አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ


1951 Members

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ቻናል ትክክለኛ, እውነተኛ እና ፈጣን መረጃ የሚያገኙበት ምርጥ የ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ቻናል ከተማሪ ለ ተማሪ ፡፡

ሀሳቦች እና እንዲስተላለፍላችሁ የምትፈጉት ነገር ካለ በ
@newneway
@tberhanu
@asutiiii ላይ ይጎብኙን፡፡
አምዩ info ........እውነተኛ እና ፈጣን መረጃ ይደርሶታል፡፡
Arba_Minch_university
{links} {LinksTitle}
{/links}
Today Views : 0
Yesterday Views : 0
One Year Views : 2
Arba Minch University አዲሱ የሠራተኞች የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ ጥቅምት ላይ ተግባራዊ ይደረጋል አዲሱን የሠራተኞች የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያን በጥቅምት ወር ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ገለፀ፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ከአምላክነሽ ደሳለኝ እንደገለፁት አጠቃላይ የድልድል ሥራው ከመሠራቱ አስቀድሞ በአፈፃፀም መመሪያው ዙሪያ በስፋት ለሠራተኞች ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች እንዲሁም ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመጋበዝ የተፈጠሩ ብዥታዎችን የማጥራት ሥራ መሠራቱን አስታውሰዋል፡፡ በአፈጻጸም መመሪያው መሠረትም የደልዳይና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ተዋቅረው እንደነበርም ገልፀዋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲው 6,132 የሥራ መደቦች ተፈቅደው እንደነበር ያስታውሱት ዳይሬክተሯ ከእነዚህም መካከል በአፈፃፀም መመሪያው መሠረት አዲስ የተቀጠሩ፣ በትምህርት ላይ ያሉ እንዲሁም በዲሲፕሊን ቅጣት ምክንያት በውድድሩ የማይሳተፉ ሠራተኞች የሥራ መደቦችን በማስቀረት 5,743 የሥራ መደቦች በሁሉም ካምፓሶች ለውድድር ይፋ ሆነው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከሥራው ውስብስብነትና ለውድድሩ የሚያስፈልጉ የሠራተኛው መረጃዎች ተጠናቅረው ባለመገኘታቸው ሳቢያ የድልድል ሥራው ረጅም ጊዜ ወስዶ እንደነበር የተናገሩት ወ/ሮ ከአምላክነሽ 3,656 ሠራተኞች እንደተመደቡ እንዲሁም ምደባውን ካገኙ ሠራተኞች መካከል 65 በመቶው በፍላጎታቸው ማለትም በ1ኛና 2ኛ ምርጫቸው ቀሪዎቹ 35 በመቶ ሠራተኞች ደግም የትምህርት ዝግጅታቸውንና የሥራ ልምዳቸውን መሠረት በማድረግ በኮሚቴው ተመድበዋል ብለዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ በኮሚቴው ከተመደቡ 1,369 ሠራተኞች መካካል 853 ያህሉ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን የቀረቡት ጥያቄዎች በተዋቀረው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከተመረመሩ በኋላ ኮሚቴው መጋቢት ወር ላይ ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ 14 ሠራተኞች ለሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው 9ኙ ለዩኒቨርሲቲው፣ 3ቱ ለሠራተኞቹ የተወሰነ ሲሆን የአንድ ሰው ጉዳይ በሂደት ላይ ነው፡፡ በአዲሱ ምደባ ከፍ ባለ መደብ የተመደቡ ሠራተኞችን በተመለከተ ያለውን የደመወዝ ልዩነት እንዲያገኙ የሚል የአፈፃፀም መመሪያ መተላለፉን የተናገሩት ዳይሬክተሯ ሠራተኞቹ የደመወዝ ልዩነቱን ማግኘት የሚችሉት በቀድሞው ደረጃ ለመደቡ የሚያስፈልገውን ተፈላጊ ችሎታ ማሟላታቸው እየተረጋገጠ ነው ስለሚል የማጣራቱ ሂደት ሰፊ ጊዜ ወስዷል ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለበላይ አካል ለውሳኔ መቅረቡንና ከመስከረም 1/2011 ዓ/ም - ሰኔ 30/2011 ዓ/ም መስፈርቱን ላሟሉ ሠራተኞች የልዩነት ክፍያው በቅርቡ የሚፈፀም መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት የደመወዝ ስኬል መመሪያ ፀድቆ ለዩኒቨርሲቲው እንደተላከ የተናገሩት ዳይሬክተሯ የመምህራንን ጨምሮ መመሪያውን ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ መመሪያው በአዲሱ የምዘና ዘዴ ደረጃ ለወጣላቸው የሥራ መደቦች ደመወዝ የሚሰጥ እንጂ የደመወዝ ጭማሪ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በ2012 በጀት ዓመት ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት ይቻለው ዘንድ ዳይሬክቶሬቱን በአዲስ መልክ ለተቀላቀሉና ለነባር ሠራተኞች ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ በበጀት ዓመቱ በደንብ ልብስ አቅርቦት ላይ የሚታይ መዘግየትን ለመቅረፍ እንዲሁም በዲጂታል የሠራተኞች የሰዓት ቁጥጥር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከICT ዳይሬክቶሬት እና ከኮምፒውተር ሣይንስ ትምህርት ክፍል ጋር በጋራ ይሠራል ብለዋል፡፡ አዲሱ የደመወዝ መመሪያ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በቅጥርም ሆነ በደረጃ ዕድገት በጎደሉ መደቦች ላይ ሠራተኞችን የማሟላት ሥራ እንደሚሠራም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት @amucampus @amucampus
2019/10/16 01:03
Arba Minch University የሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የፍሬሽ ማን ኮርሶችን በየካምፓሱ ለሚያስተባብሩ አስተባበሪዎችና በሪከርድ ሠራተኝነት አዲስ ለተመደቡ ባለሙያዎች በ SMIS አጠቃቀም ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ተባባሪ ሬጂስተራር አቶ ሶፍያን አብዱልመናን እንደገለፁት አስተባባሪዎቹና ባለሙያዎቹ አዲስ እንደመሆናቸው ሲስተሙን በተሻለ ሁኔታ ማስተዳደር እንዲችሉ ለማድረግ ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡ በሥልጠናው ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ ያለው የሲስተሙ አሠራር በዝርዘር ለሠልጣኞች ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ይልማ በበኩላቸው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ወደ ተግባር እየተቀየረ በመሆኑ በተለይ ለ1ኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች የሚሰጡ የጋራ ኮርሶች ጋር ተያይዞ ለውጦች በመኖራቸው ከዚህ ቀደም የነበረውን የ SMIS ዘዴን ከአማካሪው ድርጅት ጋር በመሆን እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ ቀደም የነበረው ዘዴ እንደገና እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል፡፡ የዘንድሮውን የምዝገባ ሂደት አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር በለጠ በአጠቃላይ እንደ ሀገር በተሰሩ የግንዛቤ ሥራዎች ምክንያት የዩኒቨርሲቲያችን ነባር ተማሪዎች በተባለው ጊዜ ወደ ግቢ እንደገቡና የምዝገባ ሂደቱም በተባለው ጊዜ ተደርጎ የመማር ማስተማሩ ሥራ በወቅቱ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ ከአዲስ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ተማሪዎች በካምፓስና በት/ክፍል ደረጃ ተመድበው ከላይ ይላኩ እንደነበር አስታውሰው ዘንድሮ ግን ተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ተብለው ለዩኒቨርሲቲው ተመድበዋል፡፡ የተመደቡትን ተማሪዎች የግድ ወደ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች መመደቡ ግድ በመሆኑ ቀላል ሶፍትዌር በማዘጋጀት ከሰው ንኪኪ ነፃ በሆነ መንገድ በሎተሪ ዘዴ ተማሪዎች ወደ 6ቱም ካምፓሶች እንዲደለደሉ ተደርጓል፡፡ ምደባው ከቅሬታ ነጻ እንዲሆን አድርጎታልም ብለዋል፡፡ አሁን ላይ የክፍል ምደባ ሥራ በየካምፓሱ የተጠናቀቀ በመሆኑ የማስተማር ሥራው ጥቅምት 05/2012 ዓ/ም በይፋ እንደሚጀመር ዶ/ር በለጠ ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት @amucampus @amucampus
2019/10/16 01:02
Straight ahead to female dorm. #Main campus
2019/10/14 19:26
12ኛ አስራ ሁለተኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን የብዝኃነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እንደሚከበር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 3 የተቀመጠውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እንዲሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ተደንግጓል። መልካም ባአል @amucampus @amucampus
2019/10/14 09:44
40 Spring በአርባምንጭ ከተማ በዝርፊያ፣ በህገ-ወጥ መሳሪያና ኮንትሮባንድ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የክልሉን ሠላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ማወጁን መነሻ በማድረግ ከመከላከያና ልዩ ሃይል ጋር በቅንጅት በመስራት የቡድን ዘረፋን ጨምሮ ህገ-ወጥ መሳሪያና የተለያዩ ኮንትሮባንድ ንግዶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻለ የአርምንጭ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል መስፍን አንዳርጌ ገልፀዋል፡፡ የነዋሪውን ደህንነት ለማስጠበቅ የከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንዳለ ያሳውቁት ኃላፊው በከተማው በውህ ምንጭ ቀበሌ በተለምዶ ቆንጥር ሰፈር በሚባልበት አከባቢ ለበርካታ ጊዜያት በመመሸግ የተለያዩ ዝርፍያዎችን ሲፈፅሙ የቆዩና የነዋሪውን የቤት እንስሳ ሰርቀው በማረድ ለሆቴሎች በሽያጭ ሲያከፋፍሉ የነበሩ 12 ግለሰቦች ለእኩይ ተግባራቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙበትን ገጀራና ሰንጢዎች ፤ አደንዛዥ እፆች እንዲሁም ስልክና የተለያዩ ክህብረተሰቡ የዘረፏቸው ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በኤግዝብትነት መያዛቸውን አሳውቀዋል፡፡ ምንጭ፦ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን @amucampus @amucampus
2019/10/14 00:03
#Arbaminch ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤትና ከውጭ ሃገር የመጡ የቴክኒክ አባላት በአርባምንጭ ከተማ ለሚገነባው ስመጥርና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታ ጅማሮ የሚሆን የቦታ መረጣና ቅኝት ስራዎችን አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ለህዝብ እንደራሴ አባላት በአፍሪካ ሲሼልስ ከሚገኘው ግዙፉ ሆቴልና ሪዞርት በመቀጠል በአርባምንጭ ከተማ ስለሚገነባው ሆቴልና ሪዞርት ገለፃ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ https://telegra.ph/ETH-10-13 ምንጭ፦ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን @amucampus @amucampus @tberhanu
2019/10/13 11:47
☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝☝የተማሪዎች አቀባበል እንዲህ ነበር ከጥቂቱ በትንሹ እናመሠግናለን ብርቅዬ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ማህበረሰብ @amucampus @amucampus @asutiiii
2019/10/12 18:09
የ2012 ዓ/ም አገራዊ የከፍተኛ ጥምህርት ተቋማት ውይይት በዩኒቨርሲቲው ተካሄደ ‹‹ለሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መስፈን የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች አገራዊ የማኅበረሰብ ውይይት መስከረም 14 ተካሂዷል፡፡  የ2011 ዓ/ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2012 ዓ.ም ዕቅድ፣ በፍኖተ ካርታ ጥናት ግኝት መሠረት ተቋማትን በተልዕኮና በልህቀት ልየታ አተገባበርና ፋይዳው፣ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚወስዷቸው የትምህርት ዓይነቶችና ፋይዳቸው፣ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ማረጋገጥና ማዝለቅ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሚናና በየደረጃው ያለውን ኃላፊነትና ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ የመምህራንና የተማሪዎች ዲስፕሊን መመሪያ የውይይቱ ይዘቶች ናቸው፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እንደገለጹት የውይይቱ ዓላማ በ2012 የትምህርት ዘመን ህግና ሥርዓትን በዩኒቨርሲቲው የበለጠ አጠናክሮ በመተግበር ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስፈንና ማስቀጠል ነው፡፡ ከ2012 ትምህርት ዘመን ጀምሮ በዩኒቨርሲቲ ትምህርት 3 ዓመት የነበረው ዝቅተኛ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም 4 ዓመት የሚደረግ ሲሆን የሙያ ሥነ-ምግባር ኮርሶች በእያንዳንዱ የትምህርት መርሃ-ግብር ተካተው ይሰጣሉ፡፡ ተማሪዎች አገራቸውንና አካባቢያቸውን እንዲያውቁና እንዲረዱ፣ ለሙያ መስመር የሚያዘጋጁ ኮርሶችም የ21ኛውን ክ/ዘመን ክህሎት በሚያጠናክር ሁኔታ የ1ኛ ዓመት የትምህርት ፕሮግራም መቀየሱ ተገልጿል፡፡ የመምህራንና የቴክኒክ ረዳቶች ቅጥርና ስልጠና፣ የቤተ-ሙከራዎች ግብዓትና አደረጃጀት ማሻሻል፣ ዲጂታል ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት በማንኛውም ሥፍራ ለተገልጋይ ተደራሽ ማድረግ፣ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላት፣ ካምፓሶችና ኮሌጆች ከማዕከል ጋር ተናበው ዕቅድ ማዘጋጀትና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ በዝግጅት ምዕራፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ናቸው፡፡ የኢንተርኔት መቆራረጥ፣ የቢሮና የኮምፒውተር እጥረት፣ በተማሪዎች አካባቢ የሚታይ የኃይማኖትና የብሔር ጽንፈኝነት፣ በካምፓሶች ዙሪያ የጫትና መሸታ ቤቶች መስፋፋት፣ መምህራን ለትምህርት ሲሄዱ ወጥ የሆነ አሠራር አለመኖር፣ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተማሪዎችን በአግባቡ እየገመገመ አለመሆን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው በውኃ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሠራ እንደመሆኑ የማኅበረሰቡን የንፁህ ውኃ ችግር ለመፍታት የሚያከናውናቸውን ሥራዎች አስመልክቶ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡ በተጨማሪም የማኅበረሰብ አገልግሎት አገር በቀል እውቀቶች፣ መድኃኒቶች እና ባህላዊ እሴቶች ላይ በትኩረት እንዲሠራ፣ የሥነ-ምግባር ችግር ያለባቸው ሠራተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ፣ ችግር ፈቺ ምርምሮች የአስተዳደር ሠራተኞችንም እንዲያሳትፉ እንዲሁም ለአስተዳደር ሠራተኞች በየዓመቱ የሚሰጠው የ2ኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል ቁጥሩ ከፍ እንዲል አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ የመምህራን ልማት ስብጥር በተለይ የ3ኛ ዲግሪ መምህራን ቁጥር ለማሳደግ በትኩረት መሥራት፣ ከትምህርት ጥራትና መልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ጋር በየጊዜው ውይይቶችን በማካሄድ ክፍተቶችን ማስተካከል፣ በተማሪዎች ንብረት ላይ የሚፈፀም ስርቆት፣ ቅሚያና አካላዊ ጥቃትን ማስቀረት እንዲሁም ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል ከተማሪዎች አደረጃጀት፣ ከአካባቢው አስተዳደርና ከማኅበረሰቡ ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ በለውጥ መሣሪያዎች በተለይ በካይዘንና ሚዛናዊ ውጤት ተኮር ሥርዓት የሥራ አፈፃፀም ምዘና ማከናወን፣ የምርምር ውጤቶችን ማላመድና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ማኅበረሰብ ማሸጋገር፣ የገቢ ማመንጫ አማራጮችንና አሠራሮችን በማሻሻል ገቢ ማሳደግ፣ ነባር የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና አዲስ የተጀመሩ በውል መሠረት እንዲፈፀሙ መከታተል እና የግዥ ሥራ አፈፃፀምን ማቀላጠፍ በተጨማሪ የሚሠሩ ይሆናል፡፡ ከብዛት ወደ ጥራት፣ ከቅድመ ምረቃ ወደ ድኅረ-ምረቃ፣ ከትምህርት ተኮር ወደ ምርምርና ፈጠራ ተኮር፣ ከማኅበረሰብ አገልግሎት ወደ ማኅበረሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እና ከዘልማዳዊ የትምህርት አሰጣጥ ወደ ቴክኖሎጂ ተኮር መሸጋገር በ2012 ዓ.ም የተለዩ 5 አበይት የለውጥ ትኩረት አጀንዳዎች ናቸው፡፡ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት @amucampus @amucampus
2019/10/12 01:11
AMU community rejoices in Dr Abiy Ahmed’s Noble Prize victory Leading officials and entire university community, AMU President, Dr Damtew Darza, congratulated Prime Minister, Dr Abiy Ahmed, for winning The 2019 Noble Peace Prize for phenomenal efforts in ending hostility with bitter foe Eritrea in a short span of assuming his office. He said, we are proud of him and certainly strive hard to play constructive role in ensuring overall development of Ethiopia. Expressing delight, he said, it’s not only the matter of great pride and happiness for Ethiopia, but also for entire Horns of Africa as it will strengthen our collaboration with Eritrea, Djibouti, Sudan and Somalia. It will keep the momentum up to sustain peace as it’s important next to the physiological needs of human beings and that’s what he has achieved. Dr Damtew stresses that he has an inimitable style, great political acumen and humane understanding; he employs effective strategy to deal with problems and gets into the bottom to understand disputes and unsolvable political stalemate and with consensus he resolves them. And I am sure, under his leadership, Ethiopia will achieve development on all counts. His unprecedented feat will have cascading impact on people across Ethiopia and East Africa; at AMU, we are fortunate to represent a rainbow reflecting every colors of the society and we will continue to contribute best for peaceful co-existence, he quipped. For Academic Affairs Vice President, Dr Yechale Kebede, this astounding achievement belongs to entire Ethiopia and we love him for he has brought laurels to entire nation. This recognition will help us to create positive synergy that will help us to eliminate poverty and become middle-level nation. Similarly, we need strong framework to foster diversity, which is very important for country like Ethiopia. And especially, in my arena, as a leader, I will put in more efforts to bring fruitful results to enhance the quality of education, produce competent graduates and this award will energize us for the same, he adds. Research and Community Service Vice President, Dr Simon Shibru, said, showering praise on Dr Abiy for gaining this Noble Prize, he said, our Prime Minister has endeared himself with many by connecting with Ethiopian Diaspora spread across the globe. The most important thing is that he has put Ethiopia on the world map but now it’s time to look into wider dimension of internal issues that will ultimately bring peace and ensure economic growth. Administrative Vice President, Dr Melkamu Mada, said, in Dr Abiy Ahmed, we all are winners as entire Ethiopia had shown willingness to establish friendly relation with Eritrea. Moreover, this recognition is very timely, as at this juncture we are in the transition phase and AMU as an academic institute will contribute in sustaining peace so that teaching-learning and allied services can be carried out successfully. Scientific Directors of Institute of Technology and Water Technology Institute, Dr Alemayehu Chufamo and Dr Abdella Kemal expressing their deep pleasure said that our prime minister has set the example by leading from the front and we would love to follow his footsteps in doing things differently to make the difference. Academic, administrative staff, students’ fraternity and others have joined the chorus of congratulating beloved Prime Minister in becoming a unique phenomenon in Ethiopian history, in the pursuit of peace. (Corporate Communication Directorate) @amucampus @amucampus
2019/10/12 01:09
እንኳን ደስ አላችሁ, አለን!! የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2019 የኖቬል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ በ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ስም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ አለን ለማለት እንወዳለን! @amucampus @amucampus
2019/10/11 21:37
ሰላም ለሁላችን በድጋሜ እንኳን ለ 2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን በተጨማሪ አዲስ እየገባችሁ ላላችሁ ተማሪዎች እንኳን በደህና ወደ ቤታቸሁ መጣችሁ እያልን @amucampus ቻናል አንድ አመት አስቆጥሯል ይሄ ቻናል ከ ተማሪ ለ ተማሪ አዲስ እና ፈጣን በተጨማሪም እውነተኛ መረጃን በማሰራጨት ይታወቃል ወደፊትም ይቀጥላል ይሄን የ ተማሪ ቻናል በ ዋናነት የሚመሩት ከየ ከምፓሱ የተውጣጡ ተማሪዎች ናቸው @tberhanu @asutiiii @miko1122 @Josi @newneway እነዚህን ተማሪዎች በ ቻናላችሁ ስም እያመሰገንን በዚህ በያዝነው አመት በአሪፍ እና በቀለጠፈ ዘዴ እንደምንሰራ ተስፋ እያደረግን ሰላም በያላችሁበት ሃሳብ እና መስተካከል አለበት የምትሉት ነገር ከለ አድርሱን፡፡ @amucampus @amucampus
2019/10/11 21:20
ውድ የ አምዩ አበያ ካምፓስ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን በሰላም ወደ ካምፓሳችን መጣችሁ እያልን በ ካፌ ኦረንቴሽን በ 1/02/2012 ጠዋት ሰለሚሰጥ ሁላችሁም እንድተገኙ እናሳስባለን ም፡-ዳነ @amucampus @amucampus
2019/10/11 18:19
ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል የዛሬዋ የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ “ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” – Brian Tracy አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡ የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡ “ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau “የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts “ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” Source Dr_MehretDebebe @amucampus @amucampus @tberhanu
2019/10/11 10:12
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጊቢያችንን እንዴት አያችሁት 😍😜👎😠😭🙈🙉🙊
2019/10/10 21:18
pin message
2019/10/10 18:46
AMU hosts two-day training on ‘New Education Roadmap’ AMU has hosted 2-day training on strategic issues linked with New Education Roadmap on the theme - ‘Sustain peaceful teaching-learning environment across university’ from 24th to 25th September, 2019, for entire university’s academic and administrative staff at Main Campus. Both freshmen and senior students were also oriented; while Sawla Campus imparted training to its community on October 1, 2019. University President, Dr Damtew Darza, chairing training for academic staff with AMU Board member, Dr Abraham Alano, emphasized that, this academic year, AMU is determined to achieve 9:76:15 ratio of Undergraduate, Post-Graduate and PhD teachers to reinforce teaching-learning process. This time quality is our mainstay, where research, technology and professionalism will be its core components. In order to improve administrative machinery, performance tools like Kaizan, Balanced Score Card System, etc. will be strengthened. He informed that AMU could successfully complete Job Evaluation and Grading (JEG) process, 65% staff members applied for suitable positions were duly placed along with 35%, assigned new positions by JEG Committee while 13 disputed cases are being adjudicated. And under career development program around 272 academic and 15 administrative staff were given aid to build their capacity. Academic Affairs Vice President, Dr Yechale Kebede, orienting administrative staff, said, Ministry of Education is now engaged in differentiating universities in the country based on their respective available strength. It will assign or put universities in three identified categories defining their academic relevance and it will demand accountability on all higher education institutions so that they move in right direction, building capacity and disseminate qualitative education for nation development. He adds that New Education Roadmap guidelines specify that hereafter duration of UG program will be of 4-year, of which 1st year for all new entrants will be significant to learn common courses designed to address key issues like communicative skills, logical thinking, mathematical aptitude, etc. It intends to make graduates more competent and responsible about the society; emerging market needs and nation as a whole, so that they can prepare themselves to accept any challenge in any arena. It’s learnt that under common courses, freshmen would have to take yearlong orientation on subjects such as global trends, inclusiveness, critical thinking, introduction to emerging technology, social anthropology, communicative English, moral & civics, etc. AMU Board member, Dr Hewan Demissie, Vice Presidents, Dr Melkamu Mada and Tarikua Woldemedhin including Institute of Technology and Water Technology Institute’s scientific directors, Dr Alemayehu Chufamo and Dr Abdella Kemal, put in efforts in orienting AMU staff at different venues. The community training basically had more emphasize on core agenda to sustain peaceful teaching-learning environment by making all stakeholders aware about its relevance; issues like teacher-student discipline, performance of last year’s (2018-19 Plan) and New Year’s (2019-20) Annual Plans were also dealt with. (Corporate Communication Directorate @amucampus @amucampus
2019/10/10 10:06
ሰላም ለሁላችን በድጋሜ እንኳን ለ 2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን በተጨማሪ አዲስ እየገባችሁ ላላችሁ ተማሪዎች እንኳን በደህና ወደ ቤታቸሁ መጣችሁ እያልን @amucampus ቻናል አንድ አመት አስቆጥሯል ይሄ ቻናል ከ ተማሪ ለ ተማሪ አዲስ እና ፈጣን በተጨማሪም እውነተኛ መረጃን በማሰራጨት ይታወቃል ወደፊትም ይቀጥላል ይሄን የ ተማሪ ቻናል በ ዋናነት የሚመሩት ከየ ከምፓሱ የተውጣጡ ተማሪዎች ናቸው @tberhanu @asutiiii @miko1122 @Josi @newneway እነዚህን ተማሪዎች በ ቻናላችሁ ስም እያመሰገንን በዚህ በያዝነው አመት በአሪፍ እና በቀለጠፈ ዘዴ እንደምንሰራ ተስፋ እያደረግን ሰላም በያላችሁበት ሃሳብ እና መስተካከል አለበት የምትሉት ነገር ከለ አድርሱን፡፡ @amucampus @amucampus
2019/10/10 09:36
#Dave MGK ትንሻ ቤታችን ከ እድሜ ዘመናችን ተካፍላ ልታስተምረን እና የ ሕይወት አቅጣጫችንን ልታበጅ መልካም ፍቃድዋን ገልጻ እነሆ ዛሬ አዲስ ተማሪዎች ልትቀበል ነው እማዩ😍 አደራዋን አትብሉ ጠንክራችሁ ተማሩ🙏 WELL COME ALL FRESH STUDENTS 👌 AMU @amucampus @amucampus
2019/10/10 09:17
ልጄ አደራህን ተቸግሬ ተርቤ አንጀቴን አስሬ ነውና ያስተማርኩ ሁሌም እኔ ደሃ እናትህን አስብ ትምህርት ላይ ብቻ አተኩር ሳልማር ተቸግሬ ያስተማርኩህን እናትህን አስብ። መልካም ትምህርት ም፡-ዴቭ @amucampus @amucampus
2019/10/10 09:12
👇👇👇👇👇👇👇 @amucampus
2019/10/09 22:37
Ke id kutrachu chmr nw eyut teregaguna yetemedebachubet gibim ale kelay lelelochm share adrgulachew lelam mereja endederesen enadersachualen melkam yetmhrt zemen @amucampus @amucampus @asutiiii
2019/10/09 22:35
እስኪ campus በዚህ @miko1122 ያወቃችሁ👍 ያላወቃችሁ👎🏽 ጥያቄ ያልተመለሰላችሁ🤷‍♂ አሁንም ቢሆን ለኩልን በቻልነው ፍጥነት እናሳዉቃለን . . . @miko1122 @miko1122 @miko1122 . . . JOIN US @amucampus @amucampus
2019/10/09 14:38
ሰላም ሰላም ውድ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አዲስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው ስትገቡ Main campus መምጣታችሁ እንዳለ ሆኖ የተመደባችሁበትን campus ለማወቅ እና የሚፈጠረውን መጨናነቅ ለመቀነስ ስማችሁን እስከነ አያት እና Natural or Social የሚለውን በዚህ ብትልኩልን የምናደርስ መሆኑን እንገልፃለን @miko1122 @miko1122 @miko1122 @miko1122 . . . @amucampus @amucampus
2019/10/09 12:19
#FAKE የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከላይ የምትመለከቱ የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪን የሚመለከተው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ አሳውቋል። "ETHIOPIA UNIVERSITY NEWS" ይህን ገፅ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አያውቀውም። #ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ @amucampus @amucampus @asutiiii
2019/10/09 09:48
♥የበጎነት ስራ ጥሪ♥ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከፈታችን ሮብ ከ28/2012_29 ድረስ አዲስ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን ይቀበላል እና እነዚህን ተማሪዎች ግቢ በሚገቡበት ቀን የአምዩ ክበባት እና ማዕከላን ቅደመ ዝግጁት አጠናቀዋል ወድ የጊቢያችን ተማሪዎች በዚህ ኢትዮጰያነት በሚሸተው የእንግዳ ተቀባይነት ባህል መሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች ከነገ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ charity biro ጋር እንገናኘ፡፡ @amucampus @amucampus @asutiiii
2019/10/09 09:20
ብርቅዬ አዲስ የ አምዩ ተማሪዎች እንኳን በሰላም መጣችሁ በ ጉዞም ላይ ላላቻሁ መልካም መንገድ አዲስ ተማሪዎች ሜን ዋናው ጊቢ ስትደረሱ መውረድ አለባችሁ ጊቢው በራሱ bus በየካምፓሱ ያሰራጫል ለበለጠ መረጃ @newneway @asutiiii @amucampus @amucampus
2019/10/09 08:24
ውድ የ አምዩ ተማሪዎች chris yali በ Computer science ከ አምዩ በ 2011ዓ.ም የተመረቀ ሲሆን አሁን ላይ addis music በመስራት ለኛ ለ ውድ ተማሪዎች አበርክቷል ያለምን ከልብ እናመሰግናለን ተማሪዎች እናዳምጥለት chris yali hawasa @amucampus @amucampus
2019/10/08 22:28
♥የበጎነት ስራ ጥሪ♥ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከፈታችን ሮብ ከ28/2012_29 ድረስ አዲስ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን ይቀበላል እና እነዚህን ተማሪዎች ግቢ በሚገቡበት ቀን የአምዩ ክበባት እና ማዕከላን ቅደመ ዝግጁት አጠናቀዋል ወድ የጊቢያችን ተማሪዎች በዚህ ኢትዮጰያነት በሚሸተው የእንግዳ ተቀባይነት ባህል መሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች ከነገ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ሪጂስትራል አከባቢ እንገናኘ፡፡ @amucampus @amucampus
2019/10/08 19:06
አዲስ ገቢ የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ቻናል ተቀላቀላቹ እያልን የቻናሉ አባል ላልሆኑት ሊንኩን ሼር በማድረግ ለጓደኞቿቹ አድርሱልን 👇👇👇👇👇 @amucampus @amucampus @asutiiii
2019/10/08 18:45
የተስተካከለ! የ2012 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት⬆️ ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚያመሩ ተማሪዎች I. የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ዋናውን እና ሁለት ኮፒዎች፣ • የ8ኛ ክፍል (ሚኒስትሪ) ሰርተፊኬት • የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬቶች • ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት II. 8 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ (የቅርብ ጊዜ) III. አንሶላ እና ብርድ ልብስ IV. የስፖርት አልባሳት (ጫማን ጨምሮ) ** ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የሚኖራቸውን ቆይታ ሰላማዊ ለማድረግ የተማሪ ወላጆች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የዋስትና ውል እንዲገቡ መደረጉ ይታወቃል። ስለዚህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚሄዱበት ወቅት ወላጆቻቸው የተፈራረሙበትን ሰነድ ይዘው እንዲገኙ ዩኒቨርሲቲዎቹ ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ሰነዶቹን ከየሚኖሩበት ወረዳ መውሰድ ይችላሉ። ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ሲጠሩ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ሲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ቀናት ላይ የጊዜ ለውጥ ካለም ለውጡን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። Via #ETV @amucampus @amucampus
2019/10/08 18:40
በችግሮችህ ላይ ያለህ እይታ ምን ይመስላል? “ጉዞው ሲበረታ፣ ብረቱዎች ጉዟቸውን ይቀጥላሉ” በአሁን ሰዓት እኔና አንተ የምንጋራቸውን ነገሮች እንዘርዝር ብንል ብዙ ሁኔታዎችን እናገኛለን፡፡ ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዱ “ችግር” የሚባለው ጉዳይ ነው፡፡ ሁላችንም ብንሆን በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ችግሮችን እንጋፈጣለን፡፡ ችግርን በመጋፈጥ ደረጃ አንድ ስንሆን፣ የምንለያየው በችግራችን ላይ ባለን አመለካከት ነው፡፡ ችግሮችህ ከአቅምህ ቢበልጡ ኖሮ ባለፉት ሁኔታዎችህ ተውጠህ በቀረህ ነበር፡፡ አንተ ማንኛውም ሰው ካሉበት ችግር አልፎ የመሄድ ብቃት እንዳለው ከሚያመላክቱ ዋነኛ ምልክቶች አንዱ ነህ፡፡ አንድናድ ጊዜ ግን ችግሮችህ ያየሉና ከአቅምህ በላይ እንደሆኑ ልታስብ ትችላለህ፡፡ ይህ የመሸነፍ ስሜት ከተለያዩ ተጽእኖዎች ሊመጣ ይችላል፡፡ ከሚከተሉት አጉል ተጽእኖዎች ነጻነትህን አውጅ፡- 1. የሌሎች ልምምድና ሁኔታ ተጽእኖ አሁን በሕይወትህ የሚጋፋህ ችግሮች ከዚህ በፊት በሌሎች ሰዎች ላይ ያስከተሉትን አስከፊ ሁኔታዎች ስታስብ የፍርሃት ስሜት ሊያጠቃህ ይችላል፡፡ አንድ ችግር ሌላውን ሰው አሸነፈው ማለት ግን አንተን ያሸንፍሃል ማለት አይደለም፡፡ 2. የግልህ ልምምድና ሁኔታ ተጽእኖ አሁን የተጋፈጥከው ችግር ከዚህ በፊት ጎድቶህ ካለፈ አሁንም ያው ሁኔታ የሚደገም ስለሚመስልህ ፍርሃት ሊጫጫንህ ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ከመፍራት ይልቅ ሁኔታው ከዚህ በፊት ሳያሸንፍህ እዚህ መድረስህ ላይ ማተኮርን ምረጥ፡፡ 3. የመሰረተ-ቢስ ፍርሃት ተጽእኖ አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ራሱ ያስፈራናል፡፡ በውስጥህ የሚሰማህን ፍረሃት ምንጭ ለማወቅ ብትሞክር እንኳ ላታገኘው ትችላለህ፡፡ ይህ አይነቱ ፍርሃት እንዲያደክምህ ግን መፍቀድ የለብህም፡፡ መፍራትህን በመፍራት አትንበርከክ፡፡ አደጋው ያለው ፍርሃት ላይ ሳይሆን ለፍርሃት የምትሰጠው ምለሽ ላይ ነው፡፡ በቅንነት ሼር ያድርጉ 👇 http://t.me/amucampus
2019/10/07 19:10
#ቻርለስ_ዲክሰን "በጣም ትንሿ ቁልፍ ግዙፉን በር ትከፍታለች" ይለናል፡፡ እውነት ነው ጠብታ ፍቅር የማትሽረው በደልና ጥላቻ የለም፡፡ ሰዎች ስለጠሉክ አትጥላቸው፡፡ ይልቁንም እየጠልኩ ውደዳቸውና በውስጥክ ያለው ልብ መሆኑን አሳያቸው፡፡ ሰውን በፍቅር እንደማሸነፍ የሚያስደስት ነገር የለም፡፡ JOIN❤️ @amucampus @amucampus @tberhanu
2019/10/07 12:58
ለቤተ-መጽሐፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ነባርና አዲስ ሠራተኞች ሥልጠና ተሰጠ የዩኒቨርሲቲው ቤተ-መጽሐፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአዲሱ የነጥብ ሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን (JEG) በሥሩ በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተመደቡና ለነባር 170 ሠራተኞች የቤተ-መጽሐፍት ዓይነቶችና ምንነት፣ አደረጃጀት፣ ህግና ደንብ፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ደንበኛ አያያዝ፣ የቴክኒክ ክፍሎች እንዲሁም ዲጂታላይዜሽንና አውቶሜሽን፣ ዶክዩሜንቴሽን እና ማጣቀሻ በሚሉ ርዕሶች ላይ ጳጉሜ 4-5/2011 ዓ/ም የሥራ ላይ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡  የዳይሬክቶሬቱ የደንበኞች አግልግሎት ቡድን መሪና የዳይሬክተር ተወካይ አቶ እንግዳ አሰፋ ሥልጠናው የሠራተኞችን አቅም በማጎልበት ለተማሪዎች፣ ለተማራማሪዎች፣ ለአስተዳደር ሠራተኞች እና በአጠቃላይ ወደ ዩኒቨርሲቲው ለሚመጡ ደንበኞች ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ እንደ አቶ እንግዳ ገለጻ መረጃ የሰው ልጅ አይቶ ወይም አንብቦ ሊረዳው በሚችልና ትርጉም በሚሰጥ መልኩ ተቀናብሮ ስለ አንድ ጉዳይ እውቀት ሊያስጨብጥ የሚችል፣ በወቅቱ የተሰበሰበና የተደራጀ እንዲሁም በተፈለገው ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውል ነው፡፡ የቤተ-መጽሐፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ6ቱም ካምፓስ ዶክዩሜንቴሽን ቡድን መሪ ወ/ሮ ወለቱ ገብሬ በበኩላቸው ሥልጠናው የተጠቃሚዎችን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ መረጃዎችን በማሰባሰብና በማደራጀት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ባለሙያዎችን የሚያበቃ መሆኑን ገልዋል፡፡ ከተሳታፊዎች መካከል ወ/ሪት ቆንጂት ቆልቻ ሥልጠናው በሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሠልጣኝ አቶ ዘሪሁን ድርባቤ በበኩላቸው በተለይ በሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ በውስጠ ደንብ፣ በደንበኛ አያያዝና በመረጃ አያያዝ በተግባር የታገዘ ትምርት እንዳገኝ አግዞኛል ብለዋል፡፡ ከስልጠናው ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሸ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት @amucampus @amucampus @newneway
2019/10/07 10:37
አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ለአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ቀን መስከረም 28 እና 29 እንዲሆን ወስኗል፡፡ 👇👇👇👇👇 JOIN @amucampus @amucampus @miko1122
2019/10/06 21:48
Welcome to arbaminch university student
2019/10/02 09:54
Zed , Naol habtamu , bruka yee , iman enamesegnachualen adis gebiwochachn endaydenagetuna gra endaygebachew bmideregew astewatso enamesegnachualen adadis gebi temariwochn wedechanalachn bemegabez yebekulachenn enweta @amucampus @amucampus
2019/09/29 17:18
Trip shayi
2019/09/29 17:12
Iman enamesegnalen
2019/09/29 17:10
1