Bleacher Report Football


536 Members

ስለ ሁሉም ሊግ ሚዘገብበት ፣ ጨዋታዎች በቀጥታ ስርጭት ሚተላለፉበት ፣ የዝውውር ዜናዎችም ሳይቀሩ ሚነገሩበት ምርጥ ቻናል እንዳያመልጣቹ።
#ምርጫቹ@Bleacher_Football ብቻ ይሁን

ሀሳብ አስተያየት(0924621529 ) @Yaredtg በስልክ ቁጥር


የስፖርት መረጃ ለማግኘት ትክክለኛው አማራጭ
{links} {LinksTitle}
{/links}
Today Views : 3
Yesterday Views : 1
One Year Views : 101
በእለቱ ከታዩት ምስሎች መካከል። @Bleacher_Football
2019/06/14 20:14
👌የሀዛርድ ማሊያ በሳንቲያጎ በርናባዉ ሲታተም። @Bleacher_Football
2019/06/14 20:14
😲Eden Hazard ይፋዊ ትዉዉቅን ለመከታተል በ 50ሺ ደጋፊዎች በ Santiago Bernabeu ተገኝተዉ እንደነበር ተስተውሏል። @Bleacher_Football
2019/06/14 20:13
👉Hazard በሳንቲያጎ በርናባዉ ኳስ ሲያንጠባጥብ @Bleacher_Football
2019/06/14 20:13
🍎በሪያል ማድሪድ የመጫወት ህልሜ እጅግ በማጣም ጥልቅ ነበረ ባንዴዉም ደጋፊዉ እንዲህ ይወዳኛል ብዬ አልጠበኩም ነበር። @Bleacher_Football
2019/06/14 20:13
🌎እለተ ሰኞ የወጡ አዳዲስ ስፖርታዊ መረጃዎች። ✏️አንቱአን ግሬዝማን ከ ባርሴሎና ይልቅ ለ PSG የመፈረም እድሉ ሰፊ እንደሆነ Marca አስነብቧል :: ✏️የ ማንችስተር ዩናይትዱ አማካኝ Juan Mata ስሙ ከ ባርሴሎና ጋር እየተያያዘ ይገኛል ኮንትራቱም ከ 20 ቀናት በሗላ ያበቃል :: [ Marca ] ✏️የ ኢንተር ሚላኑ አለቃ አንቶንዮ ኮንቴ የ ሪያል ማድሪዱን ተጫዋች ሉካስ ቫስኩየዝ በ 30 ሚሊየን ዩሮ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል :: [ Marca ] ✏️ከ ወደ ጣልያን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ አትሌቲኮ ማድሪዶች የ ኤሲ ሚላኑን የክንፍ ተጫዋች Suso ን ለማስፈረም ይፈልጋሉ :: [ Marca ] ✏️ማን.ዩናይትዶች ስፔናዊው የ28 አመት ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደ ሂያ በዚህ የዝውውር መስኮት ላይ ፒ.ኤስ.ጂን የሚቀላቀል ከሆነ የ £20m ክፍያ ይፈፅሙለታል። (sun) ✏️አሌክሳንደር ኮላሮቭ ለ ሮማ የልቀቁኝ ደብዳቤ ማስገባቱ ተነግሯል ወደ ኢንተር ሚላን ለመዘዋወር :: [ Marca ] ✏️የሊዮኑ የግራ መስመር ተከላካይ ፈርላን ሜንዲ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ለመሆን የህክምና ምርመራውን ማድረጉ ይታወሳል ሆኖም የክለቡ ዶክተሮች በተጫዋቹ የህክምና ውጤት ጥርጣሬ ውስጥ ገብተው ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ለ ረቡዕ (June 12) ሌላ ቀጠሮ ይዘዋል! ✏️የ33 አመቱ የማን.ሲቲ አማካይ ዴቪድ ሲልቫ በቀጣዩ አመት በኢትሃድ ስቴዲየም የመታሰቢያ ጨቃታ ይደረግለታል። የስፔናዊው ኢንተርናሽናል ኮንትራት በቀጣዩ አመት የሚጠናቀቅ ሲሆን የእግር ኳስ ህይወቱን በላስ ፓልማስ ማጠናቀቅ ይፈልጋል። (Sun) ✏️ኤሲ ሚላኖች በ £30m የዝውውር ሂሳብ አማካዩን ፍራንክ ኬሴን ለመልቀቅ ፍቃደኞች ሆነዋል። አርሰንናል፣ ቶተንሃም እና ቼልሲዎች የተጭዋቹን ፊርማ ለማግኘት ሁኔታውን በቅርበት በመከታተል ላይ ናቸው።(Sunday Express) ✏️”ሎስ ብላንካዎቹን ወደ ቀደመ ዝናቸው ይመልሳቸዋል” ክርስቲያኖ ሮናልዶ በርካታ ጀብዶችን ለመፈጸም እንደሚችል እና ሪያል ማድሪድን ወደ ቀደመ ዝናው መመለስ እንደሚችል አስባለው ፣ ከኳስ ጋር ያለው ቁርኝት ባላንዶርን በበርናቦው የሚያሸንፍበት እድል እንዳለም ሌላ ማረጋገጫ ነው ፣ በቀጣዮቹ አመታት ትልቁን ሽልማት ባላንዶርን ለማሸነፍ እድሉ የሰፋ ነው። መልካም እድል ኤደን ሀዛርድ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የቤልጅየማዊውን ኮከብ ኤደን ሀዛርድ በርናቦው መድረስ ተከትሎ የተናገረው ነው። ✏️ናፖሊዎች የኢንተርሚላኑን አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ ማስፈረም ካልቻሉ በምትኩ የቶሪኖውን አንድሪያ ቤሎቲ አስበዋል፡፡ ኢንተሮች ኢካርዲን ለመሸጥ የወሰኑ ሲሆን እስከ 100 ሚ. ዩሮ ለአጥቂው ይፈልጋሉ፡፡ ይሁንና ናፖሊዎች ይህን የመክፈል እቅድ የላቸውም፡፡ ክፍያው የማይቀንስ ከሆነ ደግሞ በ60 ሚ. ዩሮ ቤሎቲን ለማዘዋወር አቅደዋል፡፡ (ካልሺዮ መርካቶ) ✏️OFFICAL:ፍራንኪ ዲዮንግ የNATIONS LEAGUE ውድድር ምርጥ ተጫወች በመባል ተመርጧል። ✏️በርናዶ ሲልቫ ገድል ከእንግሊዝ እስከ መላው አውሮፓ በርናንዶ ሲልባ በተያዘው የውድድር አመት በግል ደረጃ ያሳካቸው ክብሮች ከየትኛውም ተጫዋች በላይ ያደርገዋል። በክለቡ ማንቸስተር ሲቲ እና ሀገሩ ፖርቹጋል ስኬት የአንበሳውን ድርሻ የተወጣው ትንሹ ቅመም ራሱን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯል። 👉ፕሪሚየር ሊግ 👉ኤፍ ኤ ዋንጫ 👉ካራቦው ዋንጫ 👉ኮሙኒቲ ሽልድ የማንስተር ሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ የዩኤፋ ኔሽስ ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ስኬታማ አመት በርናንዶ ✏️ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሊዮኒየል ሜሲ ፣ ሰርጅዮ ራሞስ አሊያ ጋሬዝ ቤል የማንቸስተር ዩናይትድን ችግር ሊቀርፉ አይችሉም ዎይን ማርክ ሮኒ ሮኒ ይቀጥላል “አንድ ወይም ሁለት ተጫቾችን በ 100 ሚሊዮን ፖዉንድ ማስፈረም ለማንችስተር ዩናይትድ ስኬት በቂ አይደለም። በአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ ለዲሲ ዩናይትድ እየተጫወተ የሚገኘው ዋይን ማርክ ሩኒ ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ የዉጤት ቀዉስ አስመልክቶ አስተያየት የሰጠ ሲሆን ክለቡ አንድ ወይም ሁለት ተጫዋቾችን ኮኮቦችን ብቻ በ 100 ሚሊዮን ፖዉንድ ማስፈረም በቂ አለመሆኑን ተናግሯል። የቀያይ ሰይጣኖች የምንግዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ዋይን ማርክ ሩኒ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የክለቡን ስኬት ለመመለስ አምስት አሊያ ስድስት ተጫዋቾችን ማስፈረም ብቸኛው መፍትሔ ነው ሲል ምክር አዘል መልእክቱን አስተላልፏል። ┄┅┄✶⚽️✶┄┅┄ ┄
2019/06/10 14:48
👉ማትያስ ዴላይት ፦ ከጨዋታው በኋላ ክርስትያኖ ወደ ጁቬንቱስ እንድመጣ ጠይቆኛል ሲል ተናግሯል። ┄┅┄✶⚽️✶┄┅┄
2019/06/10 14:47
📌እንግሊዛዊው አማካይ ጄሴ ሊንጋርድ በኦልትራፎርድ ለተጨማሪ አመት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት እንዲፈርም በሳምንት £130,000 የሚያስገኝለትን ሳምንታዊ ደሞዝ ከማንችስተር ዩናይትድ ሊቀርብለት ነው።(Sun on Sunday)
2019/06/09 10:59
👉 "ሎስ ብላንካዎቹን ወደ ቀደመ ዝናቸው ይመልሳቸዋል" ክርስቲያኖ ሮናልዶ 📌በርካታ ጀብዶችን ለመፈጸም እንደሚችል እና ሪያል ማድሪድን ወደ ቀደመ ዝናው መመለስ እንደሚችል አስባለው ፣ ከኳስ ጋር ያለው ቁርኝት ባላንዶርን በበርናቦው የሚያሸንፍበት እድል እንዳለም ሌላ ማረጋገጫ ነው ፣ በቀጣዮቹ አመታት ትልቁን ሽልማት ባላንዶርን ለማሸነፍ እድሉ የሰፋ ነው። መልካም እድል ኤደን ሀዛርድ 📌ክርስቲያኖ ሮናልዶ የቤልጅየማዊውን ኮከብ ኤደን ሀዛርድ በርናቦው መድረስ ተከትሎ የተናገረው ነው።
2019/06/09 10:59
📌ማንችስተር ዩናይትድ የ 29 አመቱን ዌልሳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ጋሬዝ ቤልን በውሰት ከሬያል ማድሪድ የመውሰድ ፍላጎት አላቸው።(Sunday Mirror)
2019/06/09 10:59
📌ናፖሊዎች የኢንተርሚላኑን አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ ማስፈረም ካልቻሉ በምትኩ የቶሪኖውን አንድሪያ ቤሎቲ አስበዋል፡፡ ኢንተሮች ኢካርዲን ለመሸጥ የወሰኑ ሲሆን እስከ 100 ሚ. ዩሮ ለአጥቂው ይፈልጋሉ፡፡ ይሁንና ናፖሊዎች ይህን የመክፈል እቅድ የላቸውም፡፡ ክፍያው የማይቀንስ ከሆነ ደግሞ በ60 ሚ. ዩሮ ቤሎቲን ለማዘዋወር አቅደዋል፡፡ (ካልሺዮ መርካቶ)
2019/06/09 10:59
📌አርሰናል በዚህ ባለፈው የውድድር አመት ጉዋንቱን የሰቀለውን የ 37 አመቱን ቼካዊ ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክን እዛው በክለቡ በሌላ የስራ ዘርፍ ላይ ለማሰማራት የማስፈረም ፍላጎታቸው አልተሳካላቸውም።እንደ ተለያዩ ሪፖርቶች ከሆነ ቼክ ወደ ቀድሞ ቸልሲ እንደሚመለስ ተዘግቡዋል።(Sunday Mirror)
2019/06/09 10:59
📌ሌጀንደሪው ጣልያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጆ ቡፎን ከፓሪሴንዤርመን ጋር ከተለያየ ቡኃላ ስሙ ከቻይና እና ከአሜሪካን በተጨማሪም ከባርሴሎና ጋር ተያይዞ ቢነሳም እግርኩዋስ ሀ ብሎ ወደ ጀመረበት ፓርማ ክለብ በድጋሚ ሊመለስ ነው።(La Gazzetta dello Sport, via Goal - in Italian)
2019/06/09 10:59
📌በአርሰናል የሚፈለገው የባርሴሎናው ተከላካይ ሳሙዔል ኡምቲቲ በዚህ የዝውውር መስኮት ክለቡን መልቀቅ እንደማይፈልግ አስታወቀ፡፡ አርሰናሎች በዚህ የውድድር አመት ክፉኛ የተፈተነውን የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር ተጫዋቾችን በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኡምቲቲ ደግሞ በአርሰናል የሚፈለግ ነበር፡፡ አሁን ግን ተጫዋቹ ክለቡን መልቀቅ እንደማይፈልግ አስታውቋል፡፡ Mirror
2019/06/09 10:59
ቅዳሜ የወጡ በርካታ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ሼር አድርጉት! ═════════════════════════ ✏️ DEAL DONE : ሪያል ማድሪዶች በመጨረሻም ኤዲን ሃዛርድን ከቼልሲ እስከ 2024 ድረስ በሚቆይ ኮንትራት ማዛወራቸውን ይፋ አደረጉ። የዝውውር ዋጋው ከ€100m [£88.5m] + ታይቶ የሚጨመር ሂሳብ ነው ብለዋል። (Source: Real Madrid C.F.) ═════════════════════════ ✏️ DEAL DONE: ማን.ዩናይትዶች በበኩላቸው የስዋንሴውን ዳንኤል ጀምስ ዝውውር በ£15m ቅድመ ክፍያ + £3m በቦነስ መልክ በመክፈል ማዛወራቸውን ይፋ አድርገዋል። (Source: Manchester United) ═════════════════════════ ✏️ ሪያል ማድሪዶች የሊዮኑን ፈረንሳዊ ግራ ተመላላሽ ተከላካይ ፈርላን ሜንዲን ዝውውር በ €55m ሂሳብ በቀጣዩ ሳምንት ያጠናቅቃሉ። (Source: ESPN) ═════════════════════════ ✏️ አንቶኒዮ ኮንቴ ማውሮ ኢካርዲ ምንም እንኳን በክለቡ ለመቆየት ፍላጎት ቢያሳድርም ክለቡ ኢንተር ሚላን አጥቂውን እንዲሸጥላቸው ተናግረዋል። (Source: Fabrizio Romano) ═════════════════════════ ✏️ ኢንተር ሚላኖች ኒኮሎ ቤሬላን በ €50m የዝውውር ሂሳብ ከካግሊያሪ ለማዛወር ከጫፍ ደርሰዋል። (Source: Calciomercato) ═════════════════════════ ✏️ የሌስተር ሲቲው አማካይ ጀምስ ማድሰን ምንም እንኳን በማን.ዩናይትድ እና በሌሎች ክለቦችም ለዝውውር ቢፈለግም በቀበሮዎቹ ቤት መቆየት እንሰሚፈልግ ታውቋል። (Source: Sun Sport) ═════════════════════════ ✏️ ፊሊፕ ኩቲንዎ አሁንም ከባርሴሎና መልቀቅ እንደሚፈልግ ለክለቡ አሳውቋል። ሆኖም።የካታላኑ ክለብ የትኛውም ፈላጊዎቹ ለዝውውሩ €90m ሂሳብ እንዲከፍሉ ነግረዋቸዋል። (Source: Cadena SER) ═════════════════════════ ✏️ ሪያል ማድሪዶች የ27 አመቱን የቶተንሃም ዴንማርካዊ ኢንተርናሽናል አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከ26 አመቱ የማን.ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ ይልቅ ቀዳሚ የዝውውር ኢላማቸው አድርገውታል። (Independent) ═════════════════════════ ✏️ የቼልሲው አለቃ ማውሪዚዮ ሳሪ በሶስት አመት ኮንትራት አዲሱ የጁቬንቱስ አለቃ በመሆን በቀጣይ ሳምንት ይሾማሉ። (Guardian) ═════════════════════════ ✏️ የቶተንሃሞች እንግሊዛዊ አማካይ የ25 አመቱ ኤሪክ ዳየር የማን.ዩናይትዶችን የተከላካይ አማካይ ቦታ ይሸፍናል ተብሎ በክለቡ እምነት የተጣለበት ኢላማቸው ሆኑአል። (Times - subscription required) ═════════════════════════ ✏️ ባርሴሎናዎች የ41 አመቱን ጣሊያናዊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ቡፎንን ከፓሪሰን ዥርሜይን መልቀቁን ይፋ ካደረገ በኃላ ወደ ካምፕ ኑ ያዛውሩታል የሚለውን ዘገባ አጣጥለውታል። (Mundo Deportivo - in Spanish) ═════════════════════════ ✏️ ባርሴሎናዎች በአንቶኔ ጋሬዝማን ወይም በኔይማር ዝውውር ላይ የማይሳካላቸው ከሆነ ፊታቸውን ወደ 21 አመቱ የማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ዝውውር ላይ ያተኩራሉ። (Mail) ═════════════════════════ ✏️ አትሌቲኮ ማድሪዶች የ28 አመቱን ስፔናዊ የቼልሲ ተከላካይ ማርከስ አሎንሶን ወደ ትውልድ ሃገሩ መመለስ ይፈልጋሉ። (Goal) ═════════════════════════ ✏️ የፉልሃሙ ከ21 አመት በታች የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጭዋች ሪያን ሲሲጎን ለክለቡ አዲስ ኮንትራት እንሰማይፈርም እና ወደ ቶተንሃም መዛወር እንደሚፈልግ ነግሯቸዋል። (Guardian) ═════════════════════════ ✏️ ሊቨርፑሎች የ24 አመቱን ፖርቹጋላዊ አማካይ ብሩኖ ፈርነንዴዝን ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ላይ ማን.ዩናይትድን እና ቶተንሃሞችን ለመፎካከር አቅደዋል። (Record, via Mirror) ═════════════════════════ ✏️ የሊሉ አይቬሪኮስታዊ የክንፍ መስመር ተጭዋች ኒኮላስ ፔፔ ከፕሪሚየር ሊጉ ይልቅ ወደ ቡንደስሊጋው ባየር ሙኒክ መዛወር ይመርጣል። የ24 አመቱ ተጭዋች የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር ኢላማ ነው። (Sun) ═════════════════════════ ✏️ አርሰናሎች ለ22 አመቱ ጥምሊያናዊ ተከላካይ ጆአኪም አንደርሰን እና ለ25 አመቱ ቤልጂየማዊ ክንፍ ዴኒስ ፕራዬት ዝውውር በድምሩ £44m እንዲያቀርቡላቸው ተነግሯቸዋል። (Star) ═════════════════════════ ✏️ ዌስትሃም ዩናይትድ እና አርሰንሎች የኢባሩን ስፔናዊ የ24 አመት አማካይ ጆአን ጆርዳንን ለማዛወር ፍላጎት አሳይተዋል። (Marca - in Spanish) ═════════════════════════ ✏️ ኤቨርተኖች የ27 አመቱን የሄታፌ ቶጎአዊ ተከላካይ ደጀን ዳኮናም ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ላይ ኤቨርተንን ተቀላቀሉ። (Marca - in Spanish) ═════════════════════════
2019/06/08 14:31
OFFICIAL: Real Madrid have signed Eden Hazard! 📝
2019/06/08 00:45
♨OFFICIAL 👉 ኔማር በደረሰበት ጉዳት ከኮፓ አሜሪካ ውድድር ውጪ መሆኑ ከተነገረ ቡሀላ የብራዚል እግር ኳስ ፌድሬሽን በኔማር ቦታ ተተኪውን ተጫዋች ማን ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር፡፡ እናም አብዛኛው የእግርኳስ ተመልካች በኔማር ቦታ የሪያል ማድሪዱ ወጣቱ ተጫዋች ቪኒሺየስ ጁኒየር ይጠራል ብሎ ቢጠብቅም ዛሬ ከሰአት የብራዚል እግር ኳስ ፌድሬሽን ግን በኔማር ቦታ የቸልሲውን የክንፍ ተጫዋች ዊልያንን ምርጫው አድርጎ እንደጠራው ይፋ አድርጓል ❗
2019/06/07 23:26
♨Breaking News 👉 ማን ዩናይትድ የስዋንሲውን የ21 አመቱን የክንፍ መስመር ተጫዋች የሆነውን ዳንኤል ጀምስን ከስዋንሲ በይፋ ማስፈረሙን አስታውቋል❗
2019/06/07 23:26
👉ኔይማር ሪያል ማድሪድን መቀላቀል እንደማይፈልግና ከማድሪድ ይልቅ ባርሳን መርጣለው።እንደሚታወቀው የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝደንት ፎለሬንቲኖ ፐረዝና የክለቡ ጉዳይ አስፈጻሚ ጆሴ አንገል ሳንቼዝ ኔይማርን ለማሳመን ሞክረው እንደነበርና እንዳልተሳካላቸው ተገልጿል። አሁን ኔይማር ወደ ባርሳ ሊመለስ ይችላል የተባለ ነው።
2019/06/07 23:26
​​ ​​እንኳን እንኳን ለ1440ኛው ዒድ አል—ፊጥር በዐል በሰላም አደረሳችሁ‼️ @Bleacher_Sport 🌙 •═•••🍃🌺🍃•••═• ​​🌙
2019/06/04 10:07
ጃኦ ካንሴሎን ለመተካት ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ወደ ማንችስተር ሲቲ የሚያቀና ከሆነ።(Source: Sky Italy) ═════════════════════════ ▶ማንችስተር ዩናይትድ ከእንግሊዛዊው አማካይ ጀምስ ማዲሰን ተወካዮች ጋር ተገናኝቱዋል።የተጫዋቹ እናት ክለብ ሌስተር ሲቲም ከተጫዋቹ ዝውውር እስከ £60m ገደማ ማግኘት ይፈልጋሉ።(Source: Daily Record) ═════════════════════════ ▶ሮሚዮ ሉካኮ ወደ አንቱኒዮ ኮንቴው ኢንተር ሚላን መዘዋወር ይፈልጋል።የሉካኮ ወኪል ፌድሪኮ ፓስቶሬሎ በግል ጉዳዮች ላይ ከኢንተር ጋር ከስምምነት ደርሱዋል አሁን የቀረው የጣልያኑ ክለብ ከማንችስተር ዩናይትድ ተገናኝቶ ዋጋ መጠየቅ ነው።(Source: SportMediaset) ═════════════════════════ ▶ሊዮናል ሜሲ በዚህ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አንቱዋን ግሬዝማን ወደ ባርሴሎና እንዲዘዋወር አይፈልግም ከዛ ይልቅ ኔይማር በድጋሚ ወደ ካምፕኑ እንዲመጣ ይፈልጋል።ባርሴሎናም ባለፈው ሳምንት ለመነሻ ያህል ከፒኤስጂ ጋር ንግግር ቢያደርግም ውድቅ ተደርጎበታል።(Source: RMC Sport) ═════════════════════════ ▶ፓውሎ ማልዲኒ የቲክኒካል ዳይሬክተርነት ቦታን በመያዝ ወደ ኤስሚላን ለመመለስ ከስምምነት ደርሱዋል።የሳምፒዶሪያው አሰልጣኝ ማርኮ ጂያንፓሮም ጂናሮ ጋትሶን በመተካት አዲሱ የኤስሚላን አሰልጣኝ ሆነው እንደሚሾሙም ተዘግቡዋል።(Source: Gazetta dello Sport) ═════════════════════════ ▶ሬያል ማድሪድ ሶስት ጋሬዝ ቤልን፣ኢስኮን እና ጀምስ ሮድሪጌዝን በመስጠት በልዋጩ ደግሞ ፖል ፖግባን ከማንችስተር ዩናይትድ ለመውሰድ እያጤኑበት ነው። (Source: Times) ═════════════════════════ ፧
2019/06/04 10:06
ማክሰኞ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት። ═════════════════════════ ▶️ቸልሲ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ከስታምፎርድብሪጅ በመልቀቅ ወደ ጁቬንቱስ የሚያቀኑ ከሆነ የዋትፎርዱን ዋና አሰልጣኝ ሀቪ ጋርሺያን ለመቅጠር እያጤኑበት ይገኛል።(ESPN) ═════════════════════════ ▶️ጁቬንቱስ ለሳሪ የሶስት አመት ኮንትራት እና በአመትም £6.22m ለመክፈል እያሰቡ ይገኛሉ።(Corriere della Sera - in Italian) ═════════════════════════ ▶️በተያያዘ ዜና የ 28 አመቱቤልጄማዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኤደን ሀዛርድም ከቸልሲ ወደ ማድሪድ የሚያደርገውን ዝውውር ዛሬ መጨረስ ይፈልጋል ነገር ግን የሳሪ ከቸልሲ የመልቀቅ ጉዳይ ዝውውር በግዜ እንዳያልቅ መሰናክል ሊሆንም እንደሚችል ተዘግቡዋል።(Evening Standard) ═════════════════════════ ▶️ሬያል ማድሪድ ለመጨረሻ ግዜ እና የመጨረሻ ያለውን €120m ለቸልሲዎች የመክፈል ፍለጎት አለው ኤደን ሀዛርድን ወደ ሳንቲያጎ በርናበው ለመውሰድ።ሎስብላንኮዎቹም ተወካዮቻቸውን ወደ ለንደን ልከዋል ከቸልሲዋ ዳይሬክተር ማርያናግራኖቪስኪ ጋር እንዲገናኙ።(Goal) ═════════════════════════ ▶️ጁቬንቱስ ከ 2012-2016 ለ 4 አመት በክለባቸው ውስጥ የቆየውን የ 26 አመቱን ፈረንሳያዊ አማካይ ፖል ፖግባን ከማንችስተር ዩናይትድ በድጋሚ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።(Sky Italy) ═════════════════════════ ▶️ናስር አልካላፊ የኳታር ኢቨርትመንት ግሩፕ እና የፓሪሴንዤርመን ባለቤት በዶሀ ከሊድስ ዩናይትድ ተወካዮች ጋር እንደተነጋገሩ እየተነገረ ይገኛል በማርሴሎ ቤልሳ የሚሰለጥነውን የሻምፕዮን ሺፑን ክለብ ለመግዛት።(L'Equipe - in French) ═════════════════════════ ▶️በተመሳሳይ የፓሪሴንዤርመኑ ሀላፊ ናስር አልካላፊ የ 27 አመቱ ብራዚላዊ ኔይማር በዚህ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከፓርክ ደፕሪንስ እንዲለቅ አይፈልጉም።(Marca) ═════════════════════════ ▶️ማንችስተር ዩናይትድ የ 22 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ጀምስ ማዲሰን በዚህ ክረምት ከሌስተር ሲቲ ማስፈረም ይፈልጋሉ።(Independent) ═════════════════════════ ▶️የሌስተር ሲቲው የግራ መስመር ተከላካይ ቢን ቻል ዌል የማንችስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ አስደናቂ የሚባል ሲዝን እንዳሳለፍኩ ነግሮኛል ሲል ተናግሯል።(Mirror) ═════════════════════════ ▶️የቻይናዎቹ ክለብ Guangzhou Evergrande and Shanghai SIPG የአርሰናሉን ጋቦናዊ አጥቂ ፔርኤሜሪክ ኦበሚያንግን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው በሳምንትም እስከ £300,000 የሚጠጋ ሳምንታዊ ደሞዝ የማቅረብ ፍላጎት አላቸው።(Times - subscription required) ═════════════════════════ ▶️ማንችስተር ዩናይትድ እስከ £31m በማውጣት የሊግ 1 ምርጥ ግብ ጠባቂ የሆነውን የሊሉን ፈረንሳያዊ ግብ ጠባቂ ማይክ ማግናን ለማስፈረም እየተመለከቱ ይገኛሉ ዴቪድዴህያን እውን እንደሚያጡት የሚያረጋግጡ ከሆነ።(Daily Record) ═════════════════════════ ▶️ዌስትሀም £20m ለባርሴሎና አቅርበዋል የ 25 አመቱን ፖርቹጋላዊ አማካይ አንደሬ ጎሜዝን ለማስፈረም አማካዩ ያለፈውን ሲዝን በውሰት በኤቨርተን ነበር ያሳለፈው።በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደሞ ዌስትሀሞች ለተጫዋቹ ዝውውር £18m አቅርበው በብሉግራናዎቹ ውድቅ ተደርጎባቸው ነበር።(Guardian) ═════════════════════════ ▶️የባየርሙኒኩ ፕሬዝዳንት ኦሊ ሆነሽ ማንችስተር ሲቲ ለ 23 አመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሊሮይ ሳኔ የጠየቀው ዋጋ እብደት ነው ሲሉ ገልፀውታል።(Star) ═════════════════════════ ▶️እንደ ቀድሞ የሊቨርፑል ተጫዋች ጆን ባርነስ እምነት ሆላንዳዊው የቀያዮቹ የመሀል ተከላካይ ቨርጅል ቫንዳዬክ የዚህን አመት ባላንዶርን ማሸነፍ እንደሚገባው ተናግሯል።(Talksport) ═════════════════════════ ▶️ጁቬንቱስ ወደ አያክሱ የመሀል ተከላካይ ማቲያስ ዴሊት ዝውውር እራሱን አስገብቷል ለዝውውሩም £75m ማቅረቡ እየተሰማ ይገኛል።(mirror) ═════════════════════════ ▶ማንችስተር ሲቲ የክሪስታል ፓላሱን የመስመር ተከላካይ አሮን ዋን ቢሳካን ለማስፈረም እንደሚሸጥ ለመጠየቅ ተዘጋጅተዋል በቶተንሀሙ ተከላካይ ኬረን ትሪፐር ላይ ያለውን ፍላጎት ካቀዛቀዘ ቡኃላ።(mirror) ═════════════════════════ ▶ፓሪሴንዤርመን ኢንተር ሚላን በመቀላቀል የሮሚዮ ሉካኮ ፈላጊ በመሆን ብቅ ብለዋል።(mirror) ═════════════════════════ ▶አርሰናል ለሳፒዶሪያዎቹ ዳኒስ ፓራቲ እና ጆዋኪም አንደርሰን £37m ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል በዚህ ክረምት ወደ ፍላይኤሜሬት ለማስኮብለል።(star) ═════════════════════════ ▶ማውሪዚዮ ሳሪ ማንችስተር ዩናይትድን በመርታት ካሊዶ ኩሊባሊን ከናፖሊ ሊያስፈርሙ ይችላሉ የጁቬንቱስ አሰልጣኝ ሆነው የሚሾሙ ከሆነ።(star) ═════════════════════════ ▶ማንችስተር ዩናይትድ፣ሬያልማድሪድ እና ባየርሙኒክ እስከ £180m በማውጣት መሀመድ ሳላህን ከሊቨርፑል ለማስፈረም በዚህ ክረምት ሊፎካከሩ ተዘጋጅቱዋል።(daily mail) ═════════════════════════ ▶ሲቪያ የግዜያዊ አሰልጣኛቸውን ጁዋኪም ካፓራሶን በቀድሞ የሬያል ማድሪድ አሰልጣኝ ጁልያን ሉፕቲጌ ለመተካት ተቃርበዋል።(daily mail) ═════════════════════════ ▶ሲውዘርላንዳዊው አማካይ ዠርዳን ሻኪሪ በሊቨርፑል በመቆየት ለቦታው መፍለም ይፈልጋል እንጂ ከክለቡ መልቀቅ አይፈልግም።(Source: Daily Express) ═════════════════════════ ▶ኤቨርተን ቱሪካዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ቼንጊዝ ኦንደርን ለማስፈረም £24m ቢያቀርቡም በሮማ ውድቅ ተደርጎባቸዋል።(Source: Daily Star) ═════════════════════════ ▶ሚሱት ኦዚል ከአርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት የሚስማማቸው አይነት ጥያቄ ከመጣ ሊሸጡት እንደሚችሉ ነግረውታል።ከኡናይ ኤምሬ ጋርም ያለው መልካም ያልሆነ ግንኙነት እና ከኢሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጫወታ ቡኃላም አሰልጣኙን መስደቡም አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተዘግቡዋል።(Source: Fanatik) ═════════════════════════ ▶የፊዮረንቲናው አማካይ ጆርዳን ቬሬንታውት ወደ ናፖሊ ለመዘዋወር ተቃርቡዋል።የ 26 አመቱ አማካይ የ 5 አመት ኮንትራት ለመፈረምም ተስማምቱዋል የዝውውር ገንዘብም £27m እንደሆነም ተዘግቡዋል።(Source: Calcio Mercato) ═════════════════════════ ▶ቶተንሀም ለፈረንሳያዊው አማካይ ታንጉይ ኒዶንቤሌ ያቀረቡት የዝውውር ሂሳብ በሊዮን ውድቅ ተደርጎባቸዋል የፈረንሳዩ ክለብም €80m ይዞ ከሚመጣ ክለብ እንጂ ከሌላ ክለብ ጋር የመደራደር ምንም አይነት ፍላጎት የለውም።(Source: Le10 Sport) ═════════════════════════ ▶ጁቬንቱስ የቶተንሀሙን ተከላካይ ኬረን ትሪፐርን ማስፈረም ይፈልጋሉ
2019/06/04 10:04
🏆ሊቨርፑል የ2018/19 ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችለዋል።
2019/06/02 04:28
🏆ዛሬ ምሽት በ2018/19 የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ። 👉FULL - TIME⌚️ ⚪️ቶትንሀም 0⃣ - 2⃣ ሊቨርፑል🔴 #ሳላህ '2⚽️ P #ኦሪጊ '87⚽️
2019/06/02 04:28
🏆ዛሬ ምሽት በ2018/19 የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ። ⚪️ቶትንሀም 🆚 ሊቨርፑል🔴 👉ምሽት 4 : 00 PM⌚️ ⛳️ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲዬም⛳️ ✳️ይህን ተጠባቂ ጨዋታ ከወዲሁ በቻናላችን ሽፋን እንደምንሰጥ ልናሳስብ እንወዳለን እስከዛም ጨዋታዉን ይገምቱ!! @Umella_bot
2019/06/01 19:27
ሰባ ተደርጎ እንደምንወያየው እኛም ተገናኝተን እንወያያለን። ቸልሲ ከኔ ምን እንደሚፈልግ ሃሳቡን ያቀርባል። እኔም ደግሞ በቸልሲ በኩል ምን እንዲያስተካክሉልኝ እንደምፈልግ ሃሳቤን አቀርባለሁ። ነገሮች ሁሉ በውይይት ይፈታሉ። ሌላው እና ትልቁ ነገር ከቸልሲ ጋር ሚያቆይ ተጨማሪ የ2 አመት ውል አለኝ" - ብሏል። ሳሪ ቸልሲን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ከሆነ ጁቬንቱስ የውል ማፍረሻውን 6.3 ሚሊዬን ፓውንድ ለመክፈል አሁንም ቁርጠኛ መሆኑንም እየተዘገበ ነው። (dailymail) ═════════════════════════ 📰 — የኢሮፓ ሊግ ምርጡ ስኳድ ዛሬ ይፋ ሲሆን ከቸልሲ አሪዛባላጋ፤ ሉይዝ፣ አዝፒሊኩዬታ፣ ጆርጂኒዮ፣ ካንቴ፣ ፔድሮ፣ ሃዛርድ እና ጂሩ መካተት ሲችሉ ይካተታሉ ተብለው ተጠብቀው የነበሩት ኦዶይ እና ሩቤን በጉዳት ጭዋታ ስላለፋቸው ሳይመረጡ ቀርተዋል። የአርሰናሉ ኦበምያንግ፤ የፍራንክፈርቶቹ ኮስቲች፣ ዳ ኮስታ እና ሃሰቤ እንዲሁም ጆቪች ይገኙበታል። (dailymail) ═════════════════════════
2019/05/31 10:07
አርብ የወጡ በርካታ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር አድርጉት! ═════════════════════════ 📰 — PSG, ቼልሲ እና ማን.ዩናይትዶች ፊሊፕ ኩቲንዎን ስለሚያዛውሩበት ሁኔታ ከስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ጋርግንኙነት ማድረግ ጀምረዋል። ተጭዋቹ ከሦስት ወራት በፊት የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቱ ይታወሳል። (Source: Mundo Deportivo) ═════════════════════════ 📰 — የሪያል ማድሪዱ የ33 አመት ስፔናዊ ተከላካይ ሰርጂዎ ራሞስ እንዳለው ከሆነ ኤዲን ሃዛርድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ሪያል የሚዛወር ከሆነ ለቡድናቸው መንፈስ ትልቅ በራስ መተማመንን ይፈጥራል። (Star) ═════════════════════════ 📰 — የ27 አመቱ ብራዚላዊ የፒ.ኤስ.ጂ አጥቂ ኔይማር ወደ ባርሴሎና መዛወር ይፈልጋል። (Sport - in Spanish) ═════════════════════════ 📰 — ማንቸስተር ዩናይትዶች የ24 አመቱን ፈረንሳዊ የፒ.ኤስ.ጂ አማካይ አድሪየን ራቢዮት የማዛወር የተሻለ እድል አላቸው። ተጭዋቹ ከፊታችን ጁላይ 1 ቀን ጀምሮ ከፓሪሱ ክለብ ኮንትራቱ ነፃ ስለሚሆን ወደ ፈለገው ክለብ ማምራት ይችላል። (Mundo Deportivo - in Spanish) ═════════════════════════ 📰 — ማንቸስተር ዩናይትዶች የ26 አመቱን ቤልጂየማው ግዙፍ አጥቂ ሮሚዮ ሉካኩን ኢንተር ሚላንን እንዲቀላቀል ይፈቅዱለታል። ይሄ የሚሆነው ግን ለተጭዋቹ ዝውውር የ £80m ሂሳብ የሚቀርብላቸው ከሆነ ብቻ ነው። (Times - subscription required) ═════════════════════════ 📰 — ማንቸስተር ሲቲዎች ባየር ሙኒኮች ለ23 አመቱ ፈርመናዊ የክንፍ ተጭዋች ሎሪ ሳኔ ዝውውር ያቀርቡላቸውን የ £70m ሂሳብ ውድቅ አድርገውባቸዋል። (Guardian) ═════════════════════════ 📰 — ማን ሲቲዎች ለ25 አመቱ ፖርቹጋላዊ የጁቬንቱስ ተከላካይ ጆአዎ ካንሴሎ ዝውውር የ £53m ሂሳብ አቅርበዋል። (Tuttosport - in Italian) ═════════════════════════ 📰 — ጁቬንቱሶች ለቼልሲው አለቃ ማውሪሲዮ ሳሪ አመታዊ የ£6.2m ደሞዝ ኮንትራት አቅርበውላቸዋል። (Mirror) ═════════════════════════ 📰 — የቀድሞው የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን አማካይ አንድሪያ ፒርሎ እንዳለው ከሆነ በ2011 ላይ ወደ ማን.ሲቲ ለመዛወር ጥያቄ ቢቀርብለትም ሳይቀበለው ቀርቷል። እንዲሁም በ2009 ላይ ደግሞ ቼልሲዎች እድሜው ገፍቷል በሚል የማዛወር እቅዳቸውን እንደተውበት ተናግሯል። (Mail) ═════════════════════════ 📰 — አርሰናሎች አሁንም የ25 አመቱን የበርንማውዝ የክንፍ ተጭዋች ሪያን ፍሬዘር ማዛወር ይፈልጋሉ። ሆኖም የክሪስታል ፓላሱን የ26 አመት አይቬሪኮስታዊ ክንፍ ዊልፍሪድ ዘሃን የማዛወር እቅዳቸው ደብዝዟል። ምክንያቱ ደግሞ በሻምፒየንስ ሊጉ መሳተፍ ስለማይችሉ ነው። (Mirror) ═════════════════════════ 📰 — የ30 አመቱ ጀርመናዊ የአርሰናል አማካይ ሜሱት ኦዚል፤ የ27 አመቱ ተከላካይ ሽኮድራን ሙስታፊ እና የ30 አመቱ አርሜኒያዊው አማካይ ሄነሪክ ሚኪተሪያን ቡድኑ ለመልሶ ግንባታና ለዝውውር የሚሆን በቂ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ሊሸጣቸው የሚችላቸው ሦስቱ ቀዳሚ ተጭዋቾች ናቸው። (Star) ═════════════════════════ 📰 — የሊቨርፑሉ ሊቀመንበር ቶም ወርነር እንዳሉት ከሆነ አሰልጣኙ የርገን ክሎፕ ከኦክቶበር ወር ጀምሮ ቡድኑን የያዘው ጀርመናዊ አሰልጣኝ በቀያይቹ ቤት እስከፈለገው አመት ድረስ መቆየት ቢችል ደስተኞች ናቸው። (Liverpool Echo) ═════════════════════════ 📰 — የ28 አመቱ የማንቸስተር ሲቲ ፈረንሳዊ ተከላካይ ኢሊኩየም ማንጋላ ክለቡን በ£32m የዝውውር ሂሳብ ከአምስት አመታት በፊት ለቆ ወደ ሲቲ ከመጣ በኃላ በድጋሚ ወደ ፖርቹጋል ሊመለስ ነው። (O Jogo - in Portuguese) ═════════════════════════ 📰 — የሪያል ማድሪዱ ኮሎምቢያዊ የ27 አመት አጥቂ ሃምስ ሮድሪጌዝ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመዛወር ፍላጎት የለውም። ሃሳቡ የተጭዋቹ ፈላጊዎቹን የጣሊያኖቹ ጁቬንቱስ እና ናፖሊን ያነቃቃ ሆኑአል። (Marca) ═════════════════════════ 📰 — ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተመለሱት አስቶን ቪላዎች የ29 አመቱን የበርንማውዝ አማካይ ሃሪ አርተርን ማዛወር ይፈልጋሉ። ሆኖም ለአየርላንዱ ሪፐብሊክ ተጫች ዝውውር ከፉልሃም እና ከስቶክ ሲቲዎች ፉክክር ይጠብቃቸዋል። (Irish Independent) ═════════════════════════ 📰 — አስቶን ቪላዎች የ26 አመቱን እንግሊዛዊ ተከላካይ ታይሮን ሚንግስንም ከበርንማውዝ በቋሚ ዝውውር ማስፈረም ይፈልጋሉ። (Sky Sports) ═════════════════════════ 📰 — የሲቪያው የአማካይ አጥቂ ፓብሎ ሳራቢያ ወደ ሪያል ማድሪድ መዛወር ይፈልጋል። ተጭዋቹ የ£17m ሂሳብ ኮንትራቱ ላይ ውል ማፍረሻ አለው። (Source: Muchodeporte) ═════════════════════════ 📰 — ኢንተር ሚላኖች ከኤዲን ዤኮ ጋር በግል ጉሳዮች ከስምምንነት ደርሰዋል ሆኖም ከሮማ ጋር መስማማት አልቻሉም። ሮማዎች ለ33 አመት አጥቂ የ£17m ሂሳብ እንሲከፍሏቸው ጠይቀዋል። (Source: Corriere dello Sport) ═════════════════════════ 📰 — ባርሴሎናዎች ሮድሪጎን የማዛወር ፍላጎት አላቸው። የ28 አመቱ ተጭዋች ኮንትራቱ ላይ £88m ውል ማፍረሻ ያለው ቢሆንም ከዛ ባነሰ የዝውውር ሂሳ እንደሚያዛውሩት ተስፋ አድርገዋል። (Source: MARCA) ═════════════════════════ 📰 — 📝 DEAL DONE: ኖርዊች ሲቲዎች የማንቸተር ሲቲውን ፓትሪክ ሮበርትስ ለአንድ ሲዝን በውሰት ውል ማዛወራቸውን ይፋ አደረጉ። (Source: Norwich City F.C.) ═════════════════════════ 📰 — ሰርጂዎ ራሞስ ምንም እንኳን ስሙ ከቻይና ሱፐር ሊግ ክለቦች ዝውውር ጋር ተያይዞ ቢነሳም በሪያል ማድሪድ እንሰሚቆይ ማረጋገጫ ሰጥቷል። (Source: Real Madrid C.F.) ═════════════════════════ 📰 — ማንቸስተር ዩናይትዶች በቤነፊካው ባለተሰጥዎ የክንፍ መስመር ተጭዋች ጆአዎ ፍሊክስ ዝውውር ላይ ከጎረቤታቸው ማን.ሲቲ ጋር እኩል ለመፎካከር ወስነዋል። ለተጭዋቹ ዝውውር እስከ £105m ድረስ ለመክፈልም ፍቃደኞች ናቸው። (Source: MEN) ═════════════════════════ 📰 — አንቶኔ ጋሬዝማን የቤርሴሎና ቀዳሚው የዝውውር ኢላማ አይደለም። የክለቡ ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ማርያ ባርቶሜው በዝውውሩ ውስብስባዊ ባኮንትራቶች ባህርይ የተነሳ ከዝውውሩ ድርድር ራሳቸውን ለግዜው አግልለዋል። (Source: MARCA) ═════════════════════════ 📰 — ማውሪዚዮ ሳሪ ወደ ጁቬንቱስ ይሄዳል ተብሎ ስለሚናፈሰው ወሬ እንዲህ ብሏል.. "አሁን ልክ እንደማንኛውም ክለብ የአመቱ መጨረሻ ላይ ስብ
2019/05/31 10:07
ማን.ዩናይትድ ሰዎች ከአያክስ ሰዎች ጋር በማቲያስ ዲ ላይት ዝውውር ዙሪያ ንግግር ማድረግ ጀምረዋል። የቀያይ ሰይጣኖቹ ባለስልጣናት አያክሶች የ19 አመቱን ተከላካይ 'በየትኛውንም የዝውውር ዋጋ' ቢሸጡት እንደሚወስዱላቸው አሳውቀዋቸዋል። [tv3] ═════════════════════════ 📰 — ከሳምንታት በፊት የባርሴሎና ሰዎች በማቲያስ ዲ ላይት ዝውውር ዙሪያ ወደ ካምፕ ኑ እንደሚያመጡት እርግጠኞች ነበሩ። አሁን ያ የቀድሞው መተማመናቸው የለም። አሁን ባሉት ሁኔታዎች ማን.ዩናይትድ የተከላካዩ ማረፊያ ይመስላል። [sid lowe, guardian] ═════════════════════════ 📰 — ፔፕ ጋርዲዮላ የአትሌቲኮ ማድሪዱ አማካይ ሮድሪጎ ወደ ማን.ሲቲ እንዲመጣ በግል ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው። አትሌቲኮዎች ተጭዋቹን ለማቆየት አዲስ የተሻሻለ ኮንትራት ውል አቅርበውለታል። ማን.ሲቲዎች በበኩላቸው የተጭዋቹን ውል ማፍረሻ ለመክፈል ፍቃደኖች ሆነዋል። በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ይሄ ሳምንት ወሳኝ ነው። [Mundo Deportivo] ═════════════════════════ 📰 — ማርሴሎ ቤይልሳ የማን.ሲቲው የክንፍ መስመር ተጭዋች ጃክ ሃሪሰን በሊድስ ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ አመት የውሰት ውል ኮንትራት እንዲቆይላቸው ፍላጎታቸውን ገልፀዋል። [YEP] ═════════════════════════ 📰 — የሊቨርፑሉ ዊልሰን በበርካታ የፕሪሚየር ሊጉ፣ የቡንደስሊጋው እና የላ ሊጋው ክለቦች ለዝውውር ይፈለጋል። በዚህ ፉክክር ቀያዮቹ ተጭዋቹን ለመልቀቅ የ£25 million የዝውውር ሂሳብ እንዲቀርብላቸው ይጠይቃሉ። (Anfieldhq) ═════════════════════════ 📰 — ባየር ሙኒኮች ሎሪ ሳኔን ለማዛወር ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ይገኛል። የባባሪያኑ ክለብ ለክንፍ ተጭዋቹ በጋርዲዮላ የተነፈገውን በሙኒኩ አለቃ ኒኮ ኮቫች የተሻለ የጨዋታ ሚና እንደሚሰጠው በመግለፅ ከኢትሃድ ሊያስኮበልሉት ይሞክራሉ። [Sport Bild] ═════════════════════════ 📰 — በሙኒክ ቤት ሳኔን እንሰሚያዛውሩት አዎንታዊ ተስፋ አለ። እንደነ ኮማን እና ግናብሪን የመሳሰሉ የቡድኑ ተጭዋቾች ሳይቀር ሳኔ ቢዛወር ለቦታው እንደሚፎካከራቸው ቢያውቁም ቡድኑ ኳሊቲ የክንፍ ተጭዋች እንደሚያስፈልገው ስለተረዱ ቢመጣ ደስተኞች ናቸው። [SportBild] ═════════════════════════ 📰 — አትሌቲኮ ማድሪዶች የኢስፓኞሉን ተከላካይ ሄርሞሶን ለማዛወር የድርድሩ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል። ሪያል ማድሪዶች ከፈለጉ የቀድሞ ተጭዋቻቸውን በ €7M ብቻ መልሶ የማዛወር መብት አላቸው። [Cope] ═════════════════════════ 📰 — የ ቼልሲዉ አሰልጣኝ ማዉሪዚዎ-ሳሪ ከ ቼልሲ የልምምድ ሜዳ ከዩሮፓ ሊጉ ድል በፊት ባለው ልምምድ ተናደዉ መዉጣታቸዉ ተነግሯል :: ይህም የሆነዉ በ David-Luiz እና Heguain በመጋጨታቸዉ ደስተኛ ባለመሆናቸው ነበር ተብሏል:: ሉዊዝ ሂጉዌይንን ልምምድ ላይ ሆን ብሎ በክርኑ መቶት እንደነበር ተነግሯል። [The Sun] ═════════════════════════ 📰 — 🏆የኢሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ወሳኝ የፍፃሜ ጨዋታ። 👉 ጨዋታው ተጠናቀቀ 🔴አርሰናል 1⃣➖4⃣ ቼልሲ🔵 #ጅሩድ 49' ⚽️ #ፔድሮ 60' ⚽️ #ሀዛርድ 65',72' ⚽️ #ኢዮቢ 69' ⚽️ ═════════════════════════ 📰 — "I think it's goodbye"....የሃዛርድ ስንብት ... "የስንብቴ የመጨረሻ ቀን ይመስለኛል፥ በእርግጥ በእግር ኳስ የሚሆነው ባይታወቅም ... በፕሪሚዬር ሊግ የመጫወት ህልም ነበረኝ፥ ላለፉት 7 ዓመታት በአውሮፓ ታላቅ ከሆነው ቼልሲ ጋር ይህን አሳክቻለሁ፥ አሁን ሌላ አዲስ ፈተናን በሌላ ሊግ ለመሞከር ተዘጋጅቻለሁ ..." ሲል የአውሮፓ ሊግን ዋንጫ ባነሱበት ምሽት ይህንኑ ተናግሯል። ═════════════════════════ 📰 — ኤዲን ሃዛርድ በቼልሲ.. ከ2012/13 -2018/19 352 - ጨዋታ 110 - ጎል 92 - የጎል ኳስ 2 - ፕርሚየር ሊግ 2 - ዩሮፓ ሊግ 1 ኤፍኤ ካፕ 1 ሊግ ካፕ ═════════════════════════ 📰 — ገና የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ ቢሆኑትም ማን.ዩናይትዶች በአውሮፓ በሚነበቡ ታላላቅ ጋዜጦች ላይ ከ22 ተጭዋቾች ዝውውር ጋር ስማቸው ተያይዞ ወጥቷል። እነርሱም.. • Sancho • Rabiot • Félix • Dybala • Wan-Bissaka • Partey • James • Griezmann • Longstaff • Rakitić • De Ligt • Van Aanholt • Icardi • Maguire • Onana • Koulibaly • Perišić • Fernandes • Bale • Collins • Varane እና • Pepe ናቸው። (Source: Various) ═════════════════════════ 📰 — በአለም ላይ ያሉ አስሩ ውድ ዋጋ ያላቸው ክለቦች - TOP 10 WORLD'S MOST VALUABLE CLUBS: 1) Real Madrid: £2.9b 2) Man United: £2.83b 3) Bayern Munich: £2.43b 4) Barcelona: £2.41b 5) Manchester City: £2.2b 6) Chelsea: £2b 7) Liverpool: £1.9b 8) Arsenal: £1.8b 9) Tottenham: £1.5b 10) Juventus: £1.3b [KPMG] ═════════════════════════ 📰 — Pep Stats: ፔፕ ጋርዲዮላ ባሰልጣኝነት ባሳለፈባቸው በላ ሊጋው፣ በቡንደስሊጋው እና በፕሪሚየር ሊጉ ለረዥም ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ያለመሸነፍ ሪከርድ ባለቤት ነው። 🇩🇪 በባየር ሙኒክ: 19 (የአውሮፓ አጠቃላይ ሪከርድ ነው) 🇬🇧 በማንቸስተር ሲቲ: 18 🇪🇸 በባርሴሎና: 16 ═════════════════════════ 📰 — በእንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ ታሪክ ከ 1888/89 እስከ 2018/19 ማለትም ለ120 አመታት የሃገሪቱ ከፍተኛው ሊግ ላይ በብዛት የተወዳደሩ ስድስት ቡድኖች.. 1. Everton: 116 2. Aston Villa: 105 3. Liverpool: 104 4. Arsenal: 102 5. Man United: 94 6. Manchester City: 90 ═════════════════════════
2019/05/30 20:37
👉Eden Hazard በቼልሲ ከ2012-2018/19📊 🏟352 ------- ጨዋታ ⚽️110 -------- ጎሎች 🎯92 --------- የጎል ኳስ 2 --------- ፕሪምየር ሊግ 🏆🏆 2 --------- የዩሮፓ ሊግ 🏆🏆 🏆ኤፌ ኤካፕ እና ሊግ ካፕ 🏆 ማንሳት ችሏል።
2019/05/30 20:36
👉በ21ኛው ክ/ዘመን በአውሮፓ መድረክ ሳይሸነፍ ዋንጫ ያነ ሱ ክለቦች። 2005/06 -------- ባርሴሎና በቻምፕዮንስ ሊግ🏆🏆 2007/08 -------- ማንችስተር ዩናይትድ በቻምፕዮንስ ሊግ 🏆🏆 2018/29 --------- ቼልሲ በኢሮፓ ሊግ 🏆
2019/05/30 20:33
⚽️ በአውሮፓ ሊግ ፍፃሜ ትናንት ምሽት አርሰናል ላይ ሁለት ግብ እና እንድ ኳ ስ ለግብ አመቻችቶ በማቃበል የጨዋታው ኮከብ ሆኖ የተመረጠው በልጄሜያዊው የቼልሲ ኮከብ #EDEN HAZARD ከጨዋታው በኋላ ስለ ጨዋታውና ስለ ወደፊት ቆይታው የሰጠው አስተያየት። ………………………………………………………………… 👉 Eden Hazard ስለጨዋታው ስናገር ''ጨዋታው ጥሩ ነበር።በመጀመሪያው ግማሽ ፍፃሜ እንደመሆኑ በሁለቱም ቡድኖች መሀል ውጥረት ነግሶ ነበር።ነገር ግን ጅሩድ ሲያስቆጥር የድሉ ምሽት መነሻ ሆነ።በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ ተጫውተናል፤ጥቂት የግብ እድሎችንም ፈጥረናል፤ጨዋታውንም ተቆጣጥረን በመጨረሻም 4-1 አሸነፈን።ይህንን ዋንጫ ከቡድኑ ጋር በማንሳቴ ደስተኛ ነ ኝ ብሏል። ………………………………………………………………… #ሀዛርድ ስለወደፊት ቆይታው ሲጠየቅ ''አሁን ይህንን አላውቅም።ከጥቂት በኋላ እወስናለው ዛሬ አላማዬ ዋንጫ ማንሳት ነበር እሱን አ ሳክቼአለው፤አሁን በአይምሮዬ ያለው ይሄ ብቻ ነው።'' ''በእኔ እምነት ይሄ መሰናብቻዬ ነው።ነገር ግን በእግር ኳስ የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም።በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ህልሜ ነበር ይህንን ህልም ከአለም ትልቁ ክለብ በሆነው በአንዱ ላለፉት ሰባት አመት አድርጊያለው።አሁን ደሞ በሌላ በአዲስ ፉክክር የማድረግ ጊዜው ነው።''
2019/05/30 20:33
851 ጨዋታዎች 14 ዋና ዋና ዋንጫዎች #ፒተር #ቼክ በምሽቱ ጨዋታ በሽንፈት ታጅቦ ጓንቱን ሰቅሏል፡፡
2019/05/30 20:31
—World Cup —European Championship —Champions League —Europa League —UEFA Super Cup —Club World Cup Pedro is the only player ever to have won all these trophies 😍
2019/05/30 07:15
Whoever the manager, Chelsea keep on winning trophies 🏆
2019/05/30 07:15
Chelsea's win means Lyon skip the qualifiers and go straight into next season’s Champions League group stage 🤝
2019/05/30 07:15
🔴አርሰናል 0⃣ - 1⃣ ቼልሲ🔵 #ጅሩድ '49⚽️
2019/05/30 07:06
🔴አርሰናል 0⃣ - 2⃣ ቼልሲ🔵 #ፔድሮ '59⚽️
2019/05/30 07:06
🔴አርሰናል 0⃣ - 3⃣ ቼልሲ🔵 #ሀዛርድ '65⚽️P
2019/05/30 07:06
🔴አርሰናል 1⃣ - 3⃣ ቼልሲ🔵 #ኢዎቢ '69⚽️
2019/05/30 07:06
🏆ዛሬ ምሽት በ2018/19 የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ። 👉FULL - TIME⌚️ 🔴አርሰናል 1⃣ - 4⃣ ቼልሲ🔵 #ኢዎቢ '69⚽️ #ጅሩድ '49⚽️ #ፔድሮ '59⚽️ #ሀዛርድ '65⚽️P '72
2019/05/30 07:06
⚠️ ሰበር ዜና ⚠️ 👉Eden Hazard ከቼልሲ እንደሚለቅ ከBt-Sport ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ አረጋግጧል።ቼልሲን ለመልቀቅ የወሰንኩት አዲስ ፈተና መሞከር ስለምፈልግ እንጂ በሌላ ምክንያት አደለም ቼል ሲን በጣም እወደዋለው ለዘላለም በልቤ ይኖራል ብሏል።
2019/05/30 07:06
📌ቢን ስፓርት ቅዳሜ የሚደረገውን የ ቻምፒዬንስ ሊግ ፋፃሜ ጨወታ በ ተንታኝነት አርሰን ዌንገር እና ጆዜ ሞሪንሆ ስቱዲዬ እንደሚኖሩ አስታውቁዋል፡፡
2019/05/28 11:36
🦋አዘርባጃ ባኩ እስታዲዬሟን ለተጠባቂው ኢሮፓ ሊግ ፍልሚያ እያዘጋጀችና ዝግጅቷን እያጧጧፈቺው ተገኛለች!
2019/05/28 11:36
📌በአውሮፓ 5ቱ ታላላቅ ሊጎች እንደ ማን ሲቲ ብዙ የማሸነፍ Rate ያለው ቡድን የለም
2019/05/28 11:36
👉ኡናይ ኤምሬ፡- በጣም ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ዋንጫም ስለማሸነፍ በ ቀጣይ አመትም ቻምፒዬንስ ሊግ ስለመሳተፍ እናውቃለን ሚኪም የለም ደጋፊዎችም ብዙ የሉንም ግን ይህ እድል ሊያመልጠን አይገባም እንደምንም ማሸነፍ አለብን፡፡
2019/05/28 11:36
📌Map of premier league teams 2019/20
2019/05/28 11:36
🔴 ማንችስተር ዩናይትዶች የሪያል ቤቲሱን ድንቅ አማካይ ጆቫኒ ሎሴልሶ ን ለማስፈረም ጥረት መጀመራቸው ተዘግቧል ይሄ ልጅ በዘንድሮው የላሊጋ ሲዝን ድንቅ ጊዜ ከ ቤቲስ ጋር አሳልፏል ቶተንሀም እና ማድሪድ የ ዩናይትድ ዋንኛ ተፎካካሪዎች ናቸው።
2019/05/28 11:34
♻️በእለተ ማክሰኞ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ #Share ማድረግዎን አይርሱ! ═════════════════════════ ▶️ባርሴሎና ለፖርቹጋላዊው አማካያቸው አንድሬ ጎሜዝ ከዌስትሀም የቀረበላቸውን £18m ውድቅ አድርገዋል።የካታሎኑ ክለብም ከ£25m እስከ £35m ለ 25 አመቱ አማካያቸው የዝውውር ዋጋ ይፈልጋሉ።(Source: SkySports) ═════════════════════════ ▶️ስሙ ከቶተንሀም ጋር ተያይዞ እየተነሳ የሚገኘው የ 19 አመቱ ጣልያናዊ አማካይ ኒኮሎ ዛኔሎ በሮማ እንደሚቆይ ተናግሯል። (Source: Calciomercato) ═════════════════════════ ▶️ማንችስተር ሲቲ ወደ ውድድሩ ተቀላቅሉዋል £40m- የተገመተውን የሞናኮውን አማካይ ዩሪ ቴልማስን ለማስፈረም።በጥሩ የዝውውር መስኮት በውሰት የወሰዱት ሌስተር ሲቲዎችም የ 22 አመቱን ቤልጄማዊ አማካይ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።(Source: Sun Sport) ═════════════════════════ ▶️የቀድሞ የቸልሲ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በኢንተር ሚላን እስከ ሰኔ 2022 የሚያቆየውን ኮንትራት ሊፈርም ነው በአመትም €12m ወደ ካዝናው ይከታል።(Source: Fabrizio Romano) ═════════════════════════ ▶️የፓሪሴንዤርመኑ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ኔይማር እና ኬለን ምባፔ ይቆያሉ ብሎ ማረጋገጫ መስጠት እንደማይችል ተናግረዋል ነገር ግን በክለቡ እንዲቆዩ ፍላጎቱ እንደሆነ ተናግሯል።(Sky Sports) ═════════════════════════ ▶️ፓሪሴንዤርመን እየተወያየ ይገኛል ከሊቨርፑል ጋር ያለው ኮንትራት በቀጣዩ አመት የሚጠናቀቀውን የ 33 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ጀምስ ሚልነርን ለማስፈረም።(Source: Le Parisien) ═════════════════════════ ▶️አንቶኒዮ ኮንቴ በዚህ ሳምንት ለኢንተር ሚላን ኮንትራት ይፈርማል።በዋንዳሜትሮፖሊታኖ የሚደረገውን የቻምፕዮን ሊግ ጫወታም ከኢንተር ሚላን ቦርድ ጋርም ሆኖ ነው የሚመለከተው። (Source: @DiMarzio) ═════════════════════════ ▶️ቸልሲ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪን በዚህ ክረምት የማሰናበት ምንም አይነት እቅድ የላቸውም።(Source: SkySports) ═════════════════════════ ▶️ማንችስተር ዩናይትድ እና ሬያል ማድሪድ ቶተንሀምን በመቀላቀል አማካዩን ጆቫኒ ሌሴልሶን ከሬያል ቤቲስ ማስፈረም ይፈልጋሉ የውል ማፍረሻውም €100m እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል።(Source: MARCA) ═════════════════════════ ▶️ማንችስተር ሲቲም ሌሴልሶን እየተከታተለው ይገኛል።(Manchester Evening News) ═════════════════════════ ▶️ቶተንሀም ሆስፐር £20m እንዲከፍሉ ተነግሩዋቸዋል የሊድስ ዩናይትዱን የክንፍ መስመር ተጫዋች ጃክ ክላርክን ለማስፈረም።(Source: Daily Mirror) ═════════════════════════ ▶️የባየርሙኒኩ ፕሬዝዳንት ኦሊ ሆነሽ ለጀርመናዊው ተከላካይ ጄሮም ቦቲንግ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቅ ነግረውታል።(Source: BILD) ═════════════════════════ ▶የቸልሲው አለቃ ማውሪዚዮ ሳሪ ከጁቬንቱስ ጋር ከስምምነት ደርሰዋል ቀጣዩ የቢያንኮነሬዎቹ አሰልጣኝ ለመሆን በሰማያዊዎቹ ቤትም በአመት ከሚያገኘው ደሞዝ£1.2m ይጨምርለታል።(Mail) ═════════════════════════ ▶የቤልጄም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የመጀመሪያ አማራጩ የባርሴሎና አሰልጣኝ መሆን ነው አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫሌቬርዴ በአሰልጣኝነታቸው የማይቀጥሉ ከሆነ።(RAC 1- in Spanish) ═════════════════════════ ▶የሆላንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን፤የቀድሞ የጁቬንቱሱ አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ እና የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን ለመተካት ባርሳ እያጤነባቸው ይገኛል።(Mundo Deportivo - in Spanish) ═════════════════════════ ▶የጁቬንቱሱ የ 25 አመት አርጀንቲናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ፖል ዲባላ በቀጣይ አመትም በሴሪያው ሻምፕዮን ክለብ ውስጥ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል ስሙ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ተያይዞ ቢነሳም። (Independent) ═════════════════════════ ▶አርሰናል ከኤስሚላን ጋር ተገናኝቱዋል በ 20 አመቱ ጣልያናዊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጆ ዳናሮማ ዝውውር ጉዳይ ላይ ለመነጋገር።(Tutto Mercato Web via Star) ═════════════════════════ ▶ሬያል ማድሪድ የ 27 አመቱን ብራዚላዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኔይማርን ለማስፈረም በሳምንት የግድ £1.2m ሳምንታዊ ደሞዝ ሊከፍሉት ይጠበቅባቸዋል።(AS via Mail) ═════════════════════════ ▶ሬያል ማድሪድ በዚህ ክረምት ከተጫዋቾች ሽያጭ እስከ €300m ይፈልጋሉ።(Marca) ═════════════════════════ ▶ እንደ ኢንትራንክፍራንክፈርቱ ሰርቢያዊ አጥቂ ሉካ ዩቪች እምነት ፕሪምየርሊጉ ወይም ሴሪያው ለሱ አመቺ እንደሆነ ተናግሯል በቀጣዩ የሚዘዋወር ከሆነም ወዴት እንደሚዘዋወር እንግዲህ ከወዲሁ ፍንጭ እየሰጠ ይገኛል።(Die Welt via Mirror) ═════════════════════════ ▶የ 20 አመቱ ፈረንሳያዊው የሊዮን አማካይ ሆሴም ኦውራ በሊቨርፑል ክትትል እየተደረገበት ነው ምንም እንኩዋን ተጫዋቹ በማንችስተር ሲቲ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስር የመስራት ፍላጎት ቢኖረውም። (Mirror) ═════════════════════════ ▶ጀርመናዊው ሌጀንድ ሉተር ማታውስ በእርግጠኝነት የ 23 አመቱ ጀርመናዊ የማንችስተር ሲቲ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሊሮይ ሳኔ በዚህ ክረምት ባየርሙኒክን ይቀላቀላል ሲል ተናግሯል።(Sky Sports - in German) ═════════════════════════ ▶የቀድሞ የቸልሲ እና የቶተንሀም አሰልጣኝ አንድሬስ ቪላስ ቦዋስ የማርሴ አሰልጣኝ ለመሆን ከስምምነት ደርሰዋል።(France Football - in French) ═════════════════════════ ▶የበርንሌው አሰልጣኝ ሺያን ዳች በዚህ የክረምት የዝውውር መስኮት ምንም አይነት ተጫዋች ለመሸጥ ጫና ውስጥ እንደማይገቡ ተናግረዋል።(Lancashire Telegraph) ═════════════════════════ ▶ሱፐር ኤጀንት ሚኖ ራዮላ ማቲያስ ዴሊት ለማንችስተር ዩናይትድ አቅርቦታል።ባርሴሎና ለተከላካዩ በአመት ከ €9m በላይ የመክፈል ፍላጎት የላቸውም ነገር ግን ዩናይትድ €14m የመክፈል ፍላጎት አላቸው።(Source: Duncan Castles) ═════════════════════════ ▶ራዳሚል ፋልካኦ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከ 6 አመታት ቆይታ ቡኃላ በድጋሚ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ሊመለስ ይችላል። (Source: Mundo Deportivo) ═════════════════════════ ▶ባርሴሎና በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከክለቡ 9 ተጫዋቾችን ለመሸጥ እየተመለከቱ ይገኛሉ ከዚህም ውስጥ ኮቲኖ፣ኡምቲ፣ራኪቲች እና ማልኮም ይገኙበታል በተመሳሳይ ጄሮም ቦቲንግ፣ጀስፐር ሴሊሰን ቶማስ ቨርማለን እና ራፉኒያም ከለቃቂዎቹ ውስጥ ይገኙበታል።(Source: D
2019/05/28 11:33
ዕለተ ማክሰኞ ጠዋት የወጡ አዳዲስ ስፖርታዊ መረጃዎች 👉 ሼክ ቢን አልዛይድ ቢንያህን የ እንግሊዙን ክለብ ኒውካስል ዩናይትድን በ350 ሚልዮን ፓውንድ ለመግዛት ከ ክለቡ ባለቤት አሽሊ ዊልያምስ ጋር ተሰስማሙ ድሮ ስምምነቱ ወደ ፕሪሜር ሊግ ፈደሬሽን ጋር ገብቷል ሼክ ቢን ዛይድ ዱባይ ዉስጥ የሚገኝ ባልሃብት ሲሆን ለ ማንቸስተር ሲቲ ባለቤት የ አጎታሞች ልጆች መሆናቸውን ታውቋል እናም ሼክ ቢን ዛይድ ከዚ ቀደም ሊቨርፑልን ለመግዛት እስከ ሁለትቢልዮን ፓውንድ መመደቡን ይታወሳል። 👉 አንቶንዮ ኮንቴ ከ ኢንተርሚላን ጋር ለማሰልጠን ስምምነት ላይ መድረሱን ታወቀ፡ኮንተ በ ዓመት 4ሚልዮን ዩሮ እንደሚከፈለው ና እስከ 2022 ዉል መፈራረሙን ታውቋል በ ሰኔ ወር ላይ ከ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ቡድኑን ይረከባል ተብሏል። 👉 የእንግሊዙ ዳኛ ማይክ ዲን ባለፈው ቅዳሜ ቀን የዜና ርእስ ሆኖ ሰንብቶ ነበር፡ማይክ ዲን በሁለተኛ ሊግ ላይ የሚጫወተውን ክለብ ተራንመረ ሚባለው ክለብ ለመደገፍ ነው የገባው እናም ቅዳሜ ቀን ዌምብለይ ላይ ክለቡ ትራንመረ ወደ ጥሎ ማለፍ ከ ኒው ፖርት ጋር ተጫውቷል እናም ማይክ ዲን በጨዋታው ላይ ተገኝቶ ቡድኑን ሲደግፍና ደስታውን ሲገልጽ ታይቷል። 👉 ስዊዘርላንዳዊው የ ያንግቦይስ ተጨዋች ሎሪስ በኒቶ ወደ ኒውካስለ ለመቀላቀል ከጫፍ መደረሱን ተገለፀ፡ሎሪስ በኒቶ ባለፈው ሳመንት ክለቡ ያንግቦይስ የሊጉን ዋንጫ ከበላ በኋላ በጽምብሉ ላይ ደጋፊዎቹን ተሰናብቷል እናም ዛሬ ጠዋት ወደ ለንደን መግባቱን በኢንስተግራሙ ላይ ፎቶ መልቀቁ ታውቋል። 👉 ባርሳ የ ጁቬንቱስን አሰልጣኝ የነበርውን ማስሚላኖ አለግሪን ለመቅጠር ሃሳብ እንዳለው ተገለጸ፡በዘንድሮ ዓመት ቫልቬርደ ከ ባርሳ ጋር ኮንትራት ይጨመርለታል ሲባል ነበር ሆኖም ግን አሁን አሁን ከ ቻምፕዮንስ ሊግና ኮፓ ደላ ሬይ ሽንፈት ካስተናገደ በኋላ ባርሳ ለማባረር የውስናል ተብሎ ይጠበቃል እናም በሱ ምትክ አለግሪን ለመቅጠር አስበዋል የተባለ ነው። 👉 ማንችስተር ዩናይትዶች የሪያል ቤቲሱን ድንቅ አማካይ ጆቫኒ ሎሴልሶ ን ለማስፈረም ጥረት መጀመራቸው ተዘግቧል ይሄ ልጅ በዘንድሮው የላሊጋ ሲዝን ድንቅ ጊዜ ከ ቤቲስ ጋር አሳልፏል ቶተንሀም እና ማድሪድ የ ዩናይትድ ዋንኛ ተፎካካሪዎች ናቸው። MARCA 👉 ራዳሜል ፋልካኦ ወደ ቀድሞ ክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ሊመለስ ነዉ። 👉 የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ Zinedin zidane ሰርጂዮ ራሞስ ክለቡን እንዲለቅ እንደማይፈልግ ተናገረ ስሙ ከማን ዪናይትድ ጋር ተያይዞ መነሳቱን ተከትሎ። 👉 የቀድሞ የማን ዪናይትድ ተጨዋች ሜፒስ ዴፓይ የሊቨርፑል የመጀመሪያ ፈራሚ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል ከቻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ በኋላ ዝዉዉሩ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። 👉የ ማንችስተር ሲቲዉ አማካኝ David Silva በ 15 ሚሊየን ዮሮ ወደ ኳታር ክለቦች ሊዛወር እንደሚችል ዛሬ ጠዋት AS አስነብቧል :: ፔፕ ሲልቫን ለመተካት ዩሪ ቲለማንስን በ 40 ሚሊየን ፓዉንድ ከ ሞናኮ ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ ነዉ :[ AS ] 👉 የዩቬንቱሱ አጥቂ ሞይሴ ኪን ከዩቬንቱስ ጋር እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራት ለመፈራረም ተስማምቷል።በአዲሱ ኮንትራት የሳምንት ደሞዙ ከ€11,000 ዩሮ ወደ €22,000 እንደሚያድግ ተነግሯል።GAZZETA DE LO SPORT 👉 ናፖሊ ግሪካዊውን የሮማ ተከላካይ ኮስታስ ማኖላስ ለማስፈረም በሚደረገው ጥረት ከአርሰናል እና ማን ዩናይትድ ጋር ፊክክር መጀመሩ ታውቋል።II TEMPO 👉የ ሊዮኑ አማካኝ Houssem Aouar በ ማንችስተር ሲቲዉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዎላ ስር መሰልጠን እንደሚፈልግ ተናግሯል :: 👉 ቢን ስፓርት ቅዳሜ የሚደረገውን የ ቻምፒዬንስ ሊግ ፋፃሜ ጨወታ በ ተንታኝነት አርሰን ዌንገር እና ጆዜ ሞሪንሆ ስቱዲዬ እንደሚኖሩ አስታውቁዋል፡፡ 👉 ኡናይ ኤምሬ፡- በጣም ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ዋንጫም ስለማሸነፍ በ ቀጣይ አመትም ቻምፒዬንስ ሊግ ስለመሳተፍ እናውቃለን ሚኪም የለም ደጋፊዎችም ብዙ የሉንም ግን ይህ እድል ሊያመልጠን አይገባም እንደምንም ማሸነፍ አለብን፡፡ 👉 ባርሴሎና ከአሌግሪ በተጨማሪ ኤርኔስቶ ቫልቨርዴን ለመተካት 4 እጩዎችን ይዙዋል፡፡ 4ቱ እጩዎች ፡፡ ኤሪክ ቴን ሃግ ሮናልድ ኩማን ሎረን ብላ እና ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ናቸው ከነዚ ውስጥ 1ዱን ሊቀጥሩ ይቻላሉ ፡፡ ባርሴሎናዎች ግን ምርጫቸው ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የሆነ ይመስላል የ ባርሳው ፕሬዜዳት ሆሴፍ ማርያ ባርቶሚዬ ከ ማርቲኔዝ ጋ ተገናኝቶ መክርዋል በዚ ጉዳይ ፡፡ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ አሁን የ ቤልጄም ብሄራዊ ቡድንን በማሰልጠን ላይ ይገኛል በ አለም ዋንጫው ቤልጀምን 3ኛ ደረጃ ይዛ እንድታጠናቅቅ ማረጉ ትልቁ ስኬቱ ነው ፡፡ ከዚ ቀደም በ እንግሊዝ ስዋንሲ ዊጋን ኤቨርተንን ለ ረዥም ጊዜ ማሰልጠኑ ይታወሳል፡፡ source dilario sport 👉 ጀርመናዊው የመድፈኞቹ ሹት ስቶፐሩ ግብ ጠባቂ በርንድ ሌኖ ኢሮፓ ሊግ ፋይናል መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል። እንዲህም ይላል ሌኖ”የኢሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ለኔ የመጀመሪያው ትልቁ ስኬት ነው፤ለፒተር ቼክ ትልቅ ክብር አለኝ ቢሆንም ግን ፋይናል መጫወት የኔም ምኞት ነው”።
2019/05/28 11:33
📌በማን ዩናይትድ ሲፈለግ የነበረው ኮከብ ጃዶን ሳንቾ በዚህ ክረምት ዶርትሞንድን እንደማይለቅ ተናገረ። (The Sun)
2019/05/26 21:38
📌ማንችስተር ዩናይትድ የስዋንሲውን አማካኝ ሳን ሎንግስታፍ ለማስፈረም ንግግር ጀምሯል። (The Sun)
2019/05/26 21:38
🚨 #ሰበር_ዜና 🚨 👉የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋቾች ጋብሬል ፖሊስታ ፍራንሲስ ኮኬን ወደ ቀድሞ ክለባቸው አርሰናል መመለስ እንደሚፈልጉ እና በኡናይ ኤምሬ መሰልጠን እንደሚፈልጉ ከትላንቱ የኮፓ ዴላሬ ባርሳን ካሸነፉበት ጨዋታ በኃላ ተናግረዋል። (Dream Team)
2019/05/26 21:38
📌የኤሲ ሚላን ኢቫን ጋዲዚ ከጁቬ አለቃ ማስሜላኖ አሌግሪኒን አሰልጣኝ አርጎ ለመቅጠር ንግግራቸውን ጀመሩ። (The Sun)
2019/05/26 21:38
☑️ የቸልሲው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ሳሪ ከዩቬንቱስ ጋር የ3 አመት ኮንትራት ለመፈራረም መቃረባቸው እየተዘገበ ይገኛል።ዝውውሩ ከእሮቡ የኢሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ቡሀላ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል።(THE SUN)
2019/05/26 21:38
☑️ቸልሲ ኤዲን ሀዛርድ ማድሪድ £130 ሚሊዮን ከከፈለ ነው ልጁን የምንሰጠው ብለዋል።(Sky Sports)
2019/05/26 21:38
🧤ዴቪድ ዴህያ ማንችስተር ዩናይትድን የሚለቅ ከሆነ ሰርጂዮ ሮሜሮ በቋሚ አሰላለፍ ሊገባ ይችላል።
2019/05/26 21:38
📌የP.S.G አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል እስከ 2021 የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል።✍
2019/05/26 21:38
🏆የስፔን ኮፓ ዴልሪ ፍፃሜ ጨዋታ ዉጤት መግለጫ። 👉FULL TIME⌚️ 🔵ባርሴሎና 1⃣ - 2⃣ ቫሌንሲያ⚪️ #ሜሲ '73⚽️ #ጋሜሮ '22⚽️ #ሮድሪጎ '34⚽️
2019/05/26 15:24
🏆ቫሌንሲያ የ2018/19 ኮፓ ዴልሪ አሸናፊ ሆኑ። 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
2019/05/26 15:24
🇧🇷የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ዛሬ የመጀመሪያ ልምምዳቸዉን ጀምረዋል።
2019/05/25 11:14
👉 2009-10 ⚽34 ጎል✅ 👉 2011-12 ⚽ 50 ጎል✅ 👉 2012-13 ⚽ 46 ጎል✅ 👉2016-17 ⚽37 ጎል✅ 👉 2017-18 ⚽ 34 ጎል✅ 👉 2018-18 ⚽ 36✅ 🦋ሊዮ ሜሲ 36 ጎሎችን በማስቆጠር የአውሮፓ የወርቅ ጫማ አሸናፊ ሆኗል።
2019/05/25 11:14
✔️የሊቨርፑሉ እንግሊዛዊ የ28 አመት ተከላካይ ናትናኤል ክልያን ከጣሊያኑ ክለብ ናፖሊ የዝውውር ጥያቄ ቀርቦለታል። ክሪስታል ፓላስ፣ ዌስትሃም እና በርንማውዝም የተጭዋቹ ፈላጊዎች ናቸው። በሁለተኛው የሲዝኑ አጋማሽ በበርንማውዝ በውሰት ያሳለፈውን ተከላካይ ለመልቀቅ ቀያዮቹ የ £15m ሂሳብ ይፈልጋሉ። (Sky Sports) ═════════════════════════ ✔ ኤቨርተኖች የአርሰናሉን እንግሊዛዊ የ28 አመት የፊት መስመር ተጫዋች ዳኒ ዌልቤክን በነፃ ለማዛወር የተሻለ እድል ይዘዋል። (Evening Standard) ═════════════════════════ ✔ አርሰናል ከሱፐር ኤጀንት ሚኖ ራዮላ ጋር እየተነጋገሩ ነው የግሪካዊውን የመሀል ተከላካይ ኮስታስ ማኖላስን £31.1m የውል ማፍረሻ በመክፈል ከሮማ ለማስፈረም። (ሚረር) ═════════════════════════ ✔ ቤልጄማዊው ኮከብ ያኒክ ካራስኮ ከ The sun ጋር ባደረገው ቆይታ ወደ እንግሊዝ ማቅናት እና አዲስ ፈተና ፈልጋለው ማለቱን ተከትሎ ለመድፈኞቹ ጥያቄ በሩን ክፍት አድርጓል! ═════════════════════════ ✔ ️መድፈኞቹ ለጀርመን ከ 21 አመት በታች ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነውን የDynamo Dresden ማርከስ ሹበርትን ለማስፈረም እየተመለከቱት ነው የፒተር ቼክ ተተኪ እንዲሆንላቸው። (Bild - in German) ═════════════════════════ ✔ ️መድፈኞቹ አርመናዊውን አማካይ ሄነሪክ ሚኪታርያንን ለመሸጥ ተዘጋጅቷል። [sun] በዚህ አመት በዩናይ ኤምሪ ስር 39ጫወታዎችን አድርጎ 6ጎል ሰባት ኳሶችን ደግሞ አመቻችቷል ═════════════════════════ ✔ የባየር ሙኒኩ ፕሬዝዳንት ኡሊ ኮነሽ የማንቸስተር ሲቲው የክንፍ ተጭዋች ሎሪ ሳኔ የክረምቱ ዋነኛው የዝውውር ኢላማቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል። (Source: Suddeutsche Zeitung) ═════════════════════════ ✔ ቶተንሃሞች ማርኮ አሴንሲዮን ስለሚያዛውሩበት ሁኔታ ላይ ከስፔኑ ክለብ ጋር ድርድር ለመጀመር ተዘጋጁ። ሆኖም ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ለሽያጭ የቀረበ እንዳልሆነ ተናነግሯቸዋል። (Source: AS) ═════════════════════════ ✔ አርሰናል አርጀንቲናዊውን የሪቨር ፕሌት የመሃል ሜዳ ቀማሪ ኤኩየል ፓላሲዮን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል። 👉 ተጫዋቹ ወደ አርሰናል እንዲመጣ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል... ሜዳ ላይ ከሚያሳያቸው የኳስ ፈጠራ ብቃቱ እንዲሁም ከሳጥን ሳጥን እየተሯሯጠ የሚጫወትበት መንገድ በክረምቱ አሮጊቶቹን የተቀላቀለውን ዌልሳዊ አሮን ራምሴ ሁነኛ ምትክ እንደሚሆን ይጠበቃል። 👉 ወጣቱ እድሜው ገና 20 አመት ሲሆን በሪቨር ፕሌት ቀዳሚ ተመራጭ በመሆን ቋሚ ቦታ ተሰጥቶት በመጫወት ላይ ይገኛል፣ ተጫዋቹ ከአርሰናል ጋር የሚሄድ አይነት የአጨዋወት ዘይቤን የሚከተል በመሆኑ እንዲሁም ለኦናይ ኤምሬ የአሰለጣጠን ስርዓት አመቺ በመሆኑ ልጁን ወደ ኤምሬት ለማስኮብለል ነገሮችን ቀላል ያደርጋቸዋል። 👉 ከሁሉም ደግሞ ከአርሰናል ጋር ያለው ለተጫዋቾች ግዢ ካለው በጀት አንፃር ልጁ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ አይደለም ለዝውውሩ ከ 18–20 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ወጪ ተለጥፎበታል። 👉 የአርሰናል መልማዮች አይናቸውን ጥሩ እይታ ላይ ያሳረፉ ይመስላል። 👉 ከላይ የተዘረዘሩትን ምክንያቶች መሰረት በማድረግ ተጫዋቹ በዚህ ክረምት ወደ አርሰናል የሚያመራ ይመስላል ሲል በፊት ገፁ ላይ አስፍሮታል። [The Mirror] ═════════════════════════ ✔ ባኩ በደጋፊዎች ላትደምቅ ነው ..... ➪ የአርሰናል የቼልሲ ደጋፊዎች ለፍፃሜው ጨዋታ የገዙትን ትኬት ሊመልሱ እንደሆነ የተዘገበ ሲሆን አርሰናል ከስድስት ሺህ ትኬት ሁለት ሺህ ትኬት እንደሚመልስ አሳውቋል ቼልሲ ደሞ 4ሺህ ቲኬት ይመልሳል ተብሏል UEFA ትልቅ ስህተት ሰርቷል:: የቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር አዲስ ሚና ይዘው ወደ እግር ኳሱ እንደሚመለሱ አስታወቁ፡፡ 22 ዓመታትን በአርሰናል የቆዩትና በፈረንጆቹ 2017-2018 የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር የተለያዩት ቬንገር ወደ እግር ኳሱ ዓለም እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል። ቬንገር በንግግራቸው ወደ እግር ኳሱ ዓለም ቢመለሱም ወደ አሰልጣኝነቱ ላይመለሱ እንደሚችሉ ነው ፍንጭ የሰጡት፡፡ አርሰን ቬንገር በስፖርቱ ዓለም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከተሰማራ ኩባንያ ጋር ድርሻ ገዝተው በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። ቬንገር በኩባንያው ድርሻ እንደሚኖራቸውና በአማካሪነት እንደሚሰሩ ይጠበቃል፡፡ ኩባንያው ቬንገር በንግድ እና በምርት ልማት ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው የገለጸ ሲሆን፥ በተጫዋቾች የቴክኒካል፣ ታክቲካል እና አካላዊ ብቃት ላይ ሙያዊ ትንተና ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ ይህም አርሰን ቬንገር በእግር ኳስ ያላቸውን ተሳትፎ እንደማያቋርጠውም ገልጿል። ═════════════════════════ ✔ መቀሌ 70 እንደርታ ተቀጥቷል ...... መቀሌ 70 እንደርታ 75ሺ ብር እና አንድ ጨዋታ በዝግ እንዲጫዎት በተጨማሪም የፋሲል ከነማ ተጨዋቾችን የህክምና ወጭ እንዲከፍል ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ወስኗል ። በትግራይ ስታዲየም ደደቢት በሜዳው ፋሲል ከነማን አስተናግዶ ፋሲሎች 5-1 በረቱበት ጨዋታ የመቀሌ ደጋፊዎች የፋሲል ከነማ ተጨዋቾች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው የሚታወቅ ነው ። የፌዴሬሽኑ ዲስኘሊን ኮሚቴ ደደቢትን በመቅጣት መቀሌዎችን ቢያልፍም ፋሲሎች ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ለእግርኳሳችን ትክክለኛውንና የሚበጀውን ውሳኔ አሳልፏል ። በዚህ መሰረት መቀሌ 70 እንደርታ 75ሺ ብር እና አንድ ጨዋታ በዝግ እንዲጫዎት በተጨማሪም የፋሲል ከነማ ተጨዋቾችን የህክምና ወጭ ፋሲል ከነማ በሚያቀርበው የህክምና ወጭ ማስረጃ መሰረት እንዲከፍል ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ወስኗል ። (ምንጭ - ሶከር ኢትዮጵያ) ═════════════════════════ ✔ አዳማ ላይ ሊካሄድ የነበረው የሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ወደ ሌላ ሜዳ ተሸጋገረ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ አንድ የሜዳው ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲያከናውን በመቀጣቱ ምክንያት አዳማ ላይ ነገ ሊካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም የአዳማ ከተማ ፀጥታ አካላት ኃላፊነት አልወስድም በማለታቸው ጨዋታው ወደ አሰላ ስታዲየም እንደተሸጋገረ ለማወቅ ተችሏል። በዚህም ነገ 9:00 ላይ በአሰላ አረንጓዴ ስታድየም የሚከናወን ይሆናል። ሀዋሳ ከተማ ወደ አሰላ ተጉዞ ጨዋታ ሲያደርግ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በሀዋሳ በነበረው የፀጥታ ስጋት ወደ አረንጓዴው ስታዲየም ተዘዋውሮ 0-0 መለያየቱ የሚታወስ ነው። (ምንጭ - ሶከር ኢትዮጵያ) ═════════════════════════
2019/05/25 11:13
ቅዳሜ የወጡ በርካታ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update! ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር አድርጉት! ═════════════════════════ ✔ የቢቢሲው ጋዜጠኛ ሲሞን ስቶን.. “ላረጋግጥላችሁ የምችለው ዲ ሊዥት ሳምንታዊ £250,000 እየተከፈለው ለማን.ዩናይትድ ለመፈረም በግሉ ተስማምቷል። ከአያክስ ጋር ከአመሻሽ ጀምሮ ድርድር እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። ከባርሴሎና መንጋጋ ውስጥ ፈልቅቀው ዝውውሩ የሚሳካ ከሆነ ለኢድ ውድዋርድ ትልቅ ስኬት ይሆናል።" [bbc] ═════════════════════════ ✔ ማንቸስተር ዩናይትዶች ማቲያስ ዲ ላይትን ወደ ክለባቸው ለማምጣት አሁን በአያክስ የ ስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ስራ ላይ ያለውን የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ በረኛ ኤድዊን ቫን ደር ሰርን እየተጠቀሙበት ነው። [Marca] ═════════════════════════ ✔ ሪዮ ፈርዲናንድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ያነሳውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ፎቶ ኢንስታግራም ገፁ ላይ ለጥፎት ማቲያስ ዲ ላይት ፖስቱን ላይክ በማድረጉ የ19 አመቱ አምበል እና የመሀል ተከላካይ ወደ ዩናይትድ ሊዛወር ይችላል የሚለውን መረጃ ወደላቀ ደረጃ አድርሶታል። [instagram] ═════════════════════════ ✔ ሊቨርፑል፣ ማን.ዩናይትድ እና አርሰናሎች ከሪያል ማድሪድ በውሰት ተሰጥቶ በዚህ ክረምት ላይ ወደ በርናባው ይመለሳል የተባለውን ሃምስ ሮድሪጌዝ ለማዛወር ፍላጎት አሳይተዋል። (Source: Daily Mirror) ═════════════════════════ ✔ አንቶዋን ግሪዝማን አትሌቲኮ ማድሪድን እንደሚለቅ ካሳወቀ በኋላ ማንቸስተር ዩናይትዶች የሱን ጉዳይ አቋርጠው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ድጋሚ በማንሰራራት ውል ማፍረሻውን ለመክፈል ተዘጋጅተዋል። ከተለያዩ ክለቦችም ጋር ብርቱ ፉክክር ይገጥማቸዋል። [livesoccertv] ═════════════════════════ ✔ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር እና ማይክ ፌላን ጃደን ሳንቾ ክለቡን እንዲቀላቀል ኢድ ዉድዋርድን አናግረውታል። [Express] ═════════════════════════ ✔ የ28 አመቱ ስፔናዊ የቼልሲ ተከላካይ ማርኮስ አሴስንሶ በኦክቶበር ወር ላይ በክለቡ ለተጨማሪ አምስት አመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ቢፈራረምም ክለቡን ሊለቅ ይችላል። (Evening Standard) ═════════════════════════ ✔ በተያያዘ ዜና የሰማያዊዎቹ እና የቤልጂየሙ ፊት አውራሪ የ28 አመቱ ኤዲን ሃዛርድ የሪያል ማድሪድ ዝውውሩ በጁን 4 ይፋ እንዲሆን ይፈልጋል። ሆኖም ሁለቱ ክለቦች መሃል በተጭዋቹ የዝውውር ሂሳብ የ£26m ልዩነት አለ። ሪያሎች እስካሁን የ £86m አቅርበዋል ቼልሲዎች ግን የ £112m ሂሳብ ጠይቀዋል። (Mirror) ═════════════════════════ ✔ ሮሜሉ ሉካኩ ፣ ማርከስ ሮሆ፣ ሁዋን ማታ እና ማቲዩ ዳርሚያን በክለቡ እንደማይፈለጉ መልቀቃቸው እንደማይቀር ተዘገበ። [Mirror] ═════════════════════════ ✔ የቤኔፊካው ፕሬዝዳንት ስለ ጃኦ ፌሊክስ... "ወይ የሚፈልጉት ክለቦች 120 ሚሊየን ውል ማፍረሻውን ይከፍሉናል ወይም ደግሞ ፌሊክስ ከኛ ጋር ይቆያል።" ═════════════════════════ ✔ ማንቸስተር ዩናይትዶች ለ ሮሜሉ ሉካኩ ተተኪነት ያቀዱትን የ ልዮኑ አጥቂ ሞውሳ ደምበሌን ለማስፈረም የመጀመሪያ 40 ሚሊየን ዩሮ አቅርበዋል። [Goal france] ═════════════════════════ ✔ በተያያዘ ዘገባ የሞውሳ ደምበሌ ዝውውር የማይሳካ ከሆነ ዩናይትዶች ፊታቸውን ወደ ኤቨርተኑ ብራዚላዊ የፊት አጥቂ ሪቻርልሰን ያዞራሉ። [Express] ═════════════════════════ ✔ ብሩኖ ፈርናንዴዝ... "ሁሌም እንደምለው እኔ የምጓጓ ተጫዋች ነኝ ፤ በቅርብ ጊዜ ህይወቴ ደግሞ እንግሊዝ ውስጥ መጫወት ህልሜ ሆነ። ንትርክ ያልበዛበት ጥርት ያለ እግርኳስ ያለበት ቦታ ነው።" [sportwitness] ═════════════════════════ ✔ "በህይወት ዘመኔ ከገጠሙኝ አሳዛኝ ነገሮች አንዱ የአንፊልዱ ሽንፈት ነው" ሊዮኔል ሜሲ [The sun] ═════════════════════════ ✔ ፓውሎ ዲባላ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ስሙ በተደጋጋሚ እየተነሳ ቢሆንም ፤ ትላንት በተናገረው መሠረት ከአሮጊቶቹ ጋር ለተጨማሪ አመታት እንደሚቆይ አስታውቋል። [The sun] ═════════════════════════ ✔ ስታም... "ሆላንድ እያለሁ ታላቅ ነበርኩኝ ዩናይትድ ስመጣ ግን ትንሽ ሆንኩኝ ፤ እንደ ኪን ፣ ሽማይክል ፣ ስኩልስ እና ጊግስ ያሉ ተጫዋቾች ሁሉም አለም ጉብዝናቸውን የመሰከረላቸው ተጫዋቾች ነበሩ። እንደውም ቡድኑን ስቀላቀል አብዛኞቹ አያውቁኝም ነበር።" [The sun] ═════════════════════════ ✔ የፕርሜርሊጉ ተወዳጅ አሰልጣኝ ማውርስዮ ፖቸቲኖ ከሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጫወታ በፊት በወደፊት ቆይታው ዙርያ ምንም አይነት ውሳኔ እንደማያስተላልፍ ተናግሯል። [The sun] ═════════════════════════ ✔ የሎስ ብላንኮዎቹ ካፒቴን ሰርጂዮ ራሞስ በክረምቱ ሳንቲያጎ በርናባውን ስለመልቀቅ እያጤነ ነው። ይህንንም ተከትሎ ፒኤስጂ እና ማንችስተር ዩናይትድ የተጫዋቹ ፈላጊ ክለቦች ናቸው። [Marca] ═════════════════════════ ✔ "የአርሰናል ጨዋታን በቴሌቪዥን እከታተል ነበር አርሰናል ትልቅ ክለብ ትልቅ ታሪክ ያለው ነው። ለዚህ ክለብ የመጫወት ህልም ነበረኝ። ለዚህ ክለብ አሁን እየተጫወትኩ ነው ህልሜን እየኖርኩ ነው" - [ ማቲዬ ጉንዶዚ] ═════════════════════════ ✔ ተፈላጊው የ 25 አመቱን ስኮትላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሬያን ፍሬዘርን ከኢሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጫወታ ቡኃላ አርሰናሎች ለማስፈረም በይፋ ለክለቡ የዝውውር ጥያቄአቸውን ያቀርባሉ። ነገር ግን እናት ክለቡ በርንስማውዝ ከተጫዋቹ ዝውውር £30m ይፈልጋሉ። (Evening Standard) ═════════════════════════ ✔ የቀድሞው የመድፈኞቹ አጥቂ ሮቢን ቫንፐርሲ ስለ ኢሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ እንዳለው አርሰናል ኢሮፓ ሊግ የማሸነፍ እድል በእጁ አለ ። እኔም ከልቤ አርሰናል ተሽሎ እንዲወጣ ምኞቴ ነው ብሏል ። እንዲሁም አርሰናል በክረምት ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ከገዛ በማንችስተር ሲቲ የተያዘውን የበላይነት አርሰናል ሊረከብ ይችላል ብለዋል። (Evening Standard) ═════════════════════════ ✔ የአርሰናል ተጫዋቾች ለሚኪታሪያን ድጋፋቸውን ለማሳየት ቲሸርት ለማሰራት ፍቃድ ተቀባይነት አግኝተዋል። ═════════════════════════ ✔ ፒተር ቼክ:- "ሚኪታሪያን አብሮን ባለመጓዙ በጣም አዝኛለሁ ለሱ ስንል ጠንክረን መጫወት እና ዋንጫውን ማንሳት አለብን። ═════════════════════════ ✔ "እኔ ሜሱት ኦዚልን የመሰለ ተጫዋች የመሸጥ ሀሳብ የለኝም፤ምክንያቱም ኦዚል ማለት ቡድንህ ውስጥ እንዲኖር የምትፈልገው አይነት ተጫዋች ነው። እሱ የሚፈጥራቸውን ማአት የጎል እድሎች ከአውሮፓ 5ቱ ታላላቅ ሊጎች እሚስተካከለው የለም"። [ኢያን ራይት] ═════════════════════════
2019/05/25 11:13
እንደ አሌክስ ሳንቼዝ በሳምንት £500,000 እየተከፈለው በየሳምንቱ ተጎዳሁ ብሎ ስራውን በትክክል የማይሰራ እንደ ክሪስ ስሞሊንግ የሚያፈስ ተከላካይ ባለበት ክለብ ወድቄ እየተነሳው ብቻየን እየተንገላታሁ የነሱን ችግር ተሸክሜ በጭራሽ በማንቸስተር ዩናይትድ መቆየት አልፈልግም [David De Gea Sky sport]
2019/05/25 11:13
👑ሜሲ 3ኛ ተከታታይ የአውሮፓ የወርቅ ጫማውን ማሳካቱን Almost አርጋግጧል።
2019/05/25 08:19
✔️በ 2018/19 ብዙ ጎል ያገቡ ከለቦች👆👆👆👆
2019/05/24 22:17
👉ፈረንሳዊዉ የሪያል ማድሪድ ተከላካይ Rapael Varane በቀጣይ አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር እቆያለዉ በዚህ ዝዉዉር መስኮት ወዴትም ክለብ የመዘዋወር እቅድ የለኝም ሲል በይፋ ተናገረ።
2019/05/24 14:12
🔴የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አስተዳዳሪ ኢድ ዉድዋርድ ከ 2017/18 የውድድር አመት ወዲህ ደሞዙ ከ 2.604 ሚሊየን ዩሮ ወደ 4.152 ሚሊየን ዩሮ አድጓል። ይህም በፐርሰንት ሲሰላ 59.44 % ይሆናል።
2019/05/24 14:12
ራቱን አሸንፏሉ። ሁለት በ winners' cup አንድ በ ቻምፒዮንስ ሊግ አንድ በ አውሮፓ ሊግ የመድፈኛችን አለቃ ዑናይ እምሪይ ስስት ጊዜ የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን በማንሳት የምስተካከላቸው አሰልጣኝ የለም ከሲቭያ ጋር በ2014፣ በ2015ና በ2016 GC ። የሰማያውዮቹ አለቃ ማርዚዮ ሳሪ የመጀመሪያ የአውሮፓ ሊግ ፊፃሜ ጨዋታቸው ነው። የቀድሞ መድፈኛ የአሁኑ የሰማያውዮቹ አጥቂ ኦልቬር ጅሩ በዜንድሮ አውሮፓ ሊግ 10 ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አስቆጣርነቱን ይመራል። አርሰናል ያለፉት 8 የአውሮፓ ሊግ ግቦች በኦባምያንግ 4ና በላካዜቲ 4 የተቆጠሩ ናቸው። የሰማያውዮቹ ኮከብ ኤድን ሀዛርድ ይህ ጨዋታ ምናልባት ለቼልሲ የመጨረሻው ልሆን ይችላል። የቀድሞ ሰማያዊ የአሁኑ የመድፈኛችን በረኛ ፒተር ቼክ ከቼልሲ ጋር በ2013 GC የአውሮፓ ሊግ ዋንጫ ያነሳ ስሆን ከውድድሩ ቦኃላ ጫማውን እንደምሰቅል ይጠበቃል። የመድፈኛችን ተጫዋች ሄነሪክ ሚክታርያ በ20 17GC ከማን ዩናይትድ ጋር የአውሮፓ ሊግ ዋንጫ ያነሳ ስሆን በዜንድሮ ፊፃሜ ጨዋታ የሚደረግበት ቦታ አዘርባጃን ከሀገሩ ጋር ባላት የፖለትካ አለመግባባት ምክንያት እንደማይሰለፍ አሳውቋል። አርሰናል በዜንድሮ አውሮፓ ሊግ ዉድድር ፊፃሜ እስክደርሱ ድረስ 14 ጨዋታዎችን አድርጎ 29 ጎል አስቆጥሮ 7 ጎል ተቆጥሮበት ፤11 ጨዋታ አሸንፎ 2 ተሸንፎ በ1 አቻ ተለያይቷል። ቼልሲ በዜንድሮ አውሮፓ ሊግ ዉድድር ከ14 ጨዋታዎችን አድርጎ 32 ጎል አስቆጥሮ 9 ጎል ተቆጥሮበት፤ 11 ጨዋታ አሸንፎ በ3 አቻ ተለያይቶ ያለሽንፈት ለፊፃሜ ደርሷሉ። የጉዳት ዝርዝር አርሰናል.. አሮን ራምሴ ደንስ ሱዋሬዝ ዳንይ ዌልበክ ሄክተር በሌሪን ሮብ ሆልድንግ ኮንስታትኖስ ማቭሮፓኖስ ️የጉዳት ዝርዝር ቼልሲ.. ጋሪይ ካህል ንጎሎ ካንተ ሎፍተስ ቼክ እታን አምፓዱ አንቶንሆ ሩድገር ሁለቱ ቡድኖች በታሪክ በሁሉም ውድድሮች ለ197 ጊዜ የተገናኙ ስሆን አርሰናል 77 ጊዜ ስያሸንፍ ቼልሲ 63 አሸንፎ በ57 ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይቷሉ። ═════════════════════════
2019/05/24 14:08
▶️የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አስተዳዳሪ ኢድ ዉድዋርድ ከ 2017/18 የውድድር አመት ወዲህ ደሞዙ ከ 2.604 ሚሊየን ዩሮ ወደ 4.152 ሚሊየን ዩሮ አድጓል። ይህም በፐርሰንት ሲሰላ 59.44 % ይሆናል። [The sun]  ═════════════════════════ ▶ሶ?ሶልሻየር አዲስ የሚገነባውን ቡድን በተራቡ ፣ ፈጣን በሆኑ ወጣት ተጫዋቾች መመስረት ማሰቡን ተከትሎ ማንቸስተር ዩናይትዶች የአያክሱን 19 አመት የመሀል ተከላካይ ማቲያስ ዲ ላይትን ከ ባርሴሎና እጅ ነጥቀው ለማስፈረም ከምንም ጊዜ በላይ ጠንክረው እየሰሩ ነው። [Catalunya radio, esport 3]  ═════════════════════════ DEAL DONE:አርጀንቲናዊው የቸልሲ በረኛ ዊሊ ካበዬሮ በእስታምፎርድ ብሪጅ ለተጨማሪ አንድ አመት የሚያቆየውን ኮንትራት መፈረሙ ተረጋግጧል። (Source: Chelsea Football Club) ═════════════════════════ ▶DEAL DONE:ጁልያን ብራንት ከባየርሊቨርኩሰን ወደ ቦርሲያዶርትመንድ በ €25m መዘዋወሩ ተረጋግጧል በክለቡም ለ 5 አመት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።(Source: Borussia Dortmund) ═════════════════════════ ▶ቶተንሀም ሆስፐር በሬያል ማድሪዱ አማካይ ዳኒ ሲባሎስ ላይ ያለውን ፍላጎት አሳይቷል ለዝውውሩም ከ€40m-€50m ለማውጣት አዘጋጅተዋል የክርስቲያን ኤሪክሰን ተተኪ እንዲሆንላቸው በማሰብ።(Source: AS) ═════════════════════════ ▶DEAL DONE: የ 38 አመቱ የአትሌቲኮ ቢልባኦው አጥቂ አሪዝ አዱሪዝ በክለቡ የሚያቆየውን የአንድ ተጨማሪ አመት ኮንትራት ፈርሟል ምንም እንኩዋን እስከ 2020 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም።(Source: Athletic Club) ═════════════════════════ ▶ኢንተር ሚላን የሮማውን ቦሲኒያዊ አጥቂ ኤደን ዤኮን ለማስፈረም መጨረሳቸው እየተነገረ ይገኛል ወደ ቻምፕዮን ሊጉ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ባያገኙም እንኩዋን።(Source: Gazzetta dello Sport) ═════════════════════════ ▶ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ ለመፎካከር ተዘጋጅተዋል የሬያል ማድሪዱን ኩዋስ አቀጣጣይ ኢስኮ እስከ €120m አውጥተው ለመግዛት።(Source: SPORT) ═════════════════════════ ▶ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣዩ አመት አዲስ ለሚገነባው ቡድን የጁቬንቱሱን የፊት መስመር ተጫዋች ፖል ዲባላን ለማስፈረም እየተነጋገሩ ነው።(Source: Daily Mail) ═════════════════════════ ▶DEAL DONE:ቦርሲያዶርትመንድ የቦርሲያሞንቸግላድባኩን ቶርጋን ሀዛርድን በ £30m ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል የ 5 አመት ኮንትራትም ፈርሟል።(Source: Borussia Dortmund) ═════════════════════════ ▶ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ እስከ £20m በማውጣት የ 21 አመቱን የፉልሜንሴ አጥቂ ፔድሮን ለማስፈረም ጠንከር ያለ ግንኙነት ከብራዚሉ ክለብ ጋር መፍጠራቸውን Daily Mail ዘግቡዋል። ═════════════════════════ ▶ጁቬንቱስ የላዚዮውን አማካይ ሰርጂ ሚሊንኮቪች ሳቪች ለማስፈረም እየተነጋገሩ ይገኛሉ።የሴሪያው ሻምፕዮንም የ 5 አመት ኮንትራትም አቅርበውለታል።(Source: Fabrizio Romano) ═════════════════════════
2019/05/23 14:46
FIFA በ 2022 የኳታር የአለም ዋንጫ ላይ የታሳታፊ ሀገራትን መጠን ወደ 48 የማሳደግ እቅዱን መተዉ ተሰምቷል፡፡ የFIFAው ፕሬዝደንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ የተሳታፊ ሀገራትን ወደ 48 የማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ለ 32 ሀገራት ስትዘጋጅ ለነበረችው ኳታር ይህ የቁጥር መጨመር ከፍተኛ ራስ ምታት ሆኖ ነበር፡፡ ኢንፋንቲኖ ይህን እቃዳቸውን ለማሳካት በአማራጭነት ኳታር የአለም ዋንጫውን ከሌሎች በአቅራቢያዋ ከሚገኙ ሀገራት ጋር እንድታዘጋጅ ነገሮች ለማመቻቸት ሞክረው ነበር፡ የኃላ ኃላ ግን 2022 የአለም ዋንጫ እንደተለመደው በ32 ሀገራት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
2019/05/23 14:46
CONFIRMED: Thorgan Hazard has joined Borussia Dortmund! 🤝 #bvb
2019/05/22 21:29
BREAKING: Olivier Giroud has signed a new deal with Chelsea until the end of the 2019-20 season! 🚨
2019/05/22 21:29
እልህ፣ ቁጭት፣ ቁርጠኝነትና ታዳጊው ሮናልዶ ....ክሪስቲያኖ የአሰላለፍ ዝርዝሩን በአንክሮ ቢመለከተውም ስሙን አላገኘውም። ደጋግሞ ተመለከተው። አሁንም ስሙ እንደሌለ አረጋገጠ። ከዚያ ተንሰቅስቆ አለቀሰ። በስፖርቲንግ አካዳሚ ተመልምሎ በሊዝበን ከተማ በመኖሩ ያደገባትን ደሴት፣ ሩቋን ማዴይራን ናፍቋል። የስፖርቲንግ አካዳሚ ከ15 ዓመት በታች ቡድን ወደ ማዴይራ፣ ፈንቻል ሄዶ እንደሚጫወት ከቀናት በፊት ቀድሞ ተነግሮ ስለነበር እንደ ነፍሰጡር ቀኑን ሲቆጥር ሰንብቷል። ወደዚያ መሄዱንና የናፈቃቸውን ቤተሰቦቹንና አብሮ አደግ ጓደኞቹን እንደሚያገኝ ሲያስብ ሳምንቱን ሙሉ ትኩረቱን በልምምዱ ላይ መሰብበስ አቃተው። ጨዋታው ግለኝነት በዛበት። ለጓደኞቹ ማቀበል አቆመ። ኳስ ይዞ አይለቅም። ያገኘውን ሁሉ ለጎል ይሞክራል። እግር ኳስ የቡድን ስራ መሆኑን ዘነጋው። የቡድኑ አሰልጣኝ ከተጓዥ ዝርዝሩ ውጭ ያደረገው ለዚህ ነበር። በጉዞው ባለመካተቱም ከቡድኑ ጋር ወደ ናፈቃት የትውልድ ከተማው የመጓዙ ታላቅ ዕድል አመለጠው። ሌሎች ወደ ማዴይራ ሄደው እርሱ በሊዝበን መቅረቱን ማመን አልቻለም። አለቀሰ፣ አለቀሰ፣ አለቀሰ። እምባውን አፍስሶም እልሁ ከውስጡ አልወጣልህ አለው። ከአጠገቡ ብሶቱን የሚያማክረው ሰው አጣ። በልምምድ ላይ ጥረትህን ሁሉ ሳትቆጥብ ካልሰጠህ ከአሰላለፍ ውጭ የመሆን ቅጣት እንዳለ ገና በማለዳ ተማረ። በአካዳሚው ህግ ጥፋት የፈፀመ ታዳጊ የሰልጣኞቹን የመመገቢያ ክፍል የማፅዳትና ቆሻሻውን ሰብስቦ በጋሪ የመድፋት ግዴታ ይጣልበት ነበር። አንድ ቀን የማዴይራው ልጅ ሮናልዶም መቀጣቱ አልቀረም። ይህን ሲያደርግ የተመለከቱት ታዳጊዎች ተሳለቁበት። መንጓጠጡ በዚህ ብቻ አልነበረም። ሮናልዶ ከማዴይራ ደሴት በመምጣቱ የፖርቱጊዝ አነጋገር ዘይቤው እንደ መሐል ሃገር ሰው አልነበረም። በአካዳሚው በእግር ኳስ ችሎታው የሚያማው የለም። አንድ ግዙፍ ተጫዋች "እየተሰራ" እንደሆነ ሁሉም ቢረዳም በክልል ልጅነት መገለል ገጥሞታል። በአነጋገር ዘዬው ይቀልዱበታል። ናፖሊዮን በኦገስት 15 ቀን 1769 የተወለደው በአጃክሲዮ ከተማ፣ ኮርሲካ ደሴት ነበር። ገና የ10 ዓመት ልጅ ሳለ አባቱ ለውትድርና ነፃ የትምህርት ዕድል ወደ መሐል ሃገር አካዳሚ ከላከው በኋላ ፈረንሳይኛን በኮርሲካ ቅላፄ በመናገሩ በመሳፍንት ልጆች ይሾፍበት ነበር። ነገሩ ለታዳጊው ምልምል ተማሪ መነሳሻ ሆኖት ጥረቱን ሁሉ ትምህርቱ ላይ አዋለ። ከዓመታት በኋላም ናፖሊዮን ዓለምን ቀየረ። ሮናልዶም እንደ ናፖሊዮን በስፖርታዊ ጀብድ ዓለምን መቀየሩ አልቀረም። በሰልጣኝ ታዳጊዎች ፌዝ አልተሰናከለም። ጊዜ እስኪያልፍ ለውዲቷ እናቱ እየደወለ ብሶቱን ይነግራታል። እያለቀሰ ካነጋገራት በኋላ አይኑን ጠራርጎ ወደ አካዳሚው ይመለሳል። በጥፋቱ ምግብ ቤቱን ሊጠርግ ተገደደ። ጥራጊውንም ሰብስቦ ከሌላ ቆሻሻ ጋር በእጅ በሚገፋ ጋሪ አውጥቶ መድፋት ነበረበት። ቆሻሻውን ከጊቢው ውጭ ባለ ቦታ ለመገልበጥ ጋሪዋን እየገፋ ሲወጣም አራዳ ነን ከሚሉ ልጆች ሌላ ተረብ ገጠመው። "ሃሃሃሃሃ… ሮናልዶ ፌራሪ እየነዳህ ነው እንዴ?" ሲሉ ተሳለቁበት። በንዴት የጦፈው ሮናልዶ በቁጭት መለሰላች ። "ቆይ ታያለህ… "ቆይ ታያለህ። አንድ ቀን የዓለም ምርጡ ተጫዋች እሆንና የብዙ ፌራሪዎች ባለቤት እሆናለሁ።" …………… ከክሪስቲያኖ ሮናልዶ ግለ ታሪክ መፅሐፍ ተወስዶ ለሃገራችን አንባቢዎች በሚመች መልኩ የቀረበ።
2019/05/22 18:21
የስፔን ላሊጋ የአመቱ ምርጥ ቡድን ዘንድሮ ሪያል ማድሪድ አንድም ተጫዋች አላስመረጠም ።
2019/05/21 09:24
♦የአትሌቲኮ ማድሪዱ የግብ ዘብ ኢያን ኦብሌክ ለ4ተኛ ተከታታይ ሲዝን ትንሽ ጎሎችን ያስተናገደ በረኛ መሆን ችሏል ፤ የዛሞራ ሽልማትም አሸናፊ መሆን ችሏል... 🔸2015/16 🔸2016/17 🔸2017/18 🔸2018/19 #Jan_Oblak #ZamouraAward 👏👏👏
2019/05/21 08:35
♦ፖርቱጋላዊው የማንቸስተር ሲቲ ወጣቱ ኮከብ በርናንዶ ሲልቫ ፤ የማንቸስተር ሲቲ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል... #Bernando #Salute 👏👏👏
2019/05/21 08:25
 Sports👆 ♦Opta የተሰኘው የStatistics ኩባንያ በ2018/19 ሲዝን በፕሪሚየር ሊጉ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ ሯጭ ተጫዋቾችን ይፋ አድርጓል 🔸በ3ኛ ደረጃ የተቀመጠው የዎልቭሱ ግራ ክንፍ ተመላላሽ ሩበን ቪናግሬ ሲሆን 35.20Km/hr አስመዝግቧል 🔸በ2ተኛ ደረጃ የተቀመጠው የማንቸስተር ሲቲው ካየል ዎከር ሲሆን 35.27Km/hr ተመዝግቦለታል 🔸የሊጉ ፈጣን ተጫዋች ተብሎ በ1ኛ ደረጃ የተቀመጠው የፉልለሙ ፉልባክ ቲሞቲ ፎሱ ሜንሳህ ሆኗል ፤ ፍጥነቱም 35.32Km/hr ተመዝግቦለታል
2019/05/21 07:58
1