና እንደነ ሄሮዶቶስ ያሉ፣ ገና የግሪክና ሮማ ሥልጣኔዎች ከማበባቸው በፊት በካም አበው ሥልጣኔ ላይ ተመሥርተው የሰውን ዘር የሥልጣኔ አመሠራረት መመዝገብ የጀመሩት፡፡ከደቡብ ምሥራቅ ሜዲቴራኒያ ማዶ እስከ ማዳጋስካር ባሻገር፣ ከሕንድ ውቅያኖስ በመለስ እስከ ቀይ ባህር ግራና ቀኝ ያለው ዝርያ፣ ካምም (ኩሽም) አልነው ጥቁር ግብፅ፣ ሳቢያም አልነው ኢትዮጵያ፣ ሀበሻም አልነው ኑቢያ፣ የአንድ የካም ዘር ግንድ ልጅ፣ የአንድ አጥንትና ደም ወንድምና እህት መኾናቸውን ደጋግመው ዘግበውታል፡፡…. በማለት አብራርቷል... ገና ነው አላለቀም አያልቅምም.........
2019/08/15 12:54
በጥዋት ተነስተህ አትበሳጭ፣ ባለፈው ነገር አትማረር፣ አትናደድ ይልቁም ዛሬ ለተሰጠህ ህይወት ፈጣሪህን አመስግን። በህይወት መኖርህ በራሱ ትልቅ ተስፋ ነው። አንተ ጥረትህን ቀጥል ፈጣሪ ሁሉን በጊዜው ያደርጋል። እንዳትረሳ ፦ ስለሌሉክ ነገሮች እያሰብክ ፈጣሪን አታማር ይልቁንም ስላሉክ ብዙ ነገሮች በማሰብ ደስ ይበልክ ፈጣሪህንም አመስግን። ዛሬም ፈጣሪያችን ይመስገን
2019/08/15 00:17
ለውብ ቀን 💚 ድርጊት ከቃላት የበለጠ ይናገራል! ዴል ካርኒጌ ፈገግታችን የስሜታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ በሰዎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖም አንዘንጋ፡፡ ብሩህ ፈገግታ፣ እወድሃለሁ፣ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል የሚሉትን ቃላት ይወክላል፡፡ እያሻሸነው ፍቅራችንን የምናሳየው ውሻችን ሳይቀር ከሩቅ ሲመለከተን ጭራውን እያወዛወዘ የሚሆነውን የሚያሳጣው ለምን ይመስላችኋል? የህፃን ፈገግታም ከልብ የመነጨ ስለሆን መሰል ተፅዕኖ አለው። አዎ! በካርኒጌ ሀሳብ እኔም እስማማለሁ ድርጊት ከቃላት የበለጠ ይናገራል። --------------------------------------------- ሳቅና ፈገግታ ሰደቃ ነው ብለው ነግረውኝ ሼሆቼ ስንቱን ቀን ሰደኩት በውብ ሳቅ ሸኝቼ!!! ሸጋ ኢድ ተመኘሁላችሁ !!!💚💛❤ @anederomada @anederomada
2019/08/11 00:13
አጎቴ ሚስቱ ሞታ ለቀብር ቦታ 40,000 ብር ሲጠይቁት ........ምን አለ . . . . እኔ እኮ ቅበሩልኝ እንጂ አስነሱልኝ አላልኩም😂😂 @anederomada join
2019/07/30 17:24
የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል ===================== 0. - አልቦ 1. ፩ አሐዱ 2. ፪ ክልኤቱ 3. ፫ ሠለስቱ 4. ፬ አርባዕቱ 5. ፭ ሐምስቱ 6. ፮ ስድስቱ 7. ፯ ስብዓቱ 8. ፰ ስመንቱ 9. ፱ ተሰዓቱ 10. ፲ አሠርቱ 11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 20. ፳ እስራ 21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ 22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ 23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ 24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ 26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ 27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ 29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 30. ፴ ሠላሳ 31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 40. ፵ አርብዓ 50. ፶ ሃምሳ 60. ፷ ስድሳ 70. ፸ ሰብዓ 80. ፹ ሰማንያ 90. ፺ ተሰዓ 100. ፻ ምዕት 101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ 102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ 106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ 107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ 109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 120. ፻፳ ምዕት ወእስራ 130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ 140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ 150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ 160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ 170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ 180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ 190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ 200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት 201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት 400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት 500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት 600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት 700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት 800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት 900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት 2000. ፳፻ እስራ ምዕት 3000. ፴፻ ሠላሳ ምዕት 4000. ፵፻ አርብዓ ምዕት 5000. ፶፻ ሃምሳ ምዕት 6000. ፷፻ ሳድስ ምዕት 7000. ፸፻ ሰብዓ ምዕት 8000. ፹፻ ሰማንያ ምዕት 9000. ፺፻ ተሰዓ ምዕት 10,000. ፻፻ እልፍ 20,000. ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 30,000. ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 40,000. ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 50,000. ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 60,000. ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 70,000. ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 80,000. ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 90,000. ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 100,000. ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 200,000. ፳፻፻ እስራ እልፍ 300,000. ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 400,000. ፵፻፻ አርብዓ እልፍ 500,000. ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 600,000. ፷፻፻ ስድሳ እልፍ 700,000. ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 800,000. ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 900,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 1,000,000 ፻፻፻ አእላፋት 10,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት 100,000,000. ፻፻፻፻ ትልፊታት 1,000,000,000. ፲፻፻፻፻ ምእልፊት @anederomada join @anederomada
2019/07/25 14:25
ድንጋጤ ማለት . . ቤትህ ውስጥ በማታ እባብ አይተህ. . . ልትገለው ከአጠገብህ የመጥረጊያ እንጨት አንስተህ . . እባቡ እንዳያመልጥህ በሩን ዘግተህ . . . ወደ እባቡ እየቀረብክ እያለህ. . . . . መብራት ሲጠፋ😳😳😳😳
2019/07/23 20:02
♦️የምትወደውን ሰዉ ስታይ ፈገግ በል እንደምትወደው ይረዳል ♦️ጠላትህንም ስታገኝ ፈገግ በል ጥንካሬህን ይመለከታል ♦️ጥሎህ የሄደን ሰዉ ስታገኝም ፈገግ በል ፀፀት ይሰማዋል ♦️የማታቀዉንም ሰዉ ስታገኝ ፈገግ በል ሰላም ያስገኝሀል @anederomada join
2019/07/23 19:55
​​💞💞💞💞ፍቅር💞💞💞💞 🌷ፍቅር መስጠትና መቀበል ላይ የተመሰረተ ዉለታ መመላለሻ አደለም።ላፈቀሩት ሰው ከምንም በላይ እራስን አሳልፎ መስጠት ያለበት ከራስ ወዳድነት የፀዳ ከንፁህ ልብ እሚመነጭ ኮለል ያለ ፀበል ነው። 🌷ፍቅር የጎደለን ሟሟያ አደለም ከጥቅም ፈፅሞ የራቀ ነው። 🌷ፍቅር የአላማን መንገድ እየተጓዙ አብሮ መራመድ አደለም።ያፈቀሩት ሰው መንገዱን ሲስት መምራትን ይፈልጋል።በጉዞው ደክሞ ወድቆ ቢገኝ እንኳን አዝሎ መራመድን የሚያፀና ነው። 🌷ፍቅር በደልን ይቅርታ የሚል አደለም እሚረሳ እንጂ። 🌷ፍቅር ማዕበሉን ንፋስ ቢያናውጠውም ፀጥ ማድረጊያው ትእግስት አለው። 🌷ፍቅር ውድ ነው መሬት ወድቆ ከምናየው ሰው ጀምሮ እስከ ነግሳል እስከምንለው በፍጡራን ሁሉ ውስጥ የተቀመጠ ድንቅ ስጦታ ነው። 🌷ከከበረ ነገር ሁሉ የላቀ የህይወት ማዕዘን ፍቅር ነው። 🌷ፍቅር አይገዛም አይሸጥም በባህሪው ገዢ ነው። 🌷 ፍቅር ሰጪ ነው ተቀባይ አደለም ሁሉ አላዋ.. ..ምን ጎሎበት ይቀበላል....ብዙ ብዙ ነው። 🌷ፍቅር ቃላት አይገልፀውም። በፍቅር ያኑረን ❣❣ አሜን 🙏 @anederomada join
2019/07/23 19:50
ምስጋና እንኳን እኛ ሰዋች መላእክት ሳይፈጠሩ አምላካችን ምስጋናው አልተቆረጠም ስለዚህ አንተን ከእንቅልፍክ ለመቀስቀስ አልረሳም እና አንተም ማመስገኑን አትዘንጋ። @anederomada join
2019/07/03 13:20
📯የሕይወትህ መርሆዎች በእነዚህ ላይ የተመሰረቱ ቢሆኑ 📯 1. የፈለከውን ነገር ሁልጊዜ ላታገኝ ትችላለህ፡፡ ያገኘኸውን ነገር መውደድን ግን ተለማመድ፡፡ መሻትህ ሁሉ ላይኖርህ ይችላል ያለህን መንከባከብ ግን አትርሳ፡፡ . 2. ኑሮዬ ይበቃኛል ማለትን ተለማመድ፤ ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ስለ ግብህ ማሰብ አቆምክ ማለት አይደለም፡፡ በዚህ ውሳኔ ማረፍ ቅሬታን ያርቅልሃል እምነት ማጣትን ያስወግድልሃል ተስፋ መቁረጥንና የተዛባ አመለካከትህንም ያስተካክልልሃል፡፡ 3. አሳብህም ልብህም ሰፊ ይሁን፤ አመለካከቶችህ ሁሉ ሁሉንም ነገር በቀናነት በመልካም ጎኑ በመመልከትና በማሰብ ላይ የተመሰረቱ ይሁኑ፡፡ . 4. ሥራህንና ቃልህን ለማዛመድ ትጋ፡፡ ልብህና እጅህ እርስ በእርሳቸው እንዳይጣረሱ ጥረት አድርግ፡፡ 5. ወሳኙ ነገር የምትኖርበት ቦታ ሳይሆን አኗኗርህ ነው፡፡ከምታምንበት ነገርም በላይ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባው ባመንክበት ነገር እንዴት ትኖራለህ የሚለው ነው፡፡ 6. ሁላችንም በሕይወት ያለነው ደስተኞች እንድንሆን ነው፡፡ ለዚህም የፈጣሪን ድምጽ አድምጥ፤ ለኑሮህ ብልጥግና ፍቃዱን ተከተል፤ ስኬታማ ለመሆንም በእውነት ላይ ቁም፡፡ 7. እኛ ቀብረን የምናዝነውን ሀዘን ቆመው፣ እኛ ርቦን የምንሰቃየውን ስቃይ ጠግበው፣ እኛ አጥተን የምናነባውን እንባ አግኝተው የሚያነቡት ብዙ ናቸው፡፡ ልዩነቱ እኛ ሁሉን ለእርሱ ክብር ማድረጋችን ነውና ሁኔታዎችህን ሁሉ ለእርሱ ክብር ማድረግን መልመድ ይገባሃል፡፡ 8. ማንም ሰው ከጠባቡ ግለኝነት ሕይወት ወደ ሰፊው ጠቅላላው የሰው ልጅ ምልከታ ከፍ እስኪል ድረስ መኖርን ተማረ አይባልም፡፡ ማለዳ ማለዳ አዲስ ትርጉም ባለው መንገድ ለመኖር ራሳችንንን ብቻ መመልከታችን ወደ ፊት ከመመልከት ጋር ሊዋሐድ ይገባዋል፡፡ 9 . ያለህን ስትሰጥ ጥቂት ሰጥተሃል፤ ራስህን ስትሰጥ ግን ያኔ በእውነት ሰጥተሃል እንደሚባለው የእኛን ብቻ ሳይሆን እኛንም ለሌሎች ማካፈል አለብን፡፡ ለምሳሌ፦ ማየት ለተሳነው ሰው መመልከት ቢችል ኖሮ ሊያከናውን የሚችለውን እኛ ብናከናውንለት፣ መራመድ ለማይችል ቢራመድ ኖሮ ሊሠራው የሚችለውን እኛ በመራመድ ብንሠራለት፣ መናገር ለማይችለው መናገር ቢችል ኖሮ የሚያስረዳውን አፍ ሆነን ብንናገርለት ይህ ራስን ማካፈል ነው፡፡ 10. በፍቅር መግዛት በጥላቻ ከመግዛት፣ ብቸኝነትን ከመንከባከብ ሕይወትን ማጋራት አብዝቶ የተሻለ ነው፡፡በትህትና ልንሠራው የምንችለውን መልካም ነገር በሸካራ ቃላቶች ልናውከው፣ በግለኝነት ልናፍነው አይገባም፡፡
2019/04/24 00:33
በወጣትነክ ሁሉም ነገር ልክ ነው ከሚል መመርያ ውጣ ፡፡ ሁሉን ካለየሁኝ አላምንም አትበል ሰምቶ ማመን ከተጎዱ መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ የሰማንያ አመት እውቀት ለማግኘት የግድ ሰማንያ አመት መኖር አይጠበቅብህም ሰማንያ አመት ከኖሩት በትሕትና ጠይቅ ይገበሀል፡፡ @anederomada
2019/03/13 11:56
ሞት ነው ሚያለያየን ብለን ተማምለን ሞት ስለዘገየ እኛ ተለያየን ..... ....join @anederomada
2019/01/17 23:05
የገና ሰሞን 🌲🌲🌲 ውዴ ለገና ምንድነው ምገዛልኝ ..... እሱ;- ...... አንቺ ማትረቢ የክርስቶስ ልደት እንጂ ያንቺ ልደት አይደለ፡፡ ብላት እርፍ ማነው እንዳትሉኝ ...... ታቁታለችሀ
2019/01/05 22:48
አንቺ'ና ቁንጅናሽ እኔም ለኔ ስልሽ ሌላም ሰው ሲመኝሽ ተወዳደርኩኝ እኔ የግሌ ላረግሽ ግና ምን ያደርጋል መስፈርትሽ ይከብዳል እንኳን እኔ ቀርቶ እብዱም ደግሞ ያብዳል @anederomada
2018/10/31 23:07
ይመቻችሁ ስለተመቸኝ ሰዋች ከእግር ይልቅ ጫማ ያስደንቃቸዋል ከአይን ይልቅ መነፅር ያስደምማችዋል እኮ ለምን ??? ከእግርህ ጫማ ይቀድማል ....ከዓይን መነፅር ይቀድማል ቆዳችንስ ቢሆን ከልብሳቻችን ቀዳሚ ነው እጅ እግር አይን በህይወቴችን ውስጥ ከምንፈልጋቸው በርካታ ሀብቶች በላይ የሚልቁና ትልቁን ስፋራ የሚዙ ናቸው ፡፡ ችግራችን ግን ምንም ጊዜ የምናስበው ያለንን ነገር ሳይሆን የሌለንን ነገር በመሆኑ ነው፡፡ # የአምላካችን ፀጋዋች በእኛ ላይ ከመብዛታቸው የተነሳ እንዘነጋቸዋለን ፡፡ ገንዘብ አውጥተን ለዓይናችን መነፅር ለእግራችን ጫማ እንገዛለን ዳሩ ግን ዓይኖቻችንንም ሆኑ እግሮቻችንም በገንዘብ አልገዛናቸውም ፡፡ ዋጋቸው ለቸሩ አምላካችን ምስጋና ማቅረብ ብቻ፡፡ እኛ ግን ለነገሮች ያለን ዋጋ የተዛባ ነው ፡፡ ከሚያስፈልጉን ይልቅ የምንፈልገውን ዋጋ እንሰቅላለን በዓለም ገበያ የወርቅ ዋጋ ከውሀ ዋጋ ይበልጣል ፡፡ የሰው ልጅ አስተሳሰብ እንጂ ወርቅ ለህይወታችን ከውሀ የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ አልነበረም !!!! #ፈጣሪያችን ሆይ ተቆጥሮ ለማያልቀው ፀጋዋች ምስጋና እናቀርባለን !!!! Join..... @anederomada @anederomada @anederomada
2018/10/22 14:39
እንደው ግራ ገባን ከጠጡ አይንዱ ይሉናል ካልጠጣን ደሞ ሽልማት ያመልጠናል ምን ይሻላል ..... @anederomada
2018/10/10 22:12
ባለፈው የሆነች ወፍራም ነርስ ታክሲ ሰልፍ ላይ መታ " ሜክሲኮ " ነው ......ስትለኝ አው ግን ይሄ የሰዎች እንጂ የዝሆኖች የት እንደሆነ አላቅም ......, ሲያቀብጠኝ ብያት ትላትና ደም ልሰጥ ደም ባንክ ሄጄ ቅጥነቴን አይታ ምን ብትለኝ አሪፍ ነው....... " ምራቅና ሽንት ስንጀምር እንጠርሃለን አላለችኝም " የምን አይቶ ዝም ነው 😅😅😅 @anederomad join @anederomada join
2018/09/28 17:59
እረፍት ስሆን ብቻ ስራዬን እወደዎለሁኝ ፡፡ @anederomada join
2018/09/19 23:57
ይገርመኛል 💧 ችግርህን ለመናገር ሀይማኖት ቦታ ትሄዳለህ ፡፡ 💧 ደስታህን ለመግለፅ ጭፈራ ቦታ ትገባለህ ፡፡ ለዚህም እኮ ነው ገነት የመግባት እድልህ የጠበበው ...... ሮበት ሙጋቤ @anederomada @anederomada
2018/09/01 13:04
እግዜርና ዳዊት አብረው ተባደኑ ብቻውን ታጠቀ ጎልያድ ሚስኪኑ አንዱ ለሽንፈት ተገዶ ሲፈጠር በጥቀሻ ይወድቃል እንኳንስ በጠጠር ምንጭ ፦ በዕውቀቱ ስዩም @anederomada
2018/08/29 17:31
ዛሬ በምታገኘው ካልረካክ ወደፊት ምንም ብትሰራ አትረካም @anederomada join @anederomada
2018/08/14 19:32
ባይኖርህም ትኖራለህ ቢኖርህም ትሞታለህ @anederomada @anederomada
2018/08/14 15:28
ባያስቅም ሳቁልኝ😃😄😆 አንድ ሰውዬ በጣም ሰክሮ መንገድ ላይ እየሄደ ፖሊስ ያገኘው ና ፖሊስ ፦ አንተ ሌባ ወዴእየሄድክ ነው ሰውዬው ፦ኧረ ጌ ታ ዬ ወደ ስራ እየሄድኩኝ ነው ። ፖሊሱ፦ የምን ስራ አሁን እኮ ለሊት 6: 00 ሰዓት ነው ለመሆኑ የት ነው ምሰራዉ. . . ሰውየው ፦ ሬዲዮ ጣቢያ ፖሊስ ፦ አንተ ውሸታም ሬዲዮ ጣቢያ 6 : 00 ያልቅ የለ ሰውዬው ፦ እንዴ እና ማነው ከ 6 :00 ሰዓት በ በኋላ እሽ ሽ ሽሽ ሽ ሽ ሽሽ ሽ ሽ የሚለው at @anederomada share to ur frinde Join @anederomada join
2018/07/31 12:48
ሰዎች ሲተቹህ #አድንቃቸው ሲረግሙህ #መርቃቸው ሲበድሉህ #ታገሳቸው ነገር ግን ሁሌ አይተቹህም ሁሌም አይረግሙህም ማወቅ ያለብህ እንደ ሰው ማሰብ ጀመሩ ቀን ባደረጉት ስራ ሲፀፀቱ ይኖራሉ ። የፀፀታቸውም እስረኛ ሆነው ይዘልቃሉ አንተ ግን ሁሌ #ታጋሽ ሁን join #anederomada join
2018/07/27 16:23
(ሳሙና) በእግሊዘኛ ምንድነው ስትባል # B 29 ያልከው ልጅ ትምህርት ሚኒስትር ይፈልግሃል ። 💙 @anederomada
2018/07/20 11:56
🌍 ከፍልስፍና 🌍 ማመን ስጀምር ማሰብ ታቆማለክ ። 💙 @anederomada 💛 @anederomada ❤️ @anederomada
2018/07/17 23:12
ከፍልስፍና በፈገግታ የተሞላ ፊት ሁሉ ችግር የለበትም ማለት አይደለም ። ችግራቸውን የሚወጡበት መንገድ አላቸው እንጂ ። ፦ ሼክስፒር 💙@anederomada 💛@ ❤️
2018/07/13 16:56
🚔 ሌባ 🚔 ለፍቅረኛሞች ቀን .. .... አበባ ሊሰጥሽ በገንዘቡ ገዝቶ ባልሽን አየሁት ስጦታ ቤት ገብቶ አበባዬን ሰርቆ ... አበባ ሊሰጥሽ የሚታየኝ ጀዝባ አበባ መሆንሽን አያውቅም ይህ ሌባ ( ሌባ ) የሚለውን ገልብጠሽ አብቢው ውስጥሽ ስለገባ .... join @anederomada
2018/07/12 18:32
በጣም በጣም ይቅርታ ጠፋሁኝ አይደል ወንድሞች እና እህቶች አሁን ተመልሻለሁኝ
2018/07/11 20:25
የሆነ ሰዉ እንዲህ ተብሎ ይጠየቃል ... አንተ ግን ለምንድነው ስትናደድ አይቼክ አላውቅም ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ተጠያቂው ፦ እኔ ከማይረብ ሰዎች ጋር ሙግት አልገጥምም በቃ #ልክ-ነክ ብዬ ስለማልፍ ነው ፡፡ ጠያቂም ፦ ግን እኮ እንዲህ ማድረግ ጥሩ አይደለም ሲለው ተጠያቂ ምን ቢለው ጥሩ ነው 🔻 🔻 #ልክ-ነክ Join @anederomada @anederomada
2018/06/08 19:16
edit photo
2018/06/08 19:03
ወግ መስዋዕትነት ያሁኑን ባላቅም በኛ ጊዜ ከሴት ጋር ከመውጣት ከሀገር መውጣት ይቀልነበር፡፡ ጎረምሳ እያለሁኝ የመጀመሪያ ፍቅሬን 💋 ለመሳም 💋 የከፈልኩት መስዋዕት በሰሜን ድንበር አካባቢ ብከፍለው ኖሮ ኤርትራ አትገነጠልም ነበር፡፡ ትዝ ይለኛል ለምወዳት ልጅ አምባር ለመግዛት ፈልጌ ከአባቴ አስር ብር ሰረኩት .... ፡፡ አባቴ እንዴት ከኔ ከደሀው አስር ብር ጨክነክ ሰረክ ብሎ ምርር ብሎ የሀያ ብር በርበሬ ገዝቶ አጠነኝ፡፡ ከአባትህ ጭካኔ ተርፈህ እንሻሽላ የሞቀ ፊትህን ይዘህ ጅንጀናህን ትቀጥላለክ፡፡ ሲፈርድብህ ልጅቷ ወንድም ይኖራታል ፈጣሪ አንዲት ቆንጆ ሴት በፈጠረ ቁጥር አብሮ ቀናተኛ ወንድም ለምን እንደሚፈጥር አይገኝም፡፡ ወንድምየው በጉልበት የሚበልጥህ ከሆነ መስቀልኛ መንገድ ላይ ጠብቆ በጠረባ ይጥልካል ፡፡ በጉልበት የሚያንስ ከሆነ ደግሞ ውሻ ገዝቶ ያንተን ታፋ ከእህቱ ታፋ ለይቶ እንዲነክስ አሰልጥኖ ይለቅብሃል ፡፡ በርበሬ የታጠነ ፊት የተሰበረ አፍንጫ የተነከሰ ታፋ ይዘህ ተስፋ ይዘህ አይ ስ ስ ያፈረሰው ሀውልት መስለህ ጅንጀናህን ትቀጥላለህ፡፡ በመጨረሻ ይሳካና ልጅቷን ወደ ጫካ ትወርዳለህ ፡፡ ጫካ ውስጥ ሣር አንጥፈህ ወድያው ጋደም አርገህ ልትበለበልባት ስትሰናዳ ባካባቢው የተመደበ ደን ጠባቂ ሽማግሌ ደርሶ በወይራ ሽመል ያበረይሃል ውይ ኧረ ውይ ግን ለምን ፡ እንጃ አባቱ ደን ጠባቂ በመንግሥት የተመደበ ደን እንዲጠብቅ ነበር ፡፡ በራሱ ጊዜ ያካባቢው ኮረዳች ድንግል ጠባቂ ሆኖ ይሰማራል ፡፡፡ ይቀጥላል....... join @anederomada @anederomada
2018/06/05 14:04
📔 ስለ መፅሐፍ 📙 ፦ መፅሐፍን ማንበብ ዓለምን ቁጭ ብሎ መመልከት ነው፡፡ ጭንቅላታችንን በማይረባ በከንቱ ነገር ከማጨናነቅ በተለያዩ መፃህፍት ብንሞላው ለሃገርም ሆነ ለወገን እንዲሁ ለራስ የሚጠቅም ገፀ በረከት እናበረክታለን፡፡ መፅሐፍ ማንበብ በውስጣችን ያለውን የጥበብ ስልት እንደማብራት ይቆጠራል፡፡ ብዙ የዕውቀት ባለፀጎች ዓለምን የሚለውጥ ታላላቅ ስራዎችን የሰሩት መፅሐፍትን በጥንቃቄ በማንበባቸውና በመረዳታቸው ነው፡፡ ❗️ የሰማንያ አመት ዕውቀት ለማግኘት የግድ ሰማንያ አመት መኖር አይጠበቅብህም........❗️ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡ስለዚህ እናብብ እናብብ................... @anederomada @anederomada @anederomada
2018/05/30 21:50
🔴ሴቶችን የማያከብር ያልሰለጠነ ወደፊትም የማይሰለጥን ነው፡፡ ዶ/ር አብይ አህመድ @anederomada join @anederomada
2018/05/30 21:50
የተወደዳችሁ ቤተሰቦች እንደምንመለከተው ግንቦት ወር ከመጀመሪያው እንደ ክረምት ዝናብ እየዘነበ ይገኛል ....... በርካታ አባቶች እናቶች ወንድም እህቶች ህፃናት ሳይቀሩ በየጎዳናው በየጥጋጥጉ በየ ቤ/ክ ወድቀው ይገኛሉ............ እናም በቤታችን ውስጥ የማንለብሳቸው ሳጥን ያጨናነቁ አልባሳት ለነዚህ ሰዎች ብንለግስ ትልቅ በረከት ነው፡፡ በመጪው 20/9/2010ዓ.ም ወደ እንጦጦ ለመሄድ አስበናል ፡፡ በዛ የሚገኙ ወገኖች ለመርዳት ቅድመ ዝግጅት ላይ እንገኛለን 🔴 የታመሙትን ለመጠየቅ 🔴 የተለያዩ አልባስን ማድረስ እኔ ነኝ ደራሽ ለወገኔ እኔ ነኝ እርሱ ነው እኔ ሰው ያረገኝ ያቆመኝ..... እነዚን ሀሳቦች ለመከወን ወይም ለመቀላቀል ከፈለጋችሁ... @anederomada ሰውን ለመረዳት ሰው መሆን በቂ ነው፡፡. @anederomada join @anederomada
2018/05/23 15:45
እውነተኛ ታሪክ ቀን 12/09/2010 ዓ.ም ማለዳ 1:00 ከእንቅልፍ ነቃሁኝ፡፡ በአቅራቢያችን የሚገኘው ቤ/ክ የቅዳሴው ዜማ ከማለዳው የወፎች ዝማሬ ጋር ተደምሮ መንፈስ ያድሳል፡፡ እለተ ሰንበት ስለነበር ወደ ቤ/ክ አቀናሁኝ ፡፡ ልክ ቤ/ክ አቅራብያ ስደርስ በህይወቴ እንዲህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም ፡፡ ቤ/ክ ጥግ ጥጉ ብዙ አባቶች ፣ እናቶች፣ ወንድሞች እንዲሁ ህፃናት እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ እናም አንድ አባት ይመስለኛል ማታ በዘነበው ዝናብ ምክንያት በሞት ተለይተው ነበር፡፡ በህይወቴ ሰው ሞተ ሲባል ደጋግሜ ሰምቻለሁ ፡፡ በዓይኔ ያየሁት ግን በዝች እለት ነበር፡፡ በጣም ደነገትኩኝ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አልገባኝም ፡፡ ደሞ ማለዳ ስለነበር ብዙም ሰው አልነበረም ፡፡ ይበልጥ ደሞ እንዳዝን ያደረገኝ ሰዓቱ እየገፋ ሲመጣ ብዙ ሰዎች ተሰበሰብ፡፡ መረባረብ ተጀመረ ፦ ወድያው ፊታቸው ተሸፈነ በአቅራቢያው ያለ ጤና ጣብያ ተሰዱ፡፡ ምን ልበላችሁ......................... ሁሉም በየፊናቸው ተረባረብ፡፡ ሳስበው ግን ......... ሰውዬው ሳይሞት እዛጋ የተሰበብነው ሰዎች ሁሉም አንድ ብር ቢያዎጡለት እርግጠኛ ነኝ ሰውየው ቢያንስ ደሀ አይሆንም ነበር ፡፡ ካለፈ በኃላ ምን ይረበዎል............ @anederomada...... ይቀጥላል......
2018/05/23 15:45
ለፈገግታ😆😜😳 አንድ ሃብታም ሰውዬ አርፈው፡፡ ሰፈር የሚያውቆቸው ደሀ ሰውዬ ከህፃን ልጅ ጋር አብሮ ለቅሶ ቤት ይሄዳል ...... የሀብታሙ ሞልቃቃ ልጅ ታለቅሳለች ..... ወይኔ አባብዬ .... እዛኮ ምግብ የለም.. ውይ አባዬ ....እዛኮ ውሀ የለም ወይኔ ........ አባብዬ... እዛኮ ድሎት የለም..... ህፃኑ ልጅ ሰማትና አባቱን ምን ቢለው ጥሪ ነው..... 🔻 🔻 🔻 🔻 ቆይ አባዬ ይሄ ሰውዬ እኛ ቤት ነው እንዴ የሚመጡት 😅😅😅😅😅😅😅 @anederomada join join
2018/05/21 23:34
ፍልስፍና እዉነት ምንድነው ፦ ይህ ጥያቄ በራሱ እውነት ነው❗️
2018/05/21 23:34
📝ከፃፋሽልኝ መሀል📝 ትዝታ ነው መሰል እጅግ የሚጥመኝ ከሚታየው ፁሁፋሽ የሰረሽው ጣመኝ @anederomada @anederomada
2018/05/21 23:12
የፍቅር ማገዶ ... የማይሰማ ልቧን ጋግሬ ልበላው .... የፍቅራን እንጎቻ ሳስስ ሳስስ .... ሳስስ ምጣድ ልቧን .... ሳስስ ድንጋይ ልቧን.... ሳስስ ልቤ አለቀ .... ነዶ ለፍቅር ..... ተማግዶ ወይ ነዶ join Join @anederomada
2018/05/18 19:18
ወግ ከእለታት አንድ አንድ ወጣት ወደ መርቆሪዮስ ሚባል አባት በኣት(መገኛ) ሄደና፡፡ አባቴ ሆይ ❗️ ድህነት ❗️አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ ሲል ጥያቄ አቀረበ መቃርዮስም ፦ ወደ መቃብር ሂድና ሰድበሐቸው ና ‼️ ይህም ወጣት የተባለው አድርጎ ተመለሰ፡፡ መቃርዮስም ፦ ምን አሉህ፡?? ወጣቱም ፦ ምንም አልመለሱልኝም ሲል መለሰ፡፡ አባ መቃርዮስም ፦ አሁን ደግሞ ሙታንን አመስግናቸው ና አሉት? ሄዶም አመሰገናቸው ፡፡ አሁንስ ምን አሉህ ? ሲሉ በድጋሚ ጠየቁት ወጣቱም ፦ ኧረ አንዳች አልመለሱልኝም ሲል መለሰ፡፡ አባ መቃርዮስም ፦ ስትሰድባቸውን ስታመሰግናቸውም ሆነ ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱልህም፡፡ አንተም ለነፍስህ ድህነት ከፈለክ እንደሞተ ሰው ሆነክ ኑር!!!! ሲሰድቡህም ሲያመሰግኑህም ምንም አይምሰልህ፡፡ Join @anederomada
2018/05/18 18:46
ለዛሬ በጣም አስደሳች መሳጭ የፍቅር ታሪክ ...... ሁለት ፍቅረኛሞች ነበሩ፡፡ ታድያ እነዚህ ፍቅረኛሞች ከመዋደዳቸው የተነሳ ሲበሉም ሲጠጡም ሆነ ሲዝናኑ ተለያይተው አያውቁም አንድ ቀን አንድ ላይ ሆነው ወክ በሚያደጉበት ሰዓት ሲበር የመጣ መ ኪ ና ፍረኛዋን ከጎና ነጠቃት የለበሰችው ልብስ በፍቅረኛዋ ደም ተጨማለቀ፡፡ እጅግ አዘነች ፡፡ ልብሷ ላይ የተፈናጠረው የፍቅረኛዋ ደም የፈለገውን ያህል ቢታጠብ ሊለቅ ወይም ሊፀዳ አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ ሌላ ጭንቀት ፈጠረባት ይባስ ብሎ ❗️በህልሟ❗️ፀጉራቸው የሸበተ አሮጊት ሴትዮ በፍቅረኛዋ ደም የተጨማለቀውን ልብሷን ለብሰው ይታይዋት ጀመር፡፡ ይህን ጊዜ አበደች፡፡ ብቻዋን ሆና መለፍለፍ ጀመረች፡፡ መዘባረቅ ስራዋ ሆነ፡፡ ይህ ችግሯን ልብ ያሉ ቤተሰቦቿ ይዘው ፀበል ይወስዳታል ፀበል ቦታ ስትደርስም ❗️በህልሟ❗️የታይዋት ሽበታም አሮጊት ሴትዮ በግራ እጃቸው መቋሚያ ተደግፈው በእጃቸው መቁጠሪያና የፀሎት መፅሐፍ ይዘው አገኞቸው፡፡ ደነገጠች፡፡ አጠገባቸው ስትደርስም ቀና ብለው......... ( ልጄ መጣሽ)....እኔም አንድ ቀን እንደምትመጪ ዓቅ ነበር፡፡ አሏት በደበዘዘ ድምፅ ቀጥለው.... የፍቅረኛሽ ደም ከልብስሽ አለቀቀም፡ እንዳለሽ አውቃለሁ፡፡ ማስለቀቅያው እኔ ዘንድ ይገኛል አሉና መሀረባቸውን ፈተው የተቋጠረ ነጭ ዱቄት መሰል ነገር አውጥተው ሰጧት፡፡ እሷም አሮጊቷ የሰጧትን ነገር የዛ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ በፍቅረኛዋ የተጨማለቀውን ልብሷን አሮጊት ቋጥረው በሰጧት ነጭ ዱቄት መሰል ነገር ስታጥበው የፍቅረኛዋ ደም ከልብሷ ላይ ሙልጭ ብሎ ጠፋ፡፡ ለካስ አሮጊቷ የሰጥዋት ነገር 🔻 🔻 🔻 🔻 ‼️ ኤርያል የዱቄት ሳሙና ነበር‼️ በአንድ እጥበት ቆሻሻ የሚያፀዳ ኤርያል ሳሙና ማስታወቂያ ነ በ ር፡፡ Join @anedermada
2018/05/17 18:15
📢 ረመዳን ከሪም📢 ለማከብራችሁ @የአንድሮሜዳ ቻናል ጓዶቼ የረመዳን ወር የራህመት ወር እንዲሆንላችሁ ተመኘው፡፡ ለመሆኑ # ረመዳን ማለት ምን ማለት ነው...........? በጥቂቱ ...... ታላቁ ሙፈሲር ኢማሙ ቁርጡብይ.. ረመዳን እኮ የተባለው ወንጀሎቻችንን በመልካም ስራዎች አቃጥሎ አመድ የሚያደርገውን ነው፡፡ በማለት ያብራራል... እስቲ ማነው ሙስታይድ‼️ በዚህ በተከበረው የረመዳን ወር መልካም ስራዎች አብዝቶ በመስራት አመቱን ሙሉ ያከማቸውን ወንጀል ️አቃጥሎ አመድ‼️ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ..... @አንድሮሜዳ
2018/05/15 18:35
አባዬ አባዬ፦ ማታ በህልሜ ጫማ ስትገዛልኝ አየሁ...... ፦ አይ ልጄ ላንተ ደሞ በነገው ህልምህ ሱሪ ስገዛልክ ታያለህ @anederomada
2018/05/13 20:16
❗️ እናቴ❗️ አንድ ቀን ለእናቴ ፍቅር ምንድነው??? ብዬ ጠየኳት ...... ፈገግ ብላ በኔና በአንተ ያለው ብላ መለሰችልኝ፡፡ ከዛ ቀን ጀምሮ ከዚህ የበለጠ እውነተኛ መልስ አላገኘሁም፡፡ ሁሌም በእናት ጉያ መታቀፍ በእናት ልሳን መመረቅ ከልቧ ባይሆንም መሰደብ ....መመከር ....ብቻ ሁሉ ነገር በእናቶች ያምራል ፡፡ ስለእናት ፍቅር ቃላት ልታዋቅር ብዕር ስታነሳ እንባ ባዓይንክ ይሞለዋል፡፡ ‼️ በቃ እናት እናት ናት‼️💯 ጤና ፣ እድሜ፣ ፀጋ..ለእናቶች ያብዛ ፈጣሪያችን፡፡ ክብር ለእናቶቻችን @anederomada
2018/05/13 20:16
ለፈገግታ ኑርሰፋ፦ ትላንትና የላኩልክ Text አነበብከው??? አሚር፦ 1000 ብር አበድረኝ ያልከው‼️‼️ ኑርሰፋ፦ አዎ😋😋 🔻 🔻 አሚር፦ አይይይይ አላነበብኩትም @anederomada
2018/05/12 17:27
🙏 ይቅር በለኝ ስልህ🙏 ምነው አላህዬ ምነው እግዜርዬ ሺህ ጊዜ እያጠፍሁ << ይቅር በለኝ ስልህ>> ይቅር የምትለኝ ...... ምነው አንደኛህን..... የማላጠፍበትን ጥበብ ብታድለኝ Join anederomada
2018/05/11 16:51
😆😆 ደስተኝነት😆😆 ቆይ ደስተኝነት ሁሉ ሲሞላልህ የሚገኝ ነገር ይሆን ከፍልስፍናው ጥግ እንየው...... ደስተኝነት የግል ውሣኔ ነው፡፡ እና በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ደስተኛ ለመሆን ወስን፡፡ አንተ ደስተኛ ለመሆን ከቆረጥክ ያንተን ደስታ ሊነጥቅ የሚችል አንዳች ኃይል የለም‼️ ደስተኛ ቅድመ-ሆኔታ የለውም፡፡ ምንም የጎደለህ ነገር እንደሌለህ ባሰብክ ጊዜ አለም ሁሉ ያንተ የሆነ እስኪመስል ድረስ ውስጥ ህ በደስታ ማዕበል ይጥለቀለቃል፡፡ ላኦ ዙ ( በ5 ኛው ክ/ዘመን የኖረ የቻይና ዕውቅ ፈላስፋ) ፦ Happiness is adecision . Not a coniditional fulfilment of any kind..... ስለዚህ ጎዶሏችንች እስኪሞላ ድረስ .... ባለን ፣ በተገኘንበት ፤ ባለንበት ፣ በቀረችን ............... በዚህ በእጃችን ባለችው....... ፍቅር ደስታ አይለየን፡፡ የደስታ ምንጭ የሆነ ፈጣሪ አምላካችን የተመሠገነ ይሁን፡፡ መልካም የደስታ አመታት ይሁንሎ‼️‼️ @anederomada
2018/05/11 16:51
😄😜Haha short love story💯 👨 boy፦ hi konjo 👱‍♀Girl ፦ hi bro..... The End
2018/05/10 17:32
😂😂 ያሳዝናል😰😢 እውቁ የ 31 አመቱ ደራሲ ይስማከ ወርቁ በደረሰበት ድንገተኛ የመኪና አደጋ እጅጉን ተጎድታል፡፡ ምንም መና ገር የማይችልና ያለፈ የህይወት ተግዳሮቶች ማስታወስ አይችልም፡፡ ስለዚህም የዚህ @anederomada ተከታዮች ፈጣሪ ወደ ቀድሞ ጤንነቱ እንዲ መልሰው እንደየ እምነታችን ፀሎት እናርግ፡ ፡ የይስማከ ቀደምት ስራዎች፦ ዴርቶጋዳ ፤ ራማቶሓራ ዛንቶዛራ ፣ ዮራቶራድ የወንድ ምጥ ፣ ተከርቸም ተልሚድ ፣ ክብር ድንጋይ ..... ብቻ ምን አለፋችሁ በዚህ ለጋ እድማው 13 መፃህፍት ለኢትዮጵያ ህዝብ አበርክቷል፡፡ join @anederomada
2018/05/10 16:50
🇪🇹ላወቀበት🇪🇹 ህይወት ትምህርት ቤት ናት ሰዎች ጥያቄ ናቸው፡፡ 🕖ጊዜ መልስ ነው፡፡
2018/05/10 16:50
🚖 ታክሲ ውስጥ🚕🚕 ታክሲ ውስጥ ከኃላ ተቀምጬ ከፊቴ ላይ የተቀመጠው ልጅ አጠገቡ ያለችውን ልጅ ገና ከመግባቱ ይጀነጅናት ጀሠር፡፡ ልጅ፦ ሀይ ቆንጆ ልጅቷ፦ ሀይ (ኮስተር ብላ) ልጅ፦ ጠፋሽ ምነው?? ልጅቷ፦ አይ መብራት ሀይል ገብቼ ነው ልጅ፦ ወዴት ነሽ ልጅቷ፦ ወደፊት ልጅ፦ ልሸኝሽ ( ቆይ ታክሲ ውስጥ አይደል እንዴ ያለነው) ልጅቷ፦ ይቅርብህ ትጠፍለህ ልጅ፦ ሰፈርሽ የት ነው ልጅቷ፦ ለልማት ፈርሳል ልጅ፦ ኧረ ተጫዋች ነሽ ልጅቷ፦ ኧረ አሰልጣኝ ነኝ ልጅ፦ ስልክ አለሽ ልጅቷ፦ Network የለውም ልጅ፦ ተመቸሽኝ ልጅቷ፦ ከታክሲው ነው ልጅ፦ ማታ ለወክ ትወጪያለሽ ልጅቷ፦መብራት ስለማይኖር ይጨልማል ልጅ፦ አንድ ነገር ላስቸግርሽ,,,,,,,, ልጅቷ፦ ............,... . . . . እኔ ፦ ወራጅ ፡ ወራጅ ወራጅ!!!!! እነሱን እየሰማሁኝ ቤቴን አለፋኩት፡፡ ከዚህ በኃላ የተባባሉትን አልሰማሁም፡ ፡ ወርጄ ወደቤቴ ቅደድኩት፡፡
2018/05/09 23:33
😇😇 እናስተዉል ታዋቂ ለመሆን ሳይሆን አዋቂ ለመሆን ጣር፡፡ አዋቂ ሰው ስትሆን ሳታስበው ታዋቂ መሆንህ አይቀርም አዋቂ ሳትሆን ግን ታዋቂ መሆን ከባድ ነው፡፡ please share.......👍👍👍👍 Join @anederomada
2018/05/09 16:45
⚠️ አይደንቅም⚠️ የትኛውም ሰው ልጅ ‼️እንስሳ‼️ ብትለው እጅግ ይበሳጫል😡😡😡😡 ነገር ግን አንበሳ 🦁🦁🦁 ሰትለው ይደሰታል፡፡😀😆😀 Join @anederomada
2018/05/09 16:24
📖 የኢትዮጵያ ቀደምት ስሞች📖 አቢሲኒያ ፣ ኑብያ ፣ ኩሽ ፣ አክሱም........ Join @anederomada
2018/05/09 00:50
እማዬ አቤት ልጄ ልጅ፦መቼ ነው የተወለድኩት ህዳር 9 ፡፡ እንዴ እማዬ በልደቴ ቀን Join @anederomada
2018/05/08 00:44
‼️ የድሀ ወንድ አሽሙር🙊🙊 ከመኪና ኃላ የቆንጆ ጋጋታ መስተፍቅር ነው ወይ የቤንዚኑ ሽታ Join @anederomada
2018/05/07 10:22
ከሌላው የተሻልኩኝ ነኝ ብለህ አታስብ፡፡ አንተ በቃ ልዩ ነህ እንጂ የተሻልክ ወይም ያነስክ አይደለም፡፡🇪🇹 join @anederomada
2018/05/07 10:15
📢📣📢ተፈጥሮን ተረዳ📢📢📢 ሁለት የዜን ደቀመዛሙርት ልብሳቸውን ከወንዝ ዳር ተቀምጠው ሲያጥብ አንድ እባብ ወደዉሃው ውስጥ ገብቶ ሲንፈራገጥ ለመወጣት ሲንፈራገጥ ይመለከታል፡፡ በዚህ ጊዜ አንዱ ደቀመዛሙር ወደውሃዉ ገብቶ እባብን በሁለት እጁ ወደዳር በማውጣት አስቀመጠው፡፡ ይሁንና እባብ ከመሬት እንዳረፈ የደቀመዝሙሩን እጅ ነደፈው፡፡ የተነደፈ እጅን በፍጥነት ካደማ በኃላ መድሀኒት ያደርግበታል ከቆይታ በኃላ ወደ አጠባው ይመለሳል፡፡ ለአፍታም ሳይቆይ እባብ ተመልሶ ወደ ውሀ ዉስጥ በመግባት ለመወጣት መንፈራገጥ ጀመረ፡፡ ተማሪው ደቀመዛሙር ተመልሶ ወደውሃው ገባና እባብን በማውጣት ከደረቅ ምድር አስቀመጠው ፡፡ ይህን ሁኔታ ይመለከት የነበረው ሌላው ደቀመዛሙር በጎደኛው ተግባር ተገርሞ ፦ወዳጄ! ቅድም እባብን ከውሀው ስታድነው ነደፈህ ፤ አሁን ደግሞ ምታድነው በድጋሚ እንዲነድፍህ ነው??በማለት ጠየቀው፡፡ የዜኑ ተማሪ ፦ወዳጄ!!መንደፍ የእባብ ተፈጥሮአዊ ባህሪይ ሲሆን ማዳን ደግሞ የኔ ባህሪይ ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ የሰው ልጅ የሚያጋጥሙ መከራ በእባብ ይመሠላል፡፡ ያንተ ደግነትህን ግን እንዳይለውጠው፡፡💯💯💯💯💯📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 🔔🔔 Share....share🔔🔔🔔🔔 Join @anederomada
2018/05/07 00:34
ይሄ ሞኝ ባልሽ አንቺን የወሰደሽ ከኔ ላይ ቀምቶ አንቺን ከኔ በላይ የማያቅሽ ከቶ ሚስት አገባሁኝ ይላል እሬሳ ጎትቶ ሲያሳዝን😞😞😞😞‼️‼️ ለጀለሶቻችሁ share...share
2018/05/06 17:46
ሰዎችን መቼም ቢሆን መጥፎ ነገር አትምከራቸዉ ያ መጥፎ ምክርህ መጥፎ ስያደርጋቸው መልሰው እራስህን ይጎድኃል፡፡ ልባቸዉን በመልካም ነገር ለመሙላት ሞክር ካልቻልክ ዝም በል!! ዝምታህ በራሱ መልካም ነዉ፡፡ share for ur friends...‼️‼️‼️‼️
2018/05/06 17:13
channel create
2018/05/06 16:36
1